ኢትዮ ቴሌኮም እና ብሪቲሽ ኢንተርናሽናል ኢንቨስትመንት (BII) የሀገራችንን ዲጂታል እና ዘላቂ መሠረተ ልማት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችል ስትራቴጂካዊ ውይይት አደረጉ

Ethio telecom and BII

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ፤ በክሪስቶፈር ቺጂዩቶሚ (የአፍሪካ ማኔጂንግ ዳይሬክተር እና ዋና ኃላፊ) ከተመራው የዩናይትድ ኪንግደም የልማት ፋይናንስ ተቋም – ብሪቲሽ ኢንተርናሽናል ኢንቨስትመንት (BII) ከፍተኛ አመራሮች ጋር ስትራቴጂካዊ ውይይት አካሂደዋል።

በውይይቱ ወቅት ዋና ሥራ አስፈፃሚያችን ኩባንያችን እያከናወነው የሚገኘውን የትራንስፎርሜሽን ጉዞ እና ለኢትዮጵያ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት እንዲሁም ለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እያበረከተ ስላለው ጉልህ አስተዋጽኦ ገለጻ አድርገዋል። በተለይም ኩባንያችን ከመደበኛ የኮኔክቲቪቲ (Connectivity) አገልግሎት ባሻገር ፈጣን እድገት እያስመዘገበ ያለ ዲጂታል ኦፕሬተር መሆኑንና ለዘላቂና ሁለገብ ልማት እንደ አንቀሳቃሽ ሞተር ሆኖ እያገለገለ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

አክለውም ኢትዮ ቴሌኮም ዘመናዊና ሰፊ መሠረተ ልማቱን እንዲሁም የተቀናጀ የሥነ-ምህዳር ስትራቴጂውን በመጠቀም ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ እያደረገ ያለውን ስትራቴጂካዊ ሽግግር አብራርተዋል። ይህ ሥነ-ምህዳር የክላውድ ኮምፒውቲንግ አገልግሎትን፣ ሞዱላር ዳታ ሴንተሮችን፣ ሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) እና ዲጂታል መተግበሪያዎችን ከቴሌብር የፋይናንስ ቴክኖሎጂ፣ ከኢ-ኮሜርስ፣ ከኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የኃይል መሙያ መሠረተ ልማት እና በስፋት ተደራሽ ከሆነው ኔትወርክ ጋር የሚያስተሳስር ስለመሆኑ ተብራርቷል።

ይህ የተቀናጀ የዲጂታል ሥነ-ምህዳር የሞባይል ተኮር ኢኮኖሚን ለማጎልበት እና በተለያዩ ዘርፎች ፈጣን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን እውን ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን፤ ይህም በኢትዮጵያና ከዚያም ባሻገር ለሚመዘገበው ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገትና ዲጂታል ተጠቃሚነት ከፍተኛ ሚና የሚጫወት ይሆናል።

በተጨማሪም ዋና ሥራ አስፈፃሚያችን የኩባንያችንን “ቀጣዩ አድማስ፡ ዲጂታል እና ከዚያም ባሻገር 2028” ስትራቴጂ እና ስትራቴጂው በኢትዮጵያና በአጠቃላይ በአህጉራችን የዲጂታል እድገትን ለማፋጠን ያለውን ራዕይና ፋይዳ አብራርተዋል። በዚህም ኩባንያችን በኢትዮጵያና በቀጣናው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ለማፋጠን በተለያዩ የሽርክና አማራጮች አብሮ ለመሥራት ዝግጁ መሆኑን በድጋሜ አረጋግጠዋል።

ሚስተር ክሪስቶፈር ቺጂዩቶሚ እና ልዑካቸው በበኩላቸው፤ ብሪቲሽ ኢንተርናሽናል ኢንቨስትመንት (BII) በአፍሪካ ዘላቂና ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት ረገድ ትልቅ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ገልጸው፣ ኢትዮጵያም ለተቋሙ ቁልፍ ስትራቴጂካዊ አጋር መሆኗን ገልጸዋል። ብሪቲሽ ኢንተርናሽናል ኢንቨስትመንት በአህጉሪቱ ካሉ የግል ዘርፍ ተቋማት ጋር በቅርበት የሚሠራ ስለመሆኑና የአፍሪካን ዘላቂ ልማት የሚደግፉ ሀብቶችን ለማሰባሰብ ከተለያዩ አካላት ጋር በትብብር እንደሚሠራ ጠቁመዋል።

ዋና ሥራ አስፈፃሚያችንም የኢትዮ ቴሌኮም ራዕይና እሴቶች ከብሪቲሽ ኢንተርናሽናል ኢንቨስትመንት (BII) ጋር በተለይም ዘላቂ መሠረተ ልማትን በማስፋፋት፣ በአየር ንብረት ለውጥ የማይበገሩ የዲጂታል ሥነ-ምህዳሮችን በመገንባትና በአረንጓዴ ኢነርጂ ውጥኖች ረገድ ተመሳሳይ ግቦች እንዳሏቸው ገልጸዋል።

በዚህም የሁለቱም ተቋማት አመራሮች የጋራ ራዕያቸውን ለመደገፍ፣ የዲጂታል ኢኮኖሚውን ለማሳደግ፣ ሁሉን አቀፍ የፋይናንስ ቴክኖሎጂን ለማስፋፋት እና የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የዲጂታል መሠረተ ልማትን ለመገንባት የሚያስችሉ ኢንቨስትመንቶችን በማሰባሰብ የ”ቀጣዩ አድማስ” ስትራቴጂን ትግበራ ለማፋጠን በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል።

የብሪቲሽ ኢንተርናሽናል ኢንቨስትመንት (BII) ልዑክ በበኩሉ ኢትዮ ቴሌኮም ለኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ መሠረትና ለአገራዊ የኢኮኖሚ እድገት ቁልፍ አንቀሳቃሽ መሆኑን ገልጾ፤ የዋና ሥራ አስፈፃሚያችንን አርቆ አሳቢ አመራር፣ የኩባንያችንን ውጤታማ የዘላቂነት ሥራዎች እና የወደፊት የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አጀንዳን አድንቀዋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያን የዲጂታል እና ዘላቂ መሠረተ ልማት ለመደገፍ በዩናይትድ ኪንግደም የሚደገፉ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለመፍጠር ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።

በመጨረሻም ዋና ሥራ አስፈፃሚያችን ለብሪቲሽ ኢንተርናሽናል ኢንቨስትመንት (BII) ልዑካን አዲስ የኢኮኖሚ ዕድሎችን ለመፍጠርና አገራዊ ልማትን ለማፋጠን ለሚያደርጉት ዓለም አቀፍ ትብብር ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ሁለቱ አመራሮች ውይይቱን ለመቀጠልና ተጨባጭ የሆኑ የትብብር መስኮችን በመለየት ዘላቂ ውጤት ለማምጣት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በስፋት ተወያይተዋል፡፡

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin
Share on reddit
Share on pinterest
Share on tumblr
Share on whatsapp

Follow Us

Recent Posts

Archives