የፍራንቻይዝ ሽያጭ ማዕከላት

በመላ ሃገሪቱ በ32 የፍራንቻይዝ ሽያጭ ማዕከላት አማካኝነት የቴሌኮም አገልግሎት መስጠት ጀምረናል

ለክቡራን ደንበኞቻችን ቀልጣፋ እና ተደራሽ የሆነ የአገልግሎት መስጠት እንዲያስችለን በመላ ሃገሪቱ ለሙከራ የከፈትናቸው 32 ፍራንቻይዝ የሽያጭ ማዕከላት ሥራ መጀመራቸውን በደስታ እንገልፃለን ::
በማዕከላዊ አዲስ አበባ ዞን – ቦሌ ሜጋ ማተሚያ ቤት አጠገብ
በማዕከላዊ ሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን – ሱሉልታ
በሰሜን ሪጅን – ሀገረሰላም ፣ ዛላምበሳ ፣ አፅቢ እንደስላሴ ፣ ማይካድራ ፣ ዓዲጉደም እና ኮረም
በሰሜን ምዕራብ ሪጅን – አዴት፣ መራዊ፣ደንበጫ፣ ጃዊ እና እብናት
በሰሜን ሰሜን ምዕራብ ሪጅን – ሳንጃ በደቡብ ሪጅን – ቦዲቲ ፣ ጩኮ፣ ኩየራ፣ ቀባዶ እና ቦሬ

በደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን – ጊምቢቹ ፣ ሾኔ ፣ ባስኬቶ እና ገረሴ
በደቡብ ምስራቅ ሪጅን – ኢተያ ፣ ሁሩታ ፣ አለምጤና እና ቀርሳ
በደቡብ ምዕራብ ሪጅን – ዳሪሙ ፣ አመያ ፣ ያዩ ፣ አሰንዳቦ እና ዋቻ ከተማ ሲሆኑ

ክቡራን ደንበኞች በማዕከላቱ አዲስ የሞባይል አገልግሎት ወይም ሲም ካርድ መግዛትየሞባይል ካርድ ለመግዛት እንዲሁም የጠፋ ወይንም የተበላሸ ሲም ካርድ ምትክ እና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸው የድህረ ሽያጭ አገልግሎቶች ማግኘት የምትችሉ መሆኑን በደስታ እንገልፃለን፡፡
በቀጣይነትም ቀልጣፋ እና ተደራሽ የሆነ የአገልግሎት ለመስጠት እያደረግን ያለውን ጥረት በመቀጠል በቅርቡ የምንከፍታቸውን ተጨማሪ ፍራንቻይዝ የሽያጭ ማዕከላት አድራሻ እና የምንሰጣቸውን ሌሎች አገልግሎቶች የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን ፡፡