ከግንቦት 03 ቀን 2014 ዓ.ም

የጨረታ ቁጥር 02/2014

ከአገልግሎት የተመለሱ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፤ ያገለገሉ የእንጨት ምሰሶዎች፤ የተለያዩ ፕላስቲኮች ፤ ቁርጥራጭ ኑፕሪን ገመዶች፡ ያገለገሉ ባትሪዎች፤ አሮጌ ካዝናዎች፤ ያገለገሉ ወንበሮች እና ሌሎች የመሳሰሉትን ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ ለሕጋዊ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ጨረታው የሚቆይበት ከግንቦት 03 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 29 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ይሆናል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ወቅት የዘመኑ ግብር የከፈሉበትን የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣የታደሰ መታወቂያ ወይም ማንነታቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ዋናውንና ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል::

1. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ከግንቦት 03 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ግንቦት 29 ቀን 2014 ዓ.ም ከሰኞ እስከ ዓርብ በሥራ ሰዓት ከሰ/ምስ/ሪጅን ፒያሳ ሁዳ ሪል ስቴት ቢሮ ቁጥር 201 የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በቴሌ ብር ወይም በጥሬ ገንዘብ ገቢ በማድረግ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡

2. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ውጤቱ እንደታወቀ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ለተጠቀሱት ለኩባኒያዉ ዕቃዎች የሚያቀርቡበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት ከመቶ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

3. የጨረታ ማስከበሪያው ዋስትና ከታወቀ ባንክ ተረጋግጦ በሚቀርብ ሲፒኦ(CPO) መሆን አለበት፡፡

4. ተጫራቾች ለሽያጭ የቀረቡትን እቃዎች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ እና የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ግንቦት 03 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ግንቦት 29 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ ደሴ ካራጉቱ ወይም ኮምቦልቻ ምሰሶ መቀቀያ በሚገኘው የድርጅቱ ዕቃ ግምጃ ቤት በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቾች የተጠቀሱትን ከኩባኒያዉ አገልግሎት የተመለሱ ዕቃዎችን የሚገዙበትን ዋጋ ቫትን (VAT) ጨምረው በዋጋ ማቅረቢያ ቦታው ላይ በማካተት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውን እና የጨረታውን ቁጥር በመጥቀስ በኢትዮ ቴሌኮም ሰ/ምስ/ሪጅን ፒያሳ ሁዳ ሪል ስቴት ቢሮ ቁጥር 201 2ኛ ፎቅ ግንቦት 29 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል::

6. ጨረታው ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮ ቴሌኮም ሰ/ምስ/ሪጅን ደሴ ፒያሳ ሁዳ ሪል ስቴት ቢሮ ቁጥር 201 2ኛ ፎቅ ግንቦት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል ፡፡ሆኖም በመክፈቻው ቀንና ቦታ ተጫራቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ካልተገኙ እንደተገኙ ተቆጥሮ በተገኙት ተጫራቾች ፊት ያቀረቡት ሠነዶች ይከፈታሉ፡፡

7. ተጫራቾች በጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

8. ኢትዮ ቴሌኮም የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

9. ለተጨማሪ መረጃ ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል አጠገብ ስ/ምስ/ሪጅን በሚገኘው ወይም በኢትዮ ቴሌኮም ሰ/ምስ/ሪጅን ደሴ ፒያሳ ሁዳ ሪል ስቴት ቢሮ ቁጥር 201 2ኛ ፎቅ ሥራ አስኪያጅ ቢሮ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር፡ 0911 51 23 81 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል ፡፡

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives