የሞባይል ጥቅል አገልግሎት የቆይታ ጊዜን በተመለከተ ከክቡራን ደንበኞቻችን ለቀረቡልን ጥያቄዎች የተሰጠ ማብራሪያ

የኢንተርኔት ፣ የድምፅ እና የአጭር የፅሁፍ መልዕክት ጥቅል አገልግሎት

የጥቅል አይነት የጥቅል የቆይታ ጊዜ
ዕለታዊ 24 ሰዓት
ሳምንታዊ 7 ቀናት
ወርሃዊ 30 ቀናት

ዕለታዊ ጥቅል:- የጥቅል አገልግሎቱን ከገዙበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 24 ሰዓታት ድረስ የሚቆይ ሲሆን
ለምሳሌ:- ታህሳስ 3 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 11፡15 ሰዓት የገዙት ጥቅል እስከ ታህሳስ 4 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 11፡15 ሰዓት ድረስ የአገልግሎት ቆይታ ጊዜ ይኖረዋል፡፡

ሳምንታዊ ጥቅል:- የጥቅል አገልግሎቱን ከገዙበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 7 ቀናት የሚቆይ ሲሆን
ለምሳሌ:- ታህሳስ 3 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 11፡15 ሰዓት የገዙት ጥቅል እስከ ታህሳስ 10 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 11፡15 ሰዓት ድረስ የአገልግሎት ቆይታ ጊዜ ይኖረዋል፡፡

ወርሃዊ ጥቅል:- የጥቅል አገልግሎቱን ከገዙበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 30 ቀናት የሚቆይ ሲሆን
ለምሳሌ:- ታህሳስ 23 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 11፡15 ሰዓት የገዙት ጥቅል እስከ ጥር 23 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 11፡15 ሰዓት ድረስ የአገልግሎት ቆይታ ጊዜ ይኖረዋል፡፡ በዚሁ መሰረት የወርሃዊ ጥቅል የቆይታ ጊዜ ከመደበኛው የወር መጀመሪያ እና መጨረሻ ቀናት አቆጣጠር ጋር ግንኙነት የሌለው መሆኑን እንገልፃለን፡፡

በስራ ላይ ያለው የጥቅል አገልግሎት ቆይታ ጊዜ ከላይ እንደተጠቀሰው ሲሆን እንደ አጠቃቀምዎ ሁኔታ የጥቅል አገልግሎቱን ከተጠቀሰው የጊዜ ገደብ በፊት ተጠቅመው ሊጨርሱ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ከጥቅል አገልግሎት ጋር በተያያዘ ማንኛውም አይነት ችግር ሲገጥምዎ 994 በመደወል ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችን መልዕክትዎን ማስቀመጥ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡