የኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አንዱ በሆነው የወንጪ ሃይቅ ገብኝት አካሄዱ::

በኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ የተመራ የኩባንያችን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ቡድን ከገበታ ለሃገር ፕሮጀክት መካከል አንዱ በሆነው የወንጪ ኃይቅ ዛሬ ጥር 21 ቀን 2013 ዓ.ም የመስክ ጉብኝት አካሄዷል፡፡

የጉብኝቱ ዋና ዓላማ ኩባንያው ለፕሮጀክቶቹ መሳካት እያደረገ ካለው የገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ ፕሮጀክቶቹ በሥራ ላይ ሲውሉ የተሟላ የቴሌኮም አገልግሎቶችን እንዲኖራቸው የሚያስችሉ የቴሌኮም መሠረተ ልማት እና የቴክኖሎጂ እገዛዎችን ማድረግ ስለሚቻልበት ሁኔታ ለመምከር መሆኑ ተገልጿል::

ኢትዮ ቴሌኮም ለገበታ ለሃገር ፕሮጀክት የ500,000,000 ብር ድጋፍ ማድረጉ የሚታወቅ ሲሆን ከዚሁ በተጨማሪ ቀደም ሲል ለሸገር ማስዋብ ፕሮጀክት በገንዘብ እና በአይነት ድጋፍ እንዲሁም በአገር ውስጥ እና ከአገር ውጪ የሚገኙ ዜጎች ለፕሮጀክቱ በቀላሉ ገንዘብ በመላክ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ሁኔታዎችን በማመቻቸት አሻራውን በጉልህ አስቀምጧል፡፡

Ethio telecom’s Higher Management Pay a Visit to Wonchi- one of the Dine for Ethiopia Project.

A delegation of Ethio telecom’s higher management members led by the CEO, Miss Frehiwot Tamru, today visited lake Wonchi –which is one among the three Dine for Ethiopia projects launched by Prime Minister Abiy Ahmed(Dr.).

The aim of the visit was to discuss on telecom infrastructure & technological requirements for the project, which enables the company to provide advanced & reliable telecom services for the project.

Meanwhile, Ethio telecom has contributed 500,000,000 ETB to the Dine for Ethiopia Projects (Koysha, Gorgora & Lake Wonchi); it is also remembered that our company has supported in cash and in kind for the “Beautifying Sheger” project.

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives