የLTE Advanced የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት በምስራቅ ምስራቅ ሪጅን ከተሞች ማስጀመራችንን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው፡፡ 

በምስራቅ ምስራቅ ሪጅን ውስጥ በሚገኙ ሰባት ከተሞች ማለትም በጅግጅጋ፣ ጎዴ፣ ፊቅ፣ ደገሃቡር፣ ቀብሪበያህ፣ ዋርዴር እና ቀብሪደሃር የLTE Advanced አገልግሎቱን ማስጀመር ተችሏል፡፡ በተጨማሪም በሪጅኑ የኔትወርክ ሽፋንና አቅም ለማሳደግ የሚያስችል የኔትወርክ ማስፋፊያ ፕሮጀክት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

የLTE Advanced አገልግሎት ከፍተኛ ፍጥነትና ባንድዊድዝ እንዲሁም አስተማማኝ የዳታ አገልግሎት የሚሰጥ እንደመሆኑ ደንበኞቻችን አገልግሎታቸውን ዲጂታይዝ ለማድረግ፣ ምርታማነትን ለማሳደግ እና በአጠቃላይ የቴሌኮም አገልግሎት ላይ ያላቸውን ተሞክሮ በከፍተኛ ሁኔታ የሚያሳድግ ነው፡፡

በኩባንያችን የሦስት ዓመት የእድገት ስትራቴጂ ላይ እንዳመላከትነው በአዲስ አበባና በሁሉም ክልሎች የዳታ ትራፊክ እድገትና ፍላጎትን መሠረት ያደረገ የ4G/LTE አገልግሎት የማስፋፊያ ሥራዎችን ለማከናወን ታቅዶ እየተሰራ ሲሆን በዚህም መሠረት በሌሎች የክልል ከተሞች ተመሳሳይ አገልግሎት ለማስጀመር የሚያስችሉ ቅድመ ሥራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

በዚህ አጋጣሚ የቴሌኮም አገልግሎት መጠቀሚያ መሣሪያ (smart phone) እና የይዘት (content) አቅራቢዎች በመረጃ የበለጸገ ማህበረሰብና ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ እንዲሁም አሁን የተዘረጋውን ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የሞባይል ኔትወርክ በስፋት ለመጠቀም የሚያስችሉ ዘመናዊ የሞባይል ቀፎዎችና ይዘቶችን ለህብረተሰቡ በስፋትና በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የበኩላችሁን አስተዋጽዖ እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

Ethio telecom Launches LTE Advanced Services in East East Region

We are pleased to announce the launching of LTE Advanced services in East East Region. The LTE expansion has covered towns: Jigjiga, Gode, Warder, Fik, Kebribeyah, Kebridehar, and Degehabur, where high mobile data traffic has been observed.

Currently, we are also undertaking additional network expansion projects in the region to increase network coverage and capacity. Given the reliability, high bandwidth and high-speed features of LTE Advanced services, we hope that it will enable and empower our customers to digitize their services, increase productivity and improve their experiences. We sincerely appreciate all our stakeholders who have provided the required support to realize the project within short period of time.

As clearly outlined in our three-years growth strategy, data traffic growth and demand based 4G/LTE expansion in Addis and regional towns is among the major strategic initiatives. Accordingly, we will be launching similar services in other parts of the country, for which preparation works are underway.

 

In this regard, we would like to call upon players in the ecosystem to capitalize this opportunity by providing useful contents and affordable handsets and join hands in realizing digital inclusion which paves the way for digital economy.

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives