የሲም ካርድ ደንበኝነት መረጃ ምዝገባ ተራዘመ!

ውድ ደንበኞቻችን

ሲም ካርድ ገዝታችሁ በተለያየ ምክንያት የደንበኝነት መረጃችሁ በኢትዮ ቴሌኮም የመረጃ ቋት ላይ ያልተመዘገበላችሁ ደንበኞች የደንበኝነት መረጃ ምዝገባ ከጥቅምት 1 እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2011 ዓ.ም በአቅራቢያችሁ በሚገኙ የህዳሴ ቴሌኮም ወይም የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ማዕከል ቀርባችሁ መረጃችሁን እንድታስመዘግቡ ማሳወቁ ይታወሳል፡፡ ሆኖም ግን ለምዝገባ የተዘጋጁ ማዕከላት ለምዝገባ ከሚቀርቡት ደንበኞች ቁጥር ጋር ባለመመጣጠኑ ምክንያት ደንበኞች ለከፍተኛ ሰልፍ በመዳረግ መጉላላት እንደደረሰባቸው ተገንዝበናል፡፡ ለዚህም ይቅርታ እየጠየቅን ምዝገባውን ለሁለት ወራት/እስከ ታህሳስ 3ዐ ቀን 2ዐ11 ዓ.ም  ድረስ ማራዘማችንን እየገለጽን የተከበራችሁ ደንበኞቻችን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ምዝገባውን እንድታከናውኑ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

ከህዳሴቴሌኮም እና ከኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በተጨማሪ የደንበኝነት መረጃ ምዝገባውን በሌሎች አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ለማከናወን የሚያስችል ዝግጅት እያጠናቀቅን ሲሆን አገልግሎት መስጠት ሲጀምር የምናሳውቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡