ለግለሰብ ያልተገደበ ባለገመድ ብሮድባንድ ኢንተርኔት /ኤዲኤስኤል/ አገልግሎት ተጠቃሚዎች በሙሉ!

ቀደም ሲል ሲጠቀሙበት የነበረው የባለ 256 ኪሎ ቢትስ በሰከንድ ፍጥነት ያልተገደበ የባለገመድ ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ያለምንም ተጨማሪ ወርሃዊ ክፍያ ወደ 512 ኪሎ ቢትስ በሰከንድ ፍጥነት ያደገልዎ መሆኑን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው፡፡

ምን ይሄ ብቻ!

በቅርቡ በተደረገው የ50% ኢንተርኔት አገልግሎት የታሪፍ ቅናሽ መሰረት አሁን እየተጠቀሙበት ካለው ፍጥነት ወደ ተሻለ ፍጥነት ማለትም ከ512 ኪሎ ቢትስ በሰከንድ ወደ 1 ሜጋ ቢትስ በሰከንድ ፣ ከ1 ሜጋ ቢትስ በሰከንድ ወደ 2 ሜጋ ቢትስ በሰከንድ እንዲሁም ከ2 ሜጋ ቢትስ በሰከንድ ወደ 4 ሜጋ ቢትስ በሰከንድ ማሳደግ ከፈለጉ ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ፡፡