በመላው ሃገሪቱ በይሙሉ አገልግሎት የአየር ሰዓት መሸጥ የጀመሩ አጋር ድርጅቶች ቁጥር በፍጥነት በማደግ ላይ ይገኛል

ይሙሉ አገልግሎት የቅድመ ክፍያ ሞባይል እና መደበኛ ስልክ ደንበኞች በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የሽያጭ ማዕከላችን ወይም በአጋሮቻችን አማካኝነት ከ5 ብር ጀምሮ በፈለጉት የብር መጠን ካርድ ገዝተው መፋቅ ሳያስፈልጋቸው በኤሌክትሮኒክ ዘዴ የአየር ሰዓት መሙላት የሚችሉበት አገልግሎት ነው፡፡

እስከ ህዳር 30 ቀን 2011 ዓ .ም ባለው ጊዜ ውስጥ ከሽያጭ ማዕከሎቻችን በተጨማሪ በመላው ሃገሪቱ 96 የጅምላ አከፋፋዮች፣ 1733 መለስተኛ አከፋፋዮች እንዲሁም 2634 ቸርቻሪዎች በይሙሉ አገልግሎት የሞባይል አየር ሰዓት በመሸጥ ላይ የሚገኙ ሲሆን ተጨማሪ 8818 ቸርቻሪዎች ደግሞ አገልግሎቱን ለመጀመር ቅድመ ዝግጅታቸውን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

ከዚሁ በተጨማሪ ለክቡራን ደንበኞቻችን የይሙሉ አገልግሎትን የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ ተጨማሪ አጋር ድርጅቶችን ለማሳተፍ ዝግጅት ማጠናቀቃችንን እናሳውቃለን ፡፡

እስከ የካቲት 8 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ ባቀረብነው ልዩ ሽያጭ የይሙሉ አገልግሎትን ተጠቅመው ከሽያጭ ማዕከሎቻቸን ወይም በወኪል አጋሮቻችን አማካኝነት የቅድመ ክፍያ ሞባይል እና መደበኛ ስልክ አየር ሰዓት ሲሞሉ ከሚሞሉት የብር መጠን በተጨማሪ የ10 በመቶ የአየር ሰዓት ያገኛሉ ፡፡