የሞባይል ኮንፍረንስ ጥሪ አገልግሎት

የሞባይል ኮንፍረንስ ጥሪ አገልግሎት፣ በሞባይል ስልክ እንደፍላጎትዎ እስከ 5 ከሚደርሱ ወዳጅ ዘመድዎ ወይንም የቢዝነስ አጋርዎ ጋር በተመሳሳይ ሰዓት ጥሪ ማድረግ/ማነጋገር የሚያስችልዎት አገልግሎት ነው፡፡

አጠቃቀም

  1. ወደ ሚፈልጉት ወዳጅ ዘመድዎ ወይንም የቢዝነስ አጋርዎ ይደውሉ እና ስልኩ እስኪነሣ ይጠብቁ
  2.  በመቀጠልም የደወሉላቸው ወዳጅ ዘመድዎ ወይንም የቢዝነስ አጋርዎ መስመር ላይ እንዲቆዩ ይንገሩ እና “Add call” የሚለውን በመጫን ወደ ሁለተኛው ሰው በመደወል ስልኩ ከተነሳ በኋላ እንደ  እንደሚጠቀሙት የስልክ ቀፎዎ አይነት Merge የሚለዉን ምርጫ ወይም Option ውስጥ ገብተው Conference ወይም Join የሚለውን ምርጫ በመጫን የኮንፍረንስ ጥሪውን ማድረግ ይችላሉ ። ተጨማሪ ሰዎች ወደ ኮንፍረንስ ጥሪ ለማስገባት ከፈለጉ በተራ ቁጥር 2 ላይ የተቀመጠውን ሂደት  በመከተል እስከ 5 ሰዎች ማስገባት ይችላሉ፡፡