ኢትዮ ቴሌኮም ለኩባንያው አገልግሎት የማይሰጡ አዳዲስ እና ከአገልግሎት የተመለሱ ልዩ ልዩ የከባድ እና ቀላል መኪና መለዋወጫዎችን፣ የስልክ ቀፎዎችን፣ የጽሕፈት መሣሪያዎችን፣ የተለያዩ የስራ መገልገያ መሳሪያዎችን፣ የተለያዩ የኢንፎርሜሽን ሲስተም፣ የፋን፣ የፓወር እና የኔትወርክ ዕቃዎችን፣ ልዩ ልዩ የእንጨት እና የኮንክሪት ፖሎችን፣ የብረት እና የኘላስቲክ በርሚሎችን፣ እንዲሁም ቁርጥራጭ እና ከአገልግሎት የተመለሱ፡- ብረታ ብረቶችንና አሎሙኒየሞችን፣ የተለያዬ የማሸጊያ ጣውላዎችና ሳጥኖችን፣ የእንጨት ፖሌቶችን፣ ንቃይ የበርና የመስኮት እንጨቶችን፣ የአጠና እንጨቶችን፣ የኔትዎርክ ገመዶችን፣ የኤች.ዲ.ፒ ዳክቶችና የኘላስቲክ ነክ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የኔትዎርክ ካርዶችን፣ የህዝብ ስልክ ቆፎዎችን፣የሶላር ፖኔሎችን፣ የተለያዩ የመሽ እና ሌሎች ሽቦዎችን፣ ካዝናዎችን፣ የተለያዩ የመኪና ጐማዎችን፣ የተሰባበሩ የስልክ ቆፎዎችን፣የፍሎረሰንት አምፖል ማቀፊያዎችን፣ የቤት ክዳን ቆርቆሮዎችን፣ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ከመስከረም 23 እስከ ጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ.ም ከሰዓት ቦኃላ 11:00 ድረስ በማንኛውም ጊዜ እና ሰዓት በቴሌብር የማይመለስ አንድ መቶ ብር በመክፈል ከ www.afrotender.comwww.2merkato.com እና www.extratenders.com ዌብሳይቶች  መግዛት የሚችሉ ሲሆን ንብረቶቹን ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች የታደሰ መታወቂያ በመያዝ መስቀል ፍላወር እና አቃቂ በሚገኙት የኩባንያው ዕቃ ግምጃ ቤቶች ማየት ይችላሉ፡፡

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአቃቂ ዕቃ ግምጃ ቤት ጥቅምት 16 ቀን 2015 ዓ.ም ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡

ተጨማሪ መረጃ አቃቂ ከሚገኘው የኢትዮ ቴሌኮም ዕቃ ግምጃ ቤት ቢሮ ቁጥር 001 በአካል በመቅረብ ማግኘት ይቻላል ፡፡

ኩባንያው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives