የጨረታ ማስታወቂያ

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን አዳማ ፣ዱከም፣ ሞጆ፣መተሀራ፣አቦምሳ፣ ወለንጭቲ፣ አሰላ፣ ባቱ እና መቂ የጥበቃ ቤት ግንባታ ስራ RFQ No: 4064674, 4064675 እና 4064673 ቅደም ተከተል ፡፡

በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩና ደረጃቸው GC/BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት በግንባታ ዘርፍ የተሰማራችሁ፣ህጋዊ የታደሠ ፍቃድ ያላችሁና ቢያንስ ሶስት አመት የስራ ልምድ ያላቸዉ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ደረጃ GC/BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆናችሁ ኮንትራክተሮች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 16 ቀን 2013 . ከቀኑ 500 ሰዓት ድረስ አዳማ ከተማ አዋሽ ባንክ ህንጻ 1 ፎቅ ላይ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል በመቅረብ ስለጨረታው መረጃ ማግኘትና የማይመለስ ብር 100.00 (መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሠነድ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

መስፈርት

1. ጨረታው ግንቦት 24 ቀን 2013 . ጀምሮ እስከ ሰኔ 16 ቀን 2013 . ከቀኑ 500 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል፤

2. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የታደሠ የንግድ ፈቃድ፣የተ.. ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል:

3. ተጫራቾች ከዚህ በፊት በግንባታ ዘርፍ የሠሩበትን የስራ ልምድ የጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል:

4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ብር 10,000.00/አስር ሺ/ የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ .. በኢትዮ ቴሌኮም ስም አሠርተው ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል:

5. ተጫራቾች በሰነዶቻቸዉ ላይ ስማቸዉንና ሙሉ አድራሸቸዉን በትክክል ጽፈዉ መፈረም አለባቸዉ፡፡

6. ተጫራቾች የወሰዱትን የጫረታ ሰነድ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ያለዉ ሰነድ ተቀባይነት የለዉም፡፡

7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰኔ 16 ቀን 2013 . ከቀኑ 500 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 800 ሰዓት ይከፈታል:

8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና ሲፒኦ በታሸገ ኢንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ በተዘገጀ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 022-111-0994 / 022-112-1660 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም

ደቡብ ምስራቅ ሪጅን

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives