ኢትዮ ቴሌኮም በደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ከፍተኛ ፍጥነት ያለው አገልግሎት ጀመረ

የ4G LTE አገልግሎት በደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ከተሞች ማስጀመራችንን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው፡፡ በደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ውስጥ በሚገኙ ስድስት ከተሞች ማለትም በወላይታ ሶዶ፣ በአርባ ምንጭ፣ በሆሳዕና፣ በወልቂጤ፣ በቡታጅራ  እና በጂንካ የአራተኛው ትውልድ የሞባይል ኔትዎርክ /4G LTE/ ማስፋፊያ ፕሮጀከት ተጠናቆ አገልግሎቱን ማስጀመር ተችሏል፡፡

የ4G LTE አገልግሎት ከፍተኛ ፍጥነትና ባንድዊድዝ እንዲሁም አስተማማኝ የዳታ አገልግሎት የሚሰጥ እንደመሆኑ ደንበኞቻችን አገልግሎታቸውን ዲጂታይዝ ለማድረግ፣ ምርታማነትን ለማሳደግ እና በአጠቃላይ የቴሌኮም አገልግሎት ላይ ያላቸውን ተሞክሮ በከፍተኛ ሁኔታ የሚያሳድግ ነው፡፡

በአዲስ አበባና በሁሉም ክልሎች የዳታ ትራፊክ እድገትና ፍላጎትን መሠረት ያደረገ የ4G/LTE አገልግሎት የማስፋፊያ ሥራዎችን ለማከናወን ታቅዶ እየተሰራ ሲሆን በቀጣይ ወራት በሌሎች የክልል ከተሞች ተመሳሳይ አገልግሎት ለማስጀመር የሚያስችሉ ቅድመ ሥራዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡

በዚህ አጋጣሚ የቴሌኮም አገልግሎት መጠቀሚያ መሣሪያ (smart phone) እና የይዘት (content) አቅራቢዎች በመረጃ የበለጸገ ማህበረሰብና ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ እንዲሁም አሁን የተዘረጋውን ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የሞባይል ኔትወርክ በስፋት ለመጠቀም የሚያስችሉ ዘመናዊ የሞባይል ቀፎዎችና ይዘቶችን ለህብረተሰቡ በስፋትና በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የበኩላችሁን አስተዋጽዖ እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

Ethio telecom Launches 4G LTE Service in South South West Region.

We are pleased to announce the launching of 4G LTE Services in South South West Region. The 4G/LTE expansion has covered towns: Wolaita Sodo, Arba Minch, Hosana, Wolkite, Butajira and Jinka, where high mobile data traffic has been observed. Given the reliability, high bandwidth and high-speed features of 4G/LTE services, we hope that it will enable and empower our customers to digitize their services, increase productivity and improve their experiences. We sincerely appreciate all our stakeholders who have provided required support to realize the project within a short period of time.

Data traffic growth and demand based 4G/LTE expansion in Addis and regional towns is among the major strategic initiatives set out in the three years company strategy. Accordingly, over the next few months, we will be launching similar services in other parts of the country, for which preparation works are underway.

In this regard, we would like to call upon players in the ecosystem to capitalize this opportunity by providing useful contents & affordable handsets and join hands in realizing digital inclusion which paves the way for digital economy.

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives