ኢትዮ ቴሌኮም ምዕራብ ምዕራብ ሪጅን አሶሳ ከተማ ውስጥ ዩኒቨርስቲ አከባቢ ዋና መጋዘን አጥር ለማሰራት ባወጣዉ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ እና ብቁ የሆኑ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል ፡፡

√ የብቁነት መስፈርቶች
አቅራቢዎች አገልግሎት ሰጪዎች ለውድድሩ ብቁ ለመሆን የሚከተሉትን ሰነዶች ማቅረብ አለባቸው
1) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (85,000.00 ብር) ሰማኒያ አምስት ሺህ ብር
2) በ2013 ዓ.ም ላይ በዘርፉ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል
3) የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
4) ለ2013 ከገቢዎች መስርያ ቤት በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር እዳ ነፃ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
5) የግብር ከፋይ ምዝገባ ስርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
6) በአመቱ የታደሰ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል በክልሉ ለተደራጁ ብቻ በፈደራል የተደራጁ ከሆኑ ከሲስተም ፕርንት አድርጎ ማቅረብ የሚችል፡፡
7) የመጫረቻ ሰነድ ላይ ለመፈረም የሚያስችል ሊተርኦፍ አውቶራይዜሽን አታች ስለተደረገ በፊርማ ማረጋገጥ የሚችሉ /ማነጀር CEO/ዳይሬከተር ከሆኑ መሆናቸው የሚገልጽ ዶክመንት ማቅረብ የሚችሉ (Letter of Authorization to sign the bid offers (sample form)
8) ከማንኛውም ክስ ነጻ መሆናቸውን በተያያዘው ቅፅ ላይ በፍርማቸው ማረጋገጥ የሚችሉ (Anti-bribery pledge form/ form is attached)
9) በዓመቱ የታደሰ የብቃት ማረጋጋጫ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
10) የሚያቀርቡት ሰነድ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል የሚል ምልክት በማድረግ ማቅረብ አለባችሁ
11) የማይመለስ 100 ብር በመክፈል በቢሮ ቁጥር 012 የመጫረቻ ሰነድ መውስድ ይቻላል::
12)ጨረታው መጋቢት 6 2013 እስከ መጋቢት 28 ቀን 2013 ዓ/ም ከቀኑ 8፡ 00 ሰዓት ድረስ ባሉት ቀናቶች ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
13)ጨረታው መጋቢት 28 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ኢትዬ ቴለኮም አዲሱ አስፓልት በክልሉ እስታስቲክስ ቢሮ ፊት ለፊት በቢሮ ቁጥር 012 ይከፈታል፡፡

ማሳሰብያ፡-ኢትዮ ቴሌኮም ግልጽ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives