ረጅም የቆይታ ጊዜ የሞባይል ጥቅል

ለሩብ ዓመት ወይም ዓመታዊ  የሞባይል ጥቅል ይመዝገቡ! በቅናሹም ይደሰቱ!

የሩብ ዓመት ጥቅል

ብር 650
  • 555 ደቂቃ + 150 መልዕክት + 12 ጊ.ባ ዳታ

የሩብ ዓመት ጥቅል

ብር 860
  • 1500 ደቂቃ + 150 መልዕክት + 12 ጊ.ባ ዳታ

የሩብ ዓመት ያልተገደበ ጥቅል

ብር 2620
  • 555 ደቂቃ +150 መልዕክት + ያልተገደበ ዳታ

የሩብ ዓመት ያልተገደበ ጥቅል

ብር 5,205
  • ያልተገደበ ድምፅ + 150 መልዕክት + 12 ጊ.ባ ዳታ

የሩብ ዓመት ያልተገደበ ጥቅል

ብር 6,872
  • ያልተገደበ ድምፅ + ያልተገደበ ዳታ

የአንድ ዓመት ያልተገደበ ጥቅል

ብር 18,324
  • ያልተገደበ ድምፅ + ያልተገደበ ዳታ + አጭር የፅሁፍ መልዕክት

የአንድ ዓመት ያልተገደበ ጥቅል

ብር 10,872
  • ያልተገደበ ድምፅ + ያልተገደበ አጭር የፅሁፍ መልዕክት

የአንድ ዓመት ያልተገደበ ጥቅል

ብር 10,872
  • ያልተገደበ ዳታ + ያልተገደበ አጭር የፅሁፍ መልዕክት

  • ሁሉም የቅድመ ክፍያ ሞባይል፣ የድህረ ክፍያ ሞባይል እና የሀይብሪድ ሞባይል አገልግሎት ደንበኞች የረጅም የቆይታ ጊዜ ሞባይል ጥቅል በማንኛውም ሰዓት መመዝገብና አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
  • ለረጅም የቆይታ ጊዜ ጥቅል ሲመዘገቡ የመረጡትን ጥቅል ዋጋ አንድ ጊዜ ብቻ የሚከፍሉ ይሆናል፡፡
  • ለሩብ ዓመት ወይም ለ 90 ተከታታይ ቀናት ፕላን በሽያጭ ማዕከላችን ለሚመዘገቡ ደንበኞች ሁለት ዓይነት የጥቅል መልቀቂያ አማራጮች ያሉ ሲሆን
    • ሁሉም የጥቅል አገልግሎቶቹ በአንድ ጊዜ እስከ አገልግሎት ማብቂያ ድረስ የሚለቀቁ ሲሆን ሌላኛው ደሞ
    • የተጠቀሱትን የጥቅል አገልግሎቶች የአገልግሎት ቀነ ገደቡ እስኪያልቅ ድረስ በየወሩ ከፋፍሎ የሚቀርብ ሲሆን ያልተጠቀሙት ቀሪ ጥቅል ካለ ወደ ቀጣይ ወር የሚተላለፍ ይሆናል፡፡
  • የቅድመ ክፍያ ሞባይል ተጠቃሚዎች በአጭር ቁጥር *999#፣ በማይ ኢትዮቴል መተግበሪያ እና የሽያጭ ማዕከላችን በመቅረብ መመዝገብ ይችላሉ፡፡ የድህረ ክፍያ ሞባይል ተጠቃሚዎች አገልግሎቱን በሽያጭ ማዕከሎቻችን በአካል በመቅረብ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  • የግለሰብም ሆነ የድርጅት ደንበኞች የረጅም የቆይታ ጊዜ ሞባይል ጥቅል አገልግሎት መመዝገብ ይችላሉ፡፡
  • ደንበኞች የረጅም ጊዜ ጥቅልን ለራሳቸው መግዛት ወይም ለወዳጅ ዘመዶቻቸው በስጦታ መላክ ይችላሉ
  • አንዴ ለረጅም የቆይታ ጊዜ ጥቅል ከተመዘገቡ ተመላሽ ሂሳብ መጠየቅ ወይም ወደ ሌላ የረጅም የቆይታ ጊዜ ጥቅል አማራጭ መቀየር አይፈቀድም፡፡
  • ለረጅም የቆይታ ጊዜ የሞባይል ጥቅል ለመመዝገብ እየተጠቀሙበት ያለው ሲም ካርድ የሚሠራ መሆን አለበት፡፡
  • የሞባይል ድምጽ እና የአጭር ጽሁፍ ጥቅሉ ለሀገር ውስጥ የጥሪና መልዕክት አገልግሎት ብቻ የሚውል ይሆናል፡፡
  • ከገዙት ጥቅል ውጭ እንዲሁም አጭር ቁጥር ሲጠቀሙ መደበኛው የአገልገሎት ታሪፍ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
  • ሁሉም ዋጋዎች የተጫማሪ እሴት ታክስን ያካትታሉ፡፡