ኢትዮ ቴሌኮም በመላው ሃገሪቱ ያሉ የኩባንያው ቤተሰቦች የሚሳተፉበት “የአረንጓዴ አሻራ” የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር አስጀመረ
ኢትዮ ቴሌኮም በመላ ሃገሪቱ ያሉ የኩባንያው ቤተሰቦች የሚሳተፉበት “የአረንጓዴ አሻራ” የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር በዛሬው ዕለት በሀዋሳ ከተማ ያስጀመረ ሲሆን በስድስት የኩባንያው ዞኖችና አስራ ሰባት ሪጅኖች የሚሳተፉበት መርሐ-ግብር ላይ አንድ ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል ዕቅድ ተይዞ እንቅስቃሴው በይፋ ተጀምሯል፡፡