የኢትዮ ቴሌኮም ኤሌክትሮኒክ አየር ሰዓት መሙያ በመጠቀም ተጨማሪ አየር ሰዓት ያግኙ!

የቅድመ ክፍያ ሞባይል ስልክዎን በኤሌክትሮኒክ የአየር ሰዓት መሙያ አገልግሎት ተጠቅመው በኢትዮ ቴሌኮም ሽያጭ ማዕከላት ወይም በአጋር ድርጅቶች አማካኝነት ሲሞሉ ከሞሉት የብር መጠን ላይ ተጨማሪ የሞባይልአየር ሰዓት ያገኛሉ፡፡
አገልግሎቱን ከኢትዮ ቴሌኮም ሽያጭ ማዕከላት በተጨማሪ ከታች ከተጠቀሱት አጋር ድርጅቶች ጋር የጀመርን ሲሆን በቀጣይም ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር ለመጀመር እየሰራን መሆኑን እንገልፃለን።

የአገልግሎቱ ጠቀሜታ

•  ለአጠቃቀም ምቹ፣ ፈጣን፣ ቀላል እና ደህንነቱ የተጠበቀ የአየር ሰዓት መሙያ ዘዴ ነው፡፡
•  ከ5 ብር ጀምሮ የፈለጉትን የአየር ሰዓት መጠን መሙላት ያስችልዎታል (ለምሳሌ 6፣ 7፣ 8….)
•  የይሙሉ አገልግሎት አጋር ድርጅቶች እና ወኪሎቻቸው ባሉበት በሁሉም ስፍራ አገልግሎቱን ማግኘት ያስችልዎታል፡፡
•  የቅድመ ክፍያ የአየር ሰዓት በሞባይል ስልክዎ ከየትኛውም ቦታ ሆነው መሙላት ያስችልዎታል፡፡
•  በተጨማሪም አገልግሎቱ ለሃይብሪድ ሞባይል ደንበኞች (በቅድመ ክፍያ አካውንቱ ላይ) የአየር ሰዓት መሙላት ያስችላል፡፡

አገልግሎቱን ለማግኘት

የኤሌክትሮኒክ የአየር ሰዓት መሙያ አገልግሎትን ለመጠቀም የሚከተሉትን አማራጮች በመጠቀም ማግኘት ይችላሉ።
1ኛ   በኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከላት እንዲሁም በአጋር ድርጅቶች እና ወኪሎቻቸው አማካኝነት የሞባይል የአየር ሰዓት መግዛት ሲፈልጉ ለሻጩ በቀጥታ የሞባይል ስልክ ቁጥርዎንና መሙላት የፈለጉትን የገንዘብ መጠን ብቻ በመንገር የአየር ሰዓቱን መሙላት ይችላሉ፡፡
2ኛ  የባንኮች ወይም የፋይናሺያል ተቋማት የሞባይል ዋሌት ተጠቃሚ የሆኑ ደንበኞች አገልግሎቱን በሚያገኙበት አጭር ቁጥር (USSD) ላይ በመደወል ከሚመጣው ዝርዝር ውስጥ የሞባይል የአየር ሰዓት/ የሞባይል ካርድ/ ካርድ ወይም የአየር ሰዓት የሚለውን በመምረጥ መመሪያውን ተከትለው መሙላት ይችላሉ፡፡
3ኛ  በባንኮች ወይም በፋይናሺያል ተቋማት (ሲቢኢ ብር፣ ሄሎ ካሽ፣ ኤም ብር እና ኢብር) በኩል በሞባይል ዋሌት አገልግሎቱን በሚያገኙበት አጭር ቁጥር በመጠቀም የሚፈልጉትን የሞባይል የአየር ሰዓት መጠን መሙላት ይችላሉ።

 

  • በአጋር ድርጅቶች እና ህጋዊ ወኪሎች በኩል የመታወቂያ ዋናውን እና ኮፒ ይዞ በመቅረብ የመመዝገቢያ ቅፅ በመሙላት መመዝገብ
  • ተመዝግበው ደንበኝነት ከፈፀሙ በኋላ አካውንትዎ ላይ ገንዘብ ተቀማጭ ማድረግ
  • በድርጅቱ የሚሰጥዎት የአገልግሎት መጠቀሚያ አጭር ቁጥር (USSD) ላይ በመደወል ከሚዘረዘሩት የአገልግሎት አይነቶች ውስጥ የሞባይል የአየር ሰዓት/ የሞባይል ካርድ/ካርድ ወይም የአየር ሰዓት የሚለውን በመምረጥ መመሪያውን በመከተል መሙላት ይችላሉ፡፡