የአካውንት ማጋራት አገልግሎት

ሞባይልዎ ላይ ካሎት የአየር ሰዓት ለኢንተርኔት ፤ ለድምፅ ጥሪ ፤ ለአጭር የፅሁፍ መልዕክት ወይም ለሁሉም አገልግሎቶች የሚውል አየር ሰዓት ለፈለጉት ሰው ከአካውንትዎ ላይ በቀጥታ እንዲጠቀም የሚፈቅዱበት የአገልግሎት አይነት ነው፡፡

አገልግሎቱን ለማግኘት
በማንኛውም ጊዜ በኢትዮ ገበታ *999# ደውለው ž ለተጨማሪ አገልግሎት 2ን ይጫኑ ž አካውንትዎን ለማጋራት 3ን ይጫኑ እና ይመዝገቡ በመቀጠል የሚፈልጓቸውን አገልግሎቶች ማለትም ተጋሪ መጨመር፣ ተጋሪ መቀነስ እንዲሁም የአከፋፈል ቅደም ተከተልን ለመወሰን በድጋሚ *999# ይደውሉ፡፡
የአየር ሰዓት አጋሪ ደንበኛ
•ካሎት የአየር ሳዓት ላይ ወዳጅ ዘመድዎ እንዲጠቀሙበት ለመፍቀድ በቅድሚያ የአካውንትዎን ያጋሩ አገልግሎት ደንበኛ መሆን ይኖርብዎታል፡፡
• ለድምፅ፤ ለአጭር የፅሁፍ መልዕክት፤ ለኢንተርኔት ወይም ለሁሉም አገልግሎቶች የሚውል የአየር ሰዓት በዕለታዊ፣ ሳምንታዊ ወይም ወርሃዊ አጠቃቀም ገደብ በመወሰን ወይም ያለገደብ እንዲጠቀሙ መፍቀድ
ይችላሉ፡፡
• የአየር ሳዓትዎን ሊያጋሩት የሚፈልጉትን ሰው የሞባይል ቁጥር የአየር ሳዓት ተጋሪዎች አባል ዝርዝር ውስጥ ማካተት አለብዎት፡፡
• የአየር ሳዓት ተጋሪው ደንበኛ ቅድሚያ የራሱን ወይም የተሰጠውን የአየር ሳዓት እንዲጠቀም ማድረግ ይችላሉ፡፡ • በማንኛውም ጊዜ የአየር ሳዓት ተጋሪ ደንበኛ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላሉ፡፡
የአየር ሰዓት ተጋሪ ደንበኛ
• የአየር ሳዓት አጋሪው ደንበኛ ከፈቀደልዎት የአገልግሎት አይነት እና መጠን ውጪ መጠቀም አይችሉም፡፡
• በአንዴ ከአንድ አጋሪ በላይ የአየር ሳዓት መቀበል አይችሉም፡፡
• የተሰጠዎትን የአየር ሳዓት ለሃገር ውስጥም ሆነ ለዓለም አቀፍ አገልግሎቶች መጠቀም ይችላሉ፡፡
• የአየር ሳዓት ተጋሪው ደንበኛ ከተፈቀደለት የአየር ሳዓት ላይ ጥቅል ገዝቶ ለራሱ ብቻ መጠቀም ይችላል፡፡

የአጠቃቀም ደንብ

• ሁሉም የድህረ ክፍያ፣ ሃይብሪድ እና የቅድመ ክፍያ አገልግሎት ደንበኞች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡ • የአየር ሳዓት አጋሪው ደንበኛ ተጋሪው ደንበኛ የተጠቀመበትን የአየር ሳዓት የሚከፍል ሲሆን፤ ተጋሪው ደንበኛ ከተላከለት የአየር ሳዓት ለሌላ ሰው ማጋራት አይችልም፡፡
• የአየር ሳዓት አጋሪው ደንበኛ ተጋሪው ደንበኛ እንዲጠቀም ከፈቀደለት የአየር ሰዓት ላይ ያልተጠቀመበት
ቀሪ የአየር ሳዓት ካለ ለራሱ መጠቀም ይችላል፡፡
• የድህረ ክፍያ ደንበኛ ለተጋሪው የሚያጋራው የአየር ሰዓት ተ.እ.ታ ን የማያጠቃልል ሲሆን የቅድመ ክፍያ ደንበኛ የሚያጋራው የአየር ሰዓት ተ.እ.ታን ያጠቃልላል፡፡
• የአየር ሳዓት አጋሪው ደንበኛ ከሌላ የአየር ሳዓት አጋሪ ደንበኛ ላይ የአየር ሳዓት ተጋሪ አባል መሆን አይችልም፡፡
• የቅድመ ክፍያ ደንበኞች ለድህረ ክፍያ ደንበኞች የአየር ሳዓት ማጋራት አይችሉም፡፡