የተሻለ ጥራት ያለው የሞባይል አገልግሎት ለማግኘት እባክዎን የሞባይል ስልክዎን ኔትወርክ ምርጫ 3G/2G ወይም WCDMA/GSM (Auto connect) ላይ ያድርጉ

ኢትዮ ቴሌኮም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሞባይል አገልግሎት ላይ አልፎ አልፎ እየተስተዋለ የሚገኘውን የኔትወርክ መጨናነቅ ችግር ለመፍታት የሚያስችለውን ፕሮጀክት ቀርፆ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን የሞባይል ስልክ ኔትወርክ ምርጫዎን 3G/2G ወይም WCDMA/GSM (Auto connect) ላይ በማድረግ የተሻለ ጥራት ያለው የሞባይል አገልግሎት ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የሞባይል ቀፎዎ ላይ የሚገኘውን የኔትወርክ ምርጫ ለማስተካከል የሚከተለውን ሂደት ይከተሉ፡፡
Setting ⇒ More network ⇒ Mobile or Cellular Networks ⇒ Network Mode 3G/2G or WCDMA/GSM (Auto connect)
የሚለውን ይምረጡ፡፡