የሲም ካርድ ደንበኝነት መረጃ ምዝገባ

ውድ የሞባይል ስልክ ደንበኞቻችን ሲም ካርድ ገዝተው በተለያየ ምክንያት የደንበኝነት መረጃችሁ በኢትዮ ቴሌኮም የመረጃ ቋት ላይ ላልተመዘገበላችሁ ደንበኞች የደንበኝነት መረጃ ምዝገባ በማከናወን ላይ እንገኛለን፡፡

የደንበኝነት መረጃዎን በማስመዝገብዎ የሚያገኟቸው ጠቀሜታዎች፡-

  • ሲም ካርድዎ ሲጠፋ ወይም በተለያየ ምክንያት ምትክ ሲም ካርድ ማውጣት ሲፈልጉ
  • የስልክ ቁጥርዎን ለሌላ ሰው ለማዘዋወር (የባለቤትነት ለውጥ ለማድረግ) ሲፈልጉ
  • ከሽያጭ በኋላ ያሉ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማግኘት ሲፈልጉ

የደንበኝነት መረጃዎን ለማስመዝገብ

  • በአቅራቢያችሁ ወደሚገኝ የህዳሴ ቴሌኮም ወይም የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በመቅረብ ውል እንድትፈፅሙ የሚገልጽ አጭር የፅሁፍ መልዕክት ይላክልዎታል እንዲሁም በ994 ጥሪ ይደረግልዎታል፡፡ በዚህም መሰረት በአቅራቢያዎ የሚገኝ የህዳሴ ቴሌኮም ወይም የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በመሄድ የታደሰ መታወቂያ እና የተላከልዎትን አጭር የፅሁፍ መልዕክት በማሳየት የደንበኝነት መረጃዎን ያስመዝግቡ፡፡

የምዝገባ ወቅት
• እስከ ጥቅምት 30/2011 ዓ.ም

ማስታወሻ
የደንበኝነት ውል እንድትፈፅሙ የሚገልፅ አጭር የፅሁፍ መልዕክት የተላከላችሁ ደንበኞች በሙሉ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ በተጠቀሱት ቦታዎች ቀርበው ውል መፈፀም ካልቻሉ ከደንበኝነት መረጃ አለመኖር ጋር ተያይዞ ለሚፈጠር ማንኛውም የአገልግሎት መቋረጥም ሆነ ሌሎች ቅሬታዎች ለማናስተናገድ የምንቸገር መሆኑን እንገልፃለን፡፡