የቢሮ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር – WAAZ/FCW/002/22

ኢትዮ ቴሌኮም ምዕራብ አዲስ አበባ ዞን ጽ/ቤት ሸጎሌ አካባቢ በሚገኘው ህንፃ ላይ የሚገኙ በአጠቃላይ 504.38 ካ.ሜ ስፋት ያላቸውን እንዲሁም አዲሱ ገበያ አካባቢ በሚገኘው ህንጻ ላይ አጠቃላይ 211.26 ካ.ሜ ስፋት ያላቸውን ለቢሮ እና ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎችን ማከራየት በመፈለጉ ለንግድ/ለቢሮ አገልግሎት ለመከራየት ፍላጎት ያላቸውን ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል፡፡


1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ህዳር 6 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ኢትዮ ቴሌኮም ምዕራብ አዲስ አበባ ዞን እንቁላል ፋብሪካ ታደሰ ቸኮል ህንጻ ስምንተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 803 የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በቴሌ ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
2. ተጫራቾች ከላይ ከተጠቀሰው አድራሻ የጨረታ ሰነድ በመግዛት ሸጎሌ እና አዲሱ ገበያ በሚገኘው ህንፃ ላይ የሚከራዩትን ክፍት ክፍሎችን ህዳር 6 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ማየት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የታደሰ እና አግባብነት ያለው የንግድ ስራ ፈቃድ፣የግብር ከፋይ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ (በንግድ ስራ ለተሰማሩ ድርጅቶች ብቻ) እንዲሁም ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ከሆኑ የታደሰ የምዝገባ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በክፍያ ማዘዣ ቼክ /CPO/ ብር 10,000.00 ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
5. ጨረታው ህዳር 27 ቀን 2015 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ተዘግቶ በእለቱ ከጠዋት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
6. ኢትዮ ቴሌኮም የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
7. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-1-265343 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ከሰላምታ ጋር

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives