ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ሰነዱ መሸጥ የሚጀምርበት ቀን: ሰኔ11,2011ዓ.ም 

ጨረታው የሚዘጋበት ቀን : ሐምሌ 08 ቀን 2011 ዓ.ም

መስፈርቶች

ኢትዮ ቴሌኮም ያገለገሉ ተሸከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
1. ስለ አሻሻጡ የሚገልፅ ዝርዝር የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዱን ተጫራቾች ከሰኔ11 እስከ ሐምሌ 08 ቀን 2011ዓ.ም ከቀኑ 06፡00 ድረስ በኢትዮ ቴሌኮም አቃቂ ዕቃ ግምጃ ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 ከፍለው በመውሰድ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
2. ተሸከርካሪዎችን ለማየት ለሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የገዙበትን ደረሰኝ በመያዝ አቃቂ ዕቃ ግምጃ ቤት በመገኘት ከሰኔ11 እስከ ሐምሌ 08 ቀን 2011 ዓ.ም እስከ ቀኑ 06፡00 ሰዓት ድረስ ማየት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ውጤቱ እንደታወቀ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለመግዛት የሚያቀርቡበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር ከመቶ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቀ ባንክ ተረጋግጦ በሚቀርብ ሲፒኦ (CPO) መሆን አለበት፡፡
4. ተሸከርካሪዎቹን የሚገዙበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በሚቀመጠዉ ማቅረቢያ ቅጽ/ ፎርም መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
5. ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት አቃቂ ዕቃ ግምጃ ቤት ሐምሌ 09 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 05፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡

የጨረታውን ዝርዝር መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

                      ኢትዮ ቴሌኮም