ኢትዮ ቴሌኮም በመላው ሀገሪቱ በ45 ዩኒቨርስቲዎች የሚማሩ 4000 ተማሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የ16 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ መርሐ ግብር ይፋ አደረገ

ኢትዮ ቴሌኮም በዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች የድጋፍ መርሐ ግብርን በ2006 ዓ.ም የጀመረ ሲሆን የተጠቃሚዎችም ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በ2011 በጀት ዓመት መጨረሻ በ13 ዩኒቨርስቲዎች ለ840 ተማሪዎች ድጋፍ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን ይህ ድጋፍ የሚኖረውን ጠቀሜታ ታሳቢ በማድረግ  በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ 45 ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚማሩ አራት ሺህ (4000) ተማሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የድጋፍ መርሐ ግብር አዘጋጅቶ ጥሪ የተደረገላቸው የመንግሥት ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንቶች፣ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ታኅሣሥ 21 ቀን 2012 ዓ.ም  ይፋ አድርጓል፡፡ ለዚህም ፕሮጀክት የሚውል በዓመት ብር 16 ሚሊዮን ብር መድቧል፡፡

­­­­­­­­­­­­­­ኩባንያችን ማኅበራዊ ኃላፊነቱን (Corporate Social Responsibility) ለመወጣት ትኩረት ሰጥቶ እየሠራባቸው ከሚገኙ ጉዳዮች መካከል የትምህርት ዘርፍ አንዱ ሲሆን ከዚህም ውስጥ በመንግሥት ዪኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ለሚገኙና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች ወርኃዊ የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል፡፡

በትምህርት ዘርፍ በተለያዩ አካባቢዎች ድጋፍ ለሚሹ ከአሥራ አራት ሺህ በላይ ተማሪዎች የምገባ፣ የትምህርት ቁሳቁስና የኪስ ገንዘብ ድጋፍ እንዲሁም በያዝነው 2012 በጀት ዓመት በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ 93 ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ 32,974 ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው የአንድ ደርዘን ደብተር ድጋፍ እንዲሁም ከአምስት ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የዩኒፎርምና ቦርሳ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ከዚሁ በተጨማሪ ኩባንያንችን ሴቶች በኢኮኖሚው መስክ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ ከአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች ለተውጣጡ አንድ መቶ ሴቶች የፋሽን ዲዛይን ሥልጠና እንዲወስዱ ሙሉ ወጪውን በመሸፈን ድጋፍ አድርጓል፡፡ የሥልጠና ዕድሉ የተመቻቸው ሴቶች በትምህርት፣ በሥራ እንዲሁም በአጠቃላይ የኢኮኖሚ መስኮች ያለባቸውን ተጽእኖ ከግምት በማስገባት ሴቶችን ማስተማር እና በኢኮኖሚ በማብቃት ራሳቸውን እንዲችሉና ልጆቻቸውን ማስተማር እንዲችሉ እገዛ ለማድረግ ነው፡፡

ኩባንያችን በተለይ ከ2011 በጀት ዓመት ጀምሮ በተደራጀ መልኩ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ለዋና ሥራ አስፈጻሚ ተጠሪ የሆነ የሥራ ክፍል በማደራጀት ማኅበረሰባችን ድጋፍ የሚሻባቸውን የትኩረት መስኮች በመለየት የማኅበራዊ  ኃላፊነት ሥራዎችን አጠናክሮ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡

በዚህም ረገድ:-

  • በሰብዓዊ እና ማኅበረሰብ አቀፍ ድጋፎች ለሴቶች፣ ለአረጋውያን፣ ለሕፃናት፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለጎዳና ተዳዳሪዎች እና ለመሳሰሉት የማኅበረሰብ ክፍሎች ድጋፍ አድርጓል፡፡
  • በአረንጓዴ ልማትና በአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ “በአረንጓዴ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት” አማካኝነት በመላ ሀገሪቱ ከ17 ሺ በላይ ሠራተኞችን በማሳተፍ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ተክሎ እንክብካቤ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
  • ኩባንያችን ሸገርን ለማስዋብ ፕሮጀክት ካደረገው የገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ እስከ ብሔራዊ ቤተመንግሥት የመንገድ ላይ መብራቶች ድጋፍ በማድረግ አዲስ አበባ ከተማችን ውብና ጽዱ ለማድረግ የበኩሉን አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህም ጋር በተያያዘ ተቋማችን ሌሎች የሀገራችን ከተሞች ጽዱና አረንጓዴ አካባቢን ለመፍጠር የሚያደርጉትን ጥረት በመደገፍ ላይ ይገኛል፡፡ ለወደፊትም ይህንኑ አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
  • በተጨማሪም ለሌሎች የመንግሥት ፕሮጀክቶችም በሄልዝ ኔት፣ በወረዳ ኔትና በስኩል ኔት ፕሮጀክቶች አማካኝነት ድጋፉን እያደረገ ይገኛል፡

ማኅበራዊ ኃላፊነትን የመወጣት ባህል በኩባንያችን ብቻ ሳይወሰን በሠራተኞቻችንም በበጎ ፈቃደኝነት የሚሠራ ሲሆን በዚህም ረገድ በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ሠራተኞቻችን በየአካባቢያቸው በጤና፣ በሰብዓዊነት፣ በትምህርት፣ በአካባቢ ጥበቃ እና በመሳሰሉት ዘርፎች ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡

በዩኒቨርሲቲ እንዱስትሪ ትስስር፣ በተመራቂ ተማሪዎች የኤክስተርንሺፕ እና በተለያዩ ዩኒቨርሲቲ መምህራን የጥናት ፕሮጀክቶች ላይ ኩባንያችን በሀገራችን ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር እንደሚሠራ ይታወቃል፡፡ በቀጠይም ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በቅንጅት ማኅበረሰቡን የሚጠቅሙ ፕሮጀክቶች ላይ በመሳተፍ የሀገራችን ዜጎች ከሁለቱ ተቋማት የሚጠቀሙበትን ሁኔታዎች በጋራ ያመቻቻል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም

ታኅሣሥ 21 ቀን 2012 ዓ.ም

Ethio telecom Launches Financial Aid Program of 16 million Ethiopian Birr for 4 Thousand Students in 45 Public Universities  

Ethio telecom launched the expansion of an aid package that would benefit four thousand university students in 45 universities across the country. The company made public this aid expansion program on an event attended by university presidents, high government officials and other invited stakeholders on the 31st of December 2019.

This aid package, which includes providing a monthly stipend to public university students who need support, is also an extension of the company’s support program that benefited 840 students from 13 universities since 2006 E.C. This is part of Ethio telecom’s rigorous corporate social responsibility programs.

At the beginning of this Ethiopian budget year, our company provided a dozen of notebooks to each of 32,974 students from 93 schools across the country. This is in addition to school uniforms and bags offered to more than five thousand students during the same period.

Furthermore, the company has sponsored a six-month fashion design training to 100 women drawn from the sub-cities of Addis Ababa to economically empower women and enable them to support themselves and their families.

Since the previous Ethiopian fiscal year, the company has extended its corporate social responsibility areas via its newly established CSR Department through which it made the undermentioned accomplishments:

  • Provided support to women, the elderly, children, the disabled, street children and others in the community,
  • Planted more than 1.5 million seedlings in 174 areas through all regions of the company where 17,000 employees took part to support the Green Ethiopia project initiative,
  • Contributed to the outdoor strip decoration light project, apart from the financial support given to Sheger Beautification Project and
  • Played vital roles in the extension of health net, woredanet, and schoolnet projects.

Ethio telecom

31 December 2019

Addis Ababa, Ethiopia

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives