የመገናኛ እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር የመማርያ ቁሳቁስ ማሟላት ለማይችሉ ልጆች ስጦታ አበረከተ” 

የመገናኛ እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ትኩረት ለሴቶችና ለህፃናት ማህበር ተብሎ በሚታወቀው ግብረ ሠናይ ድርጅት ሥር ለሚታገዙ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ስጦታ አበረከተ፡፡

ስጦታው የተበረከተው ከሃና ማርያም፣ ከአጋዝያን እና ከአብዲቢያ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ 250 ተማሪዎች ሲሆን፣ ስጦታው ለተማሪዎቹ የ2011 ዓ.ም የትምህርት ዘመንን ሙሉ በሙሉ ለመማር በሚያስችላቸው መልኩ የተደረገ መሆኑ በፕሮግራሙ ላይ ተመልክቷል፡፡

ስጦታው በተበረከተበት ሥነ-ስርዓት ላይ የመገናኛ እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ኡባህ መሀመድ ተማሪዎቹ መጪውን የትምህርት ዘመን ከመማርያ ቁሳቁስ ጋር በተገናኘ ምንም ሃሳብ ሳይገባቸው መማር እንዲችሉ በማሰብ ስጦታው መበርከቱን ገልፀዋል፡፡

በዕለቱ ክብርት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ኡባህ መሐመድ እና የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ በትኩረት ለሴቶችና ህፃናት ማህበር የሚደገፉ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ህፃናትንም ጎብኝተዋል፡፡

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives