ፎቶ ኮፒ ወረቀት 80 ግራም እና ጥቁርና ሰማያዊ እስክርቢቶ ለመግዛት የወጣ ግልፅ ጨረታ

ጨረታው የሚጀምርበት ቀንና ሠዓት፡ ህዳር 13 2011 ዓ.ም 02፡30

የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሠዓት፡ ታህሳስ 12 2011 ዓ.ም 11፡00

ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሠዓት፡ ታህሳስ 13 2011 ዓ.ም 04፡00

የጨረታ ቁጥር-3651496

የኢትዮ ቴሌኮም ሰ/ምዕ/ሪጅን ፎቶ ኮፒ ወረቀት 80 ግራም እና ጥቁርና ሰማያዊ እስክርቢበግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ እና ብቁ የሆኑ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከህዳር 13 ቀን 2011 . እስከ ታህሳስ 12 ቀን 2011 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ) የኢትዮ ቴሌኮም ሰ/ምዕ/ሪጅን ቢሮ 1ኛ ፎቅ ቁጥር 108 የማይመለስ ብር 30 በመክፈል ሰነዱን መግዛትና መወዳደር ይችላሉ፡፡

 1. ተጫራቾች የበለጠ መረጃ ማግኘት ከፈለጉ የኢትዮ ቴሌኮም ሰ/ምዕ/ሪጅን 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 (ባህር ዳር) በአካል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
 2. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያለው ተጫራች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅበታል
 • የዘመኑ የታደሰ እና አግባብነት ያለው ንግድ ስራ ፈቃድ
 • የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት
 • የጨረታው መልስ ሰነድ በወኪል የተፈረመ ከሆነ ከድርጅቱ/ውልና ማስረጃ/ የተወከለበት ደብዳቤ ያለው
 • የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Original Bid Security) ብር 20,000
 • የተጫራቹ የማቋቋሚያ ሰነድ (Legal Establishment Document)- (በሽሙር ለተመሰረቱ ድርጅቶች ብቻ)
 1. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው በተጫራቹ ምርጫ መሰረት ከሚከተሉት በአንዱ ዓይነት ሊሆን ይችላል፡፡

ሀ/ በሐገር ውስጥ በታወቀ ባንክ በተመሰከረለት ቼክ /በሲፒኦ/

ለ/ በሐገር ውስጥ በታወቀ ባንክ በተረጋገጠ የቦንድ (Bank Guarantee)

 • በቁጥር 3 (ለ) መሰረት ዋስትና የሚሰጥ ባንክ ከኢትዮ ቴሌኮም በጽሑፍ የመጀመሪያ የክፍያ ጥያቄ እንደቀረበለት ወዲያውኑ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለመክፈል ዋስትና ይገባል፡፡ ከኢትዮ ቴሌኮም የሚቀርበው የክፍያ ጥያቄ በማንኛውም ሁኔታ ቢሆን ምንም ዓይነት ቅደመ ሁኔታ አይቀርብበትም፡፡
 • ቦንድ ሰጭው ባንክ ከላይ በተራ ቁጥር 3.1 የተገለፀውን ይዘት(ቃል) በሚሰጠው ቦንድ ላይ በግልፅ ማካተት አለበት፡፡
 1. ፖስታዎቹ ከታሸጉ በኋላ ፎቶ ኮፒ ወረቀት 80 ግራም እና ጥቁርና ሰማያዊ እስክርቢቶ አቅርቦት ጨረታ የሚል ጽሑፍ በማስፈር ለገዥው በሚከተለው አድራሻ መላክ አለባቸው፡-

ኢትዮ ቴሌኮም

ሰ/ምዕ/ሪጅን

ባህር ዳር

ሶርሲንግ እና ሳፕላይ ቸይን

1ኛ ፎቅ ክፍል ቁጥር 108

ስልክ +251582200049

ፖ.ሣ.ቁ 01 ባህር ዳር ኢትዮጵያ