ኢትዮ ቴሌኮም በተግባር ላይ ያዋለው አዲሱ ኤሌክትሮኒክ የሞባይል አየር ሰዓት መሙያ አገልግሎት የቅድመ ክፍያ እና የጥምር (hybrid) ሞባይል አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች በውጭ ሃገር የሚገኙ ዘመድ ወዳጆቻቸው ወደ ሞባይል ቁጥራቸው የአየር ሰዓት እንዲልኩላቸው የሚያስችል አገልግሎት ነው፡፡
አገልግሎቱ ለተጠቃሚዎች የተዋወቀው በአዲስ ዓመት መግቢያ ሲሆን፤ በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ለሚገኙ ዘመድ ወዳጆቻቸው የሞባይል አየር ሰዓት በመሙላት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክቶችን እንዲለዋወጡም የሚያግዛቸው ይሆናል፡፡
ተጠቃሚዎች ይህን ኤሌክትሮኒክ የአየር ሰዓት መሙላት አገልግሎት በመጠቀም ከ25 ብር ጀምሮ ወደ ሃገር ቤት ለሞባይል ስልክ ተጠቃሚ ወዳጅ ዘመዶቻቸው የአየር ሰዓት መግዛት እና መላክ ያስችላቸዋል፡፡
በተጨማሪም አገልግሎቱ በመላው ዓለም ተደራሽነት ባላቸው ሃገሮች በቀን ሃያ አራት ሰዓት እና የበዓል ቀኖችን ጨምሮ በሁሉም ቀናት የሚስሰጥ በመሆኑ፤ ዜጎች ጊዜ እና ቦታ ሳይገድባቸው የአየር ሰዓት እንዲገዙ እና በስጦታም እንዲልኩ የስችላቸዋል፡፡
ይህ በኤሌክትሮኒክ አየር ሰዓት የመግዛት አገልግሎት ለ2G፣ 3G እና 4G የሞባይል አገልግሎት ዓይነቶች በመቅረቡ፤ ሁሉም የቅድመ ክፍያ እና የጥምር (hybrid) አገልግሎት ሞባይል ደንበኞች ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
ደንበኞች www.senditoo.com እንዲሁም www.worldremit.com በመጠቀም የአየር ሰዓት መግዛት እና ወደ ዘመድ ወዳጆቻቸው መላክ የሚችሉ ሲሆን፤  ሞባይላቸው ላይ ሂሳብ መሞላቱን የሚያረጋግጥ አጭር የጽሑፍ መልእክት ከ994 ይደርሳቸዋል፡፡ መልእክቱ የተገዛውን የአየር ሰዓት መጠን (በብር) እና የሞሉት የገንዘብ መጠን የሚያበቃበትን ቀን (expiry date) የሚያመለክት ይሆናል፡፡
በአሁኑ ወቅት አገልግሎቱ በገበያ ላይ የዋለ ሲሆን፤ ዜጎች ከላይ የተጠቀሱትን አድራሻዎች በመጠቀም የኤሌክትሮኒክ አየር ሰዓት የመሙላት አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives