የ47,098 ደንበኞች የሞባይል አገልግሎት ከ3ጂ ወደ 4ጂ በነፃ አደገ

ኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ኢንተርኔት አጠቃቀምን መሰረት በማድረግ 47,098 የሚደርሱ ደንበኞች የሞባይል አገልግሎትን ከ3ጂ ወደ 4ጂ በነፃ አሳደገ፡፡ በተጨማሪም ለእነዚሁ ደንበኞች ለሶስት ተከታታይ ወራት በየወሩ 100 ሜጋ ባይት የኢንተርኔት አገልግሎት በነፃ አቅርቧል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ኢትዮ ቴሌኮም 98 ሺህ ለሚደርሱ የ3ጂ ሞባይል አገልግሎት ደንበኞቹ ከህዳር 3 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎታቸውን ወደ 4ጂ...

በህገወጥ መንገድ የሞባይል ጥቅል አገልግሎት በመጠቀማቸው ምክንያት አገልግሎታቸው ተቋርጦ የነበሩ 5796 የሞባይል ቁጥሮች በመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተከፈቱ

ኢትዮ ቴሌኮም በኢትዮ ገበታ *999# አማካኝነት የድምፅ፣ የኢንተርኔት እንዲሁም አጭር የፅሁፍ መልዕክት አገልግሎቶችን ለክቡራን ደንበኞቹ በቅናሽ ዋጋ ማቅረቡ የሚታወቅ ሲሆን በርካታ ደንበኞችም የጥቅል አገልግሎቱን በመግዛት በቅናሹ ተጠቃሚ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ይህንን ህጋዊ አካሄድ ወደ ጎን በመተው በህገወጥ ተግባር ላይ ከተሳተፉ ጥቂት የተቋሙ ሰራተኞች እና ተባባሪ ግለሰቦች የሞባይል ጥቅል አገልግሎት...

ተቋርጦ የነበረው የአጭር ቁጥር አገልግሎት ሽያጭ በድጋሚ ተጀመረ !

ኢትዮ ቴሌኮም በአጭር ቁጥር አማካኝነት መረጃና የተለያዩ አገልግሎቶችን ከሚሰጡ አጋር ድርጅቶች ጋር ሲሰራ መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን ከአጋር ድርጅቶች መካከል አንዳንዶቹ ከገቡት ስምምነት ውጭ ያለደንበኛው ፈቃድ ተደጋጋሚና አሰልቺ አጭር የፅሁፍ መልዕክቶችን በመላክ በደንበኞች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ ሲፈጥሩ እንደነበረ ይታወሳል ፡፡ በዚሁ መሠረት ኢትዮ ቴሌኮም ለችግሩ ዋነኛ ምክንያት የነበረውን የአሰራር ክፍተት በመለየት ለችግሩ...

ኢትዮ ቴሌኮም የኤሌክትሮኒክ አየር ሰዓት መሙያ በመጠቀም ተጨማሪ 10% አየር ሰዓት ያግኙ!

የኢትዮ ቴሌኮም ኤሌክትሮኒክ አየር ሰዓት መሙያ በመጠቀም ተጨማሪ 10% አየር ሰዓት ያግኙ! የቅድመ ክፍያ ሞባይል ስልክዎን በኤሌክትሮኒክ የአየር ሰዓት መሙያ አገልግሎት ተጠቅመው በኢትዮ ቴሌኮም ሽያጭ ማዕከላት ወይም በአጋር ድርጅቶች አማካኝነት ሲሞሉ ከሞሉት የብር መጠን ላይ ተጨማሪ 10% የሞባይልአየር ሰዓት ያገኛሉ፡፡ አገልግሎቱን ከኢትዮ ቴሌኮም ሽያጭ ማዕከላት በተጨማሪ ከታች ከተጠቀሱት አጋር ድርጅቶች ጋር የጀመርን...

የሲም ካርድ ደንበኝነት መረጃ ምዝገባ

የሲም ካርድ ደንበኝነት መረጃ ምዝገባ ተራዘመ! ውድ ደንበኞቻችን ሲም ካርድ ገዝታችሁ በተለያየ ምክንያት የደንበኝነት መረጃችሁ በኢትዮ ቴሌኮም የመረጃ ቋት ላይ ያልተመዘገበላችሁ ደንበኞች የደንበኝነት መረጃ ምዝገባ ከጥቅምት 1 እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2011 ዓ.ም በአቅራቢያችሁ በሚገኙ የህዳሴ ቴሌኮም ወይም የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ማዕከል ቀርባችሁ መረጃችሁን እንድታስመዘግቡ ማሳወቁ ይታወሳል፡፡ ሆኖም ግን...