ኢትዮ ቴሌኮም የአካባቢ ጥበቃ እንቅስቃሴዎች እና የአረንጓዴ አሻራ እንዲቀጥል በማድረጉ ረገድ ያለው ቁርጠኝነት ከፍተኛ ነው። በዚህም መሠረት በ2011 በጀት ዓመት ብቻ ከ17,000 በላይ የኩባንያውን ሠራተኞች በማሳተፍ በመላ አገሪቱ በ174 ጣቢያዎች ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የችግኞች ተከላ ተከናውኗል። እንዲሁም ለሸገር የማስዋብ ፕሮጀክትና ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ እስከ ብሔራዊ ቤተ መንግሥት ለተዘረጋው የመንገድ ዳር ማስጌጫ የሚያገለግል ኃይል ቆጣቢ የመብራት መስመር ዝርጋታ የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል፡፡