ኢትዮ ቴሌኮም እና ማስተርካርድ በአጋርነት በማዘጋጀት ላይ በሚገኙት ዓለም አቀፍ የዲጂታል ፋይናንስ እና የሐዋላ አገልግሎቶች ላይ ተወያዩ

Ethio telecom and Mastercard

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ በምሥራቅ አፍሪካ የማስተርካርድ ሥራ አስኪያጅ ሸርያር አሊ ከተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ጋር በሁለቱ ተቋማት በዝግጅት ላይ የሚገኙ ዓለም አቀፍ የዲጂታል ፋይናንስ እና የሐዋላ አገልግሎቶችን አፈጻጸም የገመገሙ ሲሆን፣ በቀጣይ ስትራቴጂካዊ የፈጠራ ሥራዎች ላይም መክረዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን በውይይቱ ወቅት፤ ከ58 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች ያሉት የቴሌብር ስነ-ምህዳር እና የኩባንያው ግዙፍ የዲጂታል መሠረተ ልማት በሂደት ላይ ያሉ ዓለም አቀፍ አገልግሎቶችን በፍጥነት ለማስጀመር አስቻይ መደላድል መፍጠራቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም መሠረተ ልማት የሀገሪቱ የዲጂታል የነርቭ ሥርዓት በመሆን ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የዲጂታል ፋይናንስ፣ ዲጂታል የክፍያ እና የሬሚታንስ ሶሉሽኖችን በብቃት የማስተናገድ አቅም ያለው መሆኑንም አረጋግጠዋል።

ሚስተር ሸርያር አሊ በበኩላቸው፤ በሂደት ላይ ባሉ ምርትና አገልግሎት ዝግጅቶች የታየውን አፈጻጸም በማድነቅ፣ ማስተርካርድ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት በጋራ ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል።

በመጨረሻም ሁለቱ ተቋማት አገልግሎቶቹን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለደንበኞች ተደራሽ ለማድረግ ቀሪ የቴክኒክ እና የማርኬቲንግ ሥራዎችን ለማፋጠን ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ኩባንያችን አካታች የፋይናንስ ተደራሽነትን በሚያረጋግጡ፣ አዳዲስ የኢኮኖሚ ዕድሎችን በሚፈጥሩ እና የኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ የዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ ያላትን ሚና በሚያጠናክሩ አጋርነቶች “ዲጂታል ኢትዮጵያን” ለማፋጠን ያለውን ቁርጠኝነት አጠናክሮ ይቀጥላል።

ኢትዮ ቴሌኮም

መጋቢት 30,  2018

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin
Share on reddit
Share on pinterest
Share on tumblr
Share on whatsapp

Follow Us

Recent Posts

Archives