ጨረታ ሰነዱ የሚሸጥበት ቀን ከመጋቢት 2 – 20 ቀን 2ዐ15 ዓ.ም

ጨረታዉ የሚዘጋበት  ቀን መጋቢት 20 ቀን 2ዐ15 ዓ.ም

ጨረታዉ የሚከፈትበት  ቀን መጋቢት 21 ቀን 2ዐ15 ዓ.ም

ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ እና ከአገልግሎት የተመለሱ የተለያዩ የሞይባል እና የመደበኛ የስልክ ቀፎዎች፣ የኮሙኒኬሽን ወረቀቶች፣ የፖወር ዕቃዎች፣ የእንጨት ፖሎች፣ የግንባታ መሣሪያዎች፣ የሥራ መገልገያ የእጅ መሳሪያዎች ፣ኮምፒተሮች፣ ኘሪንተሮች፣ ቶነር ካርቲሌጆች እና ሌሎች የኢንፎርሜሽን ሲስተም እና የኔትወርክ ዕቃዎች፣ የቢሮ ፈርኒቸሮች፣ የቤት ክዳን ቆርቆሮዎች፣ ቁርጥራጭ ካርቶኖች፣ የእንጨት የማሸጊያ ሳጥኖች እና ፖሌቶች፣ የእሳት ማጥፊያዎች፣ የኘላስቲክ ቁርጥራጭና ዳክቶች ፣የበር እና የመስኮት መጋረጃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከመጋቢት 2 ቀን 2ዐ15 ዓ.ም እስከ መጋቢት 2ዐ ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በማንኛውም ጊዜ እና ሰዓት ከ www.extratenders.comwww.2merkato.com እና www.afrotender.com ዌብ ሳይቶች በቴሌ ብር አማካኝነት የማይመለስ አንድ መቶ ብር በመክፈል በቀላሉ መግዛት የምትችሉ ሲሆን  ንብረቶቹን  መመልከት እንዲሁም ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የምትፈልጉ ተጫራቾች አዲስ አበባ በሚገኘው የኩባንያው ዕቃ ግምጃ ቤቶች የታደሰ መታወቂያችሁን በመያዝ መጎብኘት የምትችሉ መሆኑን እነገልፃለን ፡፡

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአቃቂ ዕቃ ግምጃ ቤት መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡

ኩባንያው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives