ኩባንያችን ከፍተኛ የዳታ አጠቃቀም በሚታይባቸው 103 ከተሞች የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎትን ለማስፋፋት የያዘውን ዕቅድ ተከትሎ በዛሬው ዕለት በደቡብ ምዕራብ ሪጅን በሚገኙ ስምንት ከተሞች ማለትም በጅማ፣ አጋሮ፣ በደሌ፣ ቦንጋ፣ ኮይሻ፣ መቱ፣ ሚዛን፣ ማሻ እና ቴፒ የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ የሞባይል ኢንተርኔት ማስፋፊያ ፕሮጀክት አጠናቆ አገልግሎቱን ማስጀመር ችሏል።

የ4ጂ አገልግሎት የላቀ ፍጥነትና ባንድዊድዝ እንዲሁም አስተማማኝ የዳታ አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ ደንበኞቻችን አገልግሎታቸውን ዲጂታይዝ ለማድረግ፣ ምርታማነትን ለማሳደግ እና በአጠቃላይ የቴሌኮም አገልግሎት ላይ ያላቸውን ተሞክሮ በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ ያስችላቸዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም እስካሁን ባደረጋቸው የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት ማስፋፊያ ስራዎች የዛሬውን ጨምሮ በአዲስ አበባ ፣ በደቡብ ምሥራቅ ሪጅን፣ በሰሜን ምዕራብ ሪጅን፣ በምሥራቅ ምሥራቅ ሪጅን፣ በደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን፣ በምስራቅ ሪጅን፣ በማዕከላዊ ምስራቅ ሪጅን ፣ በሰሜን ምስራቅ ሪጅን እና በሰሜን ምሥራቅ ምሥራቅ ሪጅን የሚገኙ 53 ከተሞችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ችሏል። በቀጣይነትም ኩባንያችን በተመሳሳይ ሁኔታ የዳታ ትራፊክ እድገትና ፍላጎትን መሠረት ባደረገ መልኩ በዕቅድ ይዞ እያከናወናቸው ያሉ የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት የማስፋፊያ ሥራዎችን በማጠናቀቅ በተለያዩ የክልል ከተሞች አገልግሎቱን በቅርቡ ለማስጀመር የሚያስችሉ ቅድመ ሥራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል።

በዚህ አጋጣሚ የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት በተስፋፋባቸው ከተሞች የምትገኙ ደንበኞች በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የኩባንያችን የሽያጭ ማዕከል የ3ጂ ሲም ካርዳችሁን ወደ 4ጂ በነፃ በማሳደግ በ4ጂ የሞባይል ቀፎ አማካኝነት እጅግ ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት እንድትጠቀሙ ግብዣችንን እናቀርባለን።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የቴሌኮም አገልግሎት መጠቀሚያ መሣሪያ (smart phone) እና የይዘት (content) አቅራቢዎች በመረጃ የበለፀገ ማህበረሰብና ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ እንዲሁም አሁን የተዘረጋውን ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የሞባይል ኔትወርክ በስፋት ለመጠቀም የሚያስችሉ ዘመናዊ የሞባይል ቀፎዎችና ይዘቶችን ለህብረተሰቡ በስፋትና በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የበኩላችሁን አስተዋጽዖ እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives