የጨረታ ማስታወቂያ

ኢትዮ ቴሌኮም የተለያዩ ዓይነት ሴራሚኮችን በጨረታ ቁጥር 3653377-2 የሴራሚክ አቅራቢዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎቱ ያላቸውና በመስኩ የተሰማሩ ድርጅቶች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ሰዓት ከኢትዮ ቴሌኮም ዋናው መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 201 ማግኘት ይችላሉ፡፡
ጨረታው ግንቦት 19፣ 2011 ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 10 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ ማንኛውም ተጫራች እስከ ሰኔ 10 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዱን በኢትዮ ቴሌኮም ዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 211ቢ ማስገባት ይኖርበታል፡፡ ጨረታው ፍላጎቱ ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰኔ 11 ቀን 2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በዋናው መስሪያቤት ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 210 ይከፈታል::
ለበለጠ መረጃ በኢትዮ ቴሌኮም ድረ ገጽ www.ethiotelecom.et ላይ የታተመውን ዝርዝር ማስታወቂያ መመልከት ይቻላል፡፡በተጨማሪም በኢትዮ ቴሌኮም ዋናው መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 201 ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት በአካል በመገኘት ወይንም በኢሜል አድራሻ mintesenot.tezera@ethiotelecom.et በመጠየቅ ስለ ጨረታውን ዝርዝር መረጃ መውሰድ ይችላሉ፡፡

 

ኢትዮ ቴሌኮም