ኩባንያችን እና አፍሬክሲም ባንክ አህጉራዊ የዲጂታል ሽግግርን ለማፋጠን በሚያስችሉ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

Ethio telecom & Afreximbank Join Forces to Accelerate Africa’s Digital Future!

ኩባንያችን ከአፍሪካ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በዋና መሥሪያ ቤታችን ስትራቴጂካዊ ውይይት አድርጓል። ውይይቱ በዋናነት ባንኩ አዲስ ለሾማቸው የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ዳይሬክተርና የልዑካን ቡድን መሪ ሚስተር ሀምፍሬይ ንውጎ የእንኳን ደህና መጡ መልዕክት ለማስተላለፍ እንዲሁም የሀገራችንን የዲጂታል ሽግግር የሚያፋጥኑ የፋይናንስ አጋርነቶችን ለመፍጠር ያለመ ነው።

በመድረኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ፍሬሕይወት ታምሩ ኩባንያችን ባለፉት ስትራቴጂካዊ ዓመታት ያስመዘገባቸውን ስኬቶችና እያከናወነ ያለውን የትራንስፎርሜሽን ጉዞ ለባንኩ አመራሮች ገለጻ አድርገዋል። ገለጻው የኩባንያችንን ጠንካራ የፋይናንስና የኦፕሬሽን አፈጻጸም፣ የገበያ መሪነት፣ እያደገ የመጣውን የዲጂታል ሥነ-ምህዳር እንዲሁም ለሀገራዊ ዲጂታል ሽግግርና ለማኅበረ-ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እያበረከትን ያለውን ቁልፍ ሚና ያመላከተ ነው።

ውይይቱ የአፍሬክሲም ባንክን ግዙፍ አህጉራዊ የፋይናንስ አቅም ከኩባንያችን “ቀጣዩ አድማስ፡ ዲጂታል እና ከዚያም ባሻገር 2028” ስትራቴጂ ጋር በማጣጣም ላይ ትኩረት አድርጓል። ኩባንያችን ከመደበኛ የቴሌኮም ኦፕሬተርነት ወደ ቀጣናዊ የቴክኖሎጂ ተቋምነት እያደረገ ያለውን ሽግግር ያሳዩት እንደ ቴሌብር፣ ዘመን ገበያ፣ ቴሌስትሪም፣ የላቁ የክላውድ አገልግሎቶችና ዜድ-ኔክሰስ ለመሳሰሉት የዲጂታል ሥነ-ምህዳር መፍትሔዎቻችን የተሰጠው ትኩረት ተመልክቷል።

የአፍሬክሲም ባንክ ልዑካን ቡድን በበኩላቸው በኩባንያችን ጠንካራ የፋይናንስ አፈጻጸም፣ በአመራር ብቃትና በቀጣናዊ የማስፋፊያ ግቦቻችን መደመማቸውን ገልጸው፤ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ስትራቴጂካዊ የፋይናንስ አጋርነት ለመፍጠር ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።

ሁለቱም ተቋማት የዲጂታል መሠረተ ልማታችንን የሚያጠናክሩ፣ የድርጅቶችን የዲጂታል ሽግግር የሚደግፉና በአህጉሪቱ ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት እንዲመዘገብ የሚያስችሉ የፋይናንስ አማራጮችን ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኝነታቸውን ያረጋገጡ ሲሆን ይህም ይበልጥ ሁሉነ አቀፍ፣ አካታችና የበለጸገ አህጉራዊ የዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት በምናደርገው ጥረት ውስጥ ትልቅ ተስፋ የሚጣልበት ስትራቴጂካዊ እርምጃ መሆኑ ተመላክቷል።

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin
Share on reddit
Share on pinterest
Share on tumblr
Share on whatsapp

Follow Us

Recent Posts

Archives