አካታች ሀብትን ማፍራት!

እንኳን ወደ ኢትዮ ቴሌኮም የኢንቨስተር ሪሌሽንስ ፖርታል በደህና መጡ!

ይህ ፖርታል የፋይናንስ ሪፖርቶችን፣ የሁለተኛ ገበያ መረጃዎችን፣ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ቁልፍ ተቋማዊ ሰነዶችን ግልጽ እና ምቹ በሆነ መንገድ ለማቅረብ የተዘጋጀ ይፋዊ መድረክ ነው።

መድረኩ ግልጽነትን ለማጠናከር፣ የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ለማሳደግ እና ትክክለኛ መረጃ ላይ የተመሰረተ የኢንቨስትመንት ውሳኔን ለመደገፍ የተቋቋመ ነው።

K
የእኛ ኢንቨስተሮች
B
የአክሲዮን ዋጋ (በኢትዮጵያ ብር)
M
በዲጂታል መልክ የተመዘገቡ አክሲዮኖች
Investor banner

ኢንቨስተሮች ግንኙነት

የፋይናንስ ሪፖርቶች

ዓመታዊ ሪፖርቶች፣ የሩብ ዓመት ውጤቶች እና በኦዲት የተረጋገጡ የፋይናንስ መግለጫዎች።

ኢንቨስተሮች. ግንኙነት . ዜና

CEO at ESX

ኢትዮ ቴሌኮም ባለአክሲዮኖቹ አክሲዮናቸውን በሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ገበያ እንዲያስተዳድሩ፣ እንዲገዙና እንዲሸጡ ማስቻሉን በታላቅ ደስታ ያበስራል!

መንግሥት በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ዕቅዱ በርካታ ኢኮኖሚያዊ ለውጦችን በማድረግ ቀጣይነት ያለው ሀገራዊ የጋራ ዕድገትን ለማረጋገጥ ከወሰዳቸው ስትራቴጂያዊ እርምጃዎች መካከል...

Read full news here
teleshare

ኢትዮ ቴሌኮም ከ47 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች ባለድርሻ የሚሆኑበት ወሳኝ ታሪካዊ ምዕራፍ ላይ በመድረሱ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል!!

መንግስት በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው በርካታ ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያዎችን በማድረግ ቀጣይነት ያለው ሀገራዊ የጋራ እድገትን ለማረጋገጥ ከወሰዳቸው ስትራቴጂያዊ እርምጃዎች መካከል የኢትዮጵያ...

Read full news here

የዳይሬክተሮች ቦርድ

ከሥራ አስፈፃሚ አመራሮቻችን ጋር ይተዋወቁ

ለምን ኢትዮ ቴሌኮም?

87.9 ሚሊዮን ደንበኞች

58 ሚሊዮን የቴሌብር ደንበኞች

99% የሕዝብ ሽፋን

የ4ጂ ሽፋን
80% የህዝብ ሽፋን

የ5ጂ ሽፋን
28 ከተሞች

ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ

Upcoming

በተደጋጋሚ የተነሱ ቅሬታዎች

ባለሥልጣኑ የገበያውን ፍትሐዊነትና ግልጽነት የሚቆጣጠር የመንግሥት አካል ነው። ዋና ዓላማውም የባለሀብቶችን (የእርስዎን) መብት መጠበቅ እና ሕገ-ወጥ አሰራሮችን መከላከል ነው።

የካፒታል ገበያ ማለት ኩባንያዎች አክሲዮን ወይም ቦንድ በማውጣት ከህዝብ ወይም ከተቋማዊ ባለሀብቶች ገንዘብ ማሰባሰብ የሚችሉበት ሲሆን የሚሰባሰበውም ገንዘብ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ለመጀመር፣ የስራ እንቅስቃሴን ለማስፋፋት፣ ቴክኖሎጂን ለማሻሻል እና ተጨማሪ የስራ ዕድሎችን ለመፍጠር ያግዛል። መንግስትም በቦንድ ሽያጭ አማካኝነት ለመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች፣ ለመንገድ፣ ለኤሌክትሪክ፣ ለውሃ እና ለሌሎች የህዝብ አገልግሎት ስራዎች ፋይናንስ ማግኘት ይችላል። በሌላ በኩል ባለሀብቶች በካፒታል ገበያ በመሳተፍ ቁጠባቸውን በትርፍ የሚያድጉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ማዋል ይችላሉ። ከአክሲዮን የትርፍ ክፍፍል (Dividend) ወይም ከዋጋ ጭማሪ ትርፍ ማግኘት ሲችሉ፣ ከቦንድ ደግሞ በወለድ መልክ ተመላሽ ገቢ ያገኛሉ።

በአጠቃላይ የካፒታል ገበያ ዋና ዓላማ በሀገር ውስጥ ያለውን ቁጠባ ወደ ምርታማ የኢንቨስትመንት ዘርፎች በማዘዋወር የኢኮኖሚ እድገትን ማጠናከር፣ የኩባንያዎችን መስፋፋት መደገፍ፣ የስራ ፈጠራን ማበረታታት እና የፋይናንስ ስርዓቱን ግልፅነትና ተደራሽነት ማሳደግ ነው።

የአክሲዮን ድርሻ ማለት በአንድ ኩባንያ ውስጥ ያለ የባለቤትነት ድርሻ ነው። አክሲዮን የሚገዛ ሰው በዚያ ኩባንያ ውስጥ ባዋለው አክስዮን መጠን ተመጣጣኝ የባለቤትነት መብት ያገኛል። ይህም ማለት ባለአክሲዮኑ በኩባንያው ሀብት፣ ትርፍ እና አስተዳደር ላይ በያዘው ድርሻ መጠን ሕጋዊ መብትና ጥቅም እንዲኖረው ያደርጋል።

አክሲዮን የሚገዛ ሰው “ባለአክሲዮን” ወይም “ባለድርሻ” ተብሎ ይጠራል። ባለአክሲዮኑ በኩባንያው ውስጥ በያዘው የአክሲዮን መጠን መሰረት የትርፍ ክፍፍል (Dividend) ሊያገኝ ይችላል፣ እንዲሁም በጠቅላላ ጉባኤዎች ድምጽ የመስጠት እና ተጨማሪ አክስዮኖችን ድርጅቱ ለገበያ ሲያቀርብ በቅድሚያ የመገዛት መብት፣ በኩባንያው አስተዳደር ላይ ተሳትፎ የማድረግ መብት ይኖረዋል፡፡

ከኢትዮ ቴሌኮም እና መሰል ድርጅቶች አክስዮን የገዙ ባለአክስዮኖች ህጋዊ የሆኑና በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ፍቃድ ያገኙ አክስዮኖችን ስነድ ሙዓለንዋይ ለማገበያየት ፈቃድ በተሰጣችው አገበያዮች አማካኝነት ባለአክስዮኖች ያላቸውን ድርሻ መሸጥ፣ መግዛት እንዲሁም ያላቸውን የአክስዮን መጠን ማስተዳደር ይችላሉ።

አክሲዮን ለመግዛት ወይም ለመሸጥ ባለአክሲዮኑ በመጀመሪያ በተፈቀደ ብሮከር ወይም አገበያይ ዘንድ የግብይት ሂሳብ (Trading Account) መክፈት ይጠበቅበታል። ከዚያ በኋላ አክሲዮን ለመግዛት ወይም ለመሸጥ ትዕዛዝ ለብሮከሩ ይሰጣል። ብሮከሩም በገበያው ውስጥ ገዢና ሻጭን በማገናኘት ግብይቱ እንዲፈጸም ያደርጋል።

ባለአክሲዮኖች በዚህ ሂደት ያላቸውን የአክሲዮን መጠን መከታተል፣ ተጨማሪ አክሲዮን መግዛት፣ ወይም ያላቸውን ድርሻ በሙሉ ወይም በከፊል መሸጥ ይችላሉ። እንዲሁም የአክሲዮን ዋጋ በገበያ ሁኔታ፣ በኩባንያው አፈጻጸም እና በባለሀብቶች ፍላጎት መሰረት ስለሚለዋወጥ የመሸጫና የመግዣ ዋጋ በገበያ ይወሰናል።

ባለአክሲዮኖች በማንኛውም ጊዜ ከአክሲዮናቸው ጋር በተያያዘ ጥያቄ፣ ማብራሪያ ወይም በአክሲዮን አስተዳደር ሂደት ላይ ማንኛውም እክል ከገጠማቸው፣ በተቋማችን የባለአክሲዮኖች ጉዳይ የሚከታተለውን የስራ ክፍል በአካል በመቅረብ ወይም በድህረ ገጽ፣ በስልክ እና በሌሎች የመገናኛ አማራጮች በመጠቀም አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ። የስራ ክፍሉም ባለአክሲዮኖች በተገቢው መረጃ እንዲደገፉ፣ ጥያቄዎቻቸው በአግባቡ እንዲመለሱ እና የአክሲዮን አስተዳደር ሂደታቸው በቀላሉ እንዲከናወን አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል።

ባለአክሲዮኖች ስለ ተቋማችን የስራ እንቅስቃሴ፣ የፋይናንስ አፈጻጸም፣ አዳዲስ ፕሮጀክቶች፣ የአክሲዮን ጉዳዮች እና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎችን ለማወቅ የተቋማችንን ድህረ ገጽ በመጎብኘት መረጃ ማግኘት ይችላሉ። በድህረ ገጹ ላይ “Investor Relations” ወይም “የኢንቨስተር ግንኙነት” ተብሎ በተዘጋጀው ክፍል ውስጥ በመግባት ለባለአክሲዮኖች የሚጠቅሙ የተለያዩ መረጃዎችን እና ማስታወቂያዎችን ማየት ይችላሉ።

በዚህ ክፍል ውስጥ የኩባንያው ዓመታዊ ሪፖርቶች፣ የፋይናንስ መግለጫዎች፣ የጠቅላላ ጉባኤ ማስታወቂያዎች፣ የትርፍ ክፍፍል መረጃዎች፣ አዳዲስ የኢንቨስትመንት እቅዶች እና ለባለአክሲዮኖች አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች መረጃዎች በተደራጀ ሁኔታ ይቀርባሉ።

የኩባንያው ባለአክሲዮን ከሆኑ በኋላ በጠቅላላ ጉባኤ (General Assembly) ላይ የመሳተፍ መብት ይኖርዎታል። ጠቅላላ ጉባኤው የኩባንያው ከፍተኛ ውሳኔ ሰጪ አካል ሲሆን፣ ባለአክሲዮኖች በኩባንያው አስተዳደር፣ በፋይናንስ አፈጻጸም እና በወደፊት እቅዶች ላይ ውይይት ለማድረግና ውሳኔ ለመስጠት የሚሳተፉበት መድረክ ነው።

ኩባንያው የጠቅላላ ጉባኤውን ቀን፣ ቦታ፣ ሰዓት እና አጀንዳ በኢትዮጵያ የንግድ ህግ እና በሚመለከታቸው ደንቦች መሰረት በቅድሚያ በይፋ ያሳውቃል። ይህ ማስታወቂያ በድህረ ገጽ፣ በመገናኛ ብዙሃን ወይም በሌሎች ሕጋዊ የማሳወቂያ መንገዶች ሊቀርብ ይችላል።

ባለአክሲዮኖች በጉባኤው ላይ በአካል በመገኘት መሳተፍ እንዲሁም በሕጋዊ ተወካይ (Proxy) አማካኝነት መወከል ይችላሉ። በጉባኤው ላይ ባለአክሲዮኖች የድምጽ መስጠት፣ ጥያቄ ማቅረብ፣ ሀሳብ መስጠት እና በአጀንዳ ላይ በሚቀርቡ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ለመስጠት መብት አላቸው።

በተጨማሪም በጠቅላላ ጉባኤው ውስጥ የኩባንያው ዓመታዊ ሪፖርት፣ የፋይናንስ መግለጫዎች፣ የትርፍ ክፍፍል ጉዳዮች፣ የቦርድ ሹመቶች እና ሌሎች አስፈላጊ የኩባንያ ውሳኔዎች ይመረመራሉ እና ይፀድቃሉ።

የባለአክሲዮን መረጃዎን ማስተካከል ከፈለጉ አክሲዮኑን ለመግዛትና ለመሸጥ ፍቃድ በተሰጣቸው ተቋማት ወይም በተቋማችን ለባለአክስዮኖች ጉዳይ ለመከታተል በተቋቋመው የስራ ክፍል በመቅረብ ማስተካከል ይችላሉ። እንደ ስም፣ አድራሻ፣ ስልክ ቁጥር፣ የባንክ ሂሳብ እና ሌሎች መረጃዎች ለማስተካከል/ ለውጡን ለማድረግ የታደሰ መታወቂያ እና ሌሎች አስፈላጊ ሕጋዊ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይጠበቅብዎታል።

ትርፍ የሚከፈለው ኩባንያው ትርፋማ ሆኖ ሲገኝና የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ትርፍ እንዲከፋፈል ሲወስን ነው። ክፍያው በባለአክሲዮኑ ቴሌብር የሂሳብ ቁጥር ገቢ ይደረጋል።

በካፒታል ገበያ ውስጥ የአክሲዮን ዋጋ የሚወሰነው በገበያው ውስጥ ባለው የፍላጎትና የአቅርቦት ሁኔታ ነው። ኩባንያው ውጤታማ ስራ ሲሰራ የአክሲዮኑ ፈላጊ ስለሚጨምር ዋጋው ከፍ ይላል።

አዎ፣ በካፒታል ገበያ ላይ የተመዘገቡ አክሲዮኖችን ከባንክ ለሚወሰድ ብድር እንደ ዋስትና ወይም ማስያዣነት መጠቀም ይቻላል።

አዎ፣ አክሲዮን ሲገዙም ሆነ ሲሸጡ ግብይቱን ለሚያስተናግደው የኢንቨስትመንት ባንክ፣ ደላላ (Broker) ወይም ሌላ ፈቃድ ያለው የካፒታል ገበያ አገበያይ የአገልግሎት ክፍያ (Commission Fee) መክፈል ይኖርበታል። ይህ ክፍያ ገዢና ሻጭን በማገናኘት፣ የግብይት ሂደቱን በማስተዳደር እና ግብይቱ በህጋዊና በተደራጀ ሁኔታ እንዲፈጸም ለሚሰጠው አገልግሎት የሚከፈል ነው።

አዎ፣ በኢትዮጵያ የገቢ ግብር ሕግ መሠረት ከትርፍ ክፍፍል (Dividend) ላይ የሚቆረጥ የገቢ ግብር ይኖራል። ኩባንያው ትርፉን ለባለአክሲዮኖች ከማከፋፈሉ በፊት በህግ የተወሰነውን የታክስ መጠን በመቀነስ (withholding tax) ቀንሶ በቀጥታ ለገቢዎች ሚኒስቴር ያስገባል።

አዎ፣ ባለአክሲዮኖች አክሲዮናቸውን በስጦታ ወይም በውርስ ለሌላ ሰው ማስተላለፍ ይችላሉ። ሆኖም ይህ ሂደት በካፒታል ገበያ ባለሥልጣን እና በሰነደ ሙዓለነዋይ ማስቀመጫና ማስተላለፊያ (CSD) መመሪያ መሠረት ሕጋዊ የሰነድ ማረጋገጫና ዝውውር መፈጸም ይኖርበታል።

የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለነዋይ መለዋወጫ (ESX) የራሱ የሆነ የንግድ ሰዓት ይኖረዋል። ግብይቶች የሚፈጸሙት በሥራ ቀናት (ከሰኞ እስከ ዓርብ) በልውውጡ መድረክ ክፍት የሥራ ሰዓታት ውስጥ ብቻ ይሆናል። ቅዳሜ፣ እሁድ እና በበዓላት ቀናት ግብይት አይኖርም።

የባለሀብቶች ጥያቄ

ጥያቄዎን ለማስገባት እባክዎ ከታች ያሉትን መስኮች ይሙሉ።

0/35
0/16
0/200
Thank
You

Reach us via our Investor Relations Portal, call our dedicated line at 128