የጨረታ መጀመሪያ ቀን: መጋቢት 23 ቀን 2012 ዓ.ም.
የጨረታ መዝጊያ ቀን: ሚያዚያ 23 ቀን 2012 ዓ.ም.

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ደ/ምዕ/አ/አ/ዞን 01/2012 ዓ.ም.
ኢትዮ ቴሌኮም የተለያዩ ያገለገሉ ወረቀቶች፣ካርቶን፤ደረሰኞች እና ፎርሞች ባሉበት ሁኔታ ለሕጋዊ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ ከመጋቢት 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ጠዋት 4፡30 ሰዓት ድረስ ይሆናል፡፡
1/ ስለ አሻሻጡ ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ከመጋቢት 23 ቀን 2012 ዓ.ም. እስከ ሚያዚያ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ጠዋት 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ከደ/ምዕ/አ/አ/ዞን ኦልድ ኤርፖርት ካርል አደባባይ ቢሮ ቁጥር 209 የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
2/ የተለያዩ ያገለገሉ ወረቀቶች፣ካርቶን፤ደረሰኞች እና ፎርሞችን ለማየት ለሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የገዙበትን ደረሰኝና መታወቂያ በመያዝ አየርጤና ጅማ በር አካባቢ በሚገኘው የኢትዮ ቴሌኮም እቃ ግ/ቤት በመገኘት ከመጋቢት 23 ቀን 2012 ዓ.ም. እስከ ሚያዚያ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ዘወትር በስራ ሰዓት መመልከት ይቻላል፡፡
3/ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የተለያዩ ያገለገሉ ወረቀቶች፣ካርቶን፤ደረሰኞች እና ፎርሞችን ለመግዛት የሚያቀርቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት ከመቶ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታ ማስከበሪያው ከታወቀ ባንክ ተረጋግጦ በሚቀርብ ሲፒኦ (CPO) መሆን ይኖርበታል፡፡
4/ ተጫራቾች የተለያዩ ያገለገሉ ወረቀቶች፣ካርቶን፤ደረሰኞች እና ፎርሞችን የሚገዙበትን ዋጋ በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ/ፎርም መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን የተለያዩ ያገለገሉ ወረቀቶች፣ካርቶን፤ደረሰኞች እና ፎርሞችን የሚያሳይ የዋጋ ማስገቢያ ቅጽ/ፎርም፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ኮፒ፣የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ (CPO) ፣ የተጫራቾች አድራሻ መግለጫን በማካተት በታሸገ ኤንቨሎ ሙሉ አድራሻውንና የጨረታውን ቁጥር በመጥቀሰ በኢትዮ ቴሌኮም ደ/ምዕ/አ/አ/ዞን ኦልድ ኤርፖርት ካርል አደባባይ ቢሮ ቁጥር 209 ከመጋቢት 23 ቀን 2012 ዓ.ም. እስከ ሚያዚያ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት የሚጠበቅ ሲሆን ከዚህ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርብ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም::
5/ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ምዕ/አ/አ/ዞን ኦልድ ኤርፖርት ካርል አደባባይ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 209 ሚያዚያ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives