የኢትዮ ቴሌኮም የ2012 በጀት ዓመት የመጀመሪያ መንፈቅ የሥራ አፈጻጸም ማጠቃለያ ሪፖርት

ይህ ሪፖርት ከሐምሌ 2011 እስከ ታህሳስ 2012 ያለውን የኢትዮ ቴሌኮም የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም የሚገልጽ ነው፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ላይ ለህዝብ ይፋ ያደረገውን የሦስት ዓመት ስትራቴጂና የ2012 በጀት ዓመት እቅድ ተከትሎ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ሰፊ የለውጥና የኦፕሬሽን ሥራዎች እያከናወነ ሲሆን በዋናነትም በስትራቴጂው ላይ የተመለከቱ ስድስት ዋና ዋና የትኩረት መስኮችን ለመተግበር ሰፊ...

ጋዜጣዊ መግለጫ | Press Release

ኢትዮ ቴሌኮም ከተለያዩ የባለድርሻ አካላት ጋር በቴሌኮም መሠረተ ልማቶች ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከላከል የሚያስችል የውይይት መድረክ አካሄደ ኢትዮ ቴሌኮም በቴሌኮም መሠረተ ልማቶች ላይ እየደረሰ ያለውን አደጋ ለመከላከል፣ እንዲሁም በጉዳቶቹ መንስዔና መፍትሔዎቻቸው ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት ታህሳስ 30  ቀን 2012 ዓ.ም. የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አባላት፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው...

ጋዜጣዊ መግለጫ | Press Release

ኢትዮ ቴሌኮም በመላው ሀገሪቱ በ45 ዩኒቨርስቲዎች የሚማሩ 4000 ተማሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የ16 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ መርሐ ግብር ይፋ አደረገ ኢትዮ ቴሌኮም በዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች የድጋፍ መርሐ ግብርን በ2006 ዓ.ም የጀመረ ሲሆን የተጠቃሚዎችም ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በ2011 በጀት ዓመት መጨረሻ በ13 ዩኒቨርስቲዎች ለ840 ተማሪዎች ድጋፍ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን ይህ ድጋፍ የሚኖረውን ጠቀሜታ...

ኢትዮ ቴሌኮም ለአንድ መቶ ሴቶች በፋሽን ዲዛይን የሙያ መስክ ስልጠና እንዲያገኙ ድጋፍ አደረገ

ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ ከሚገኙ ክፍለ ከተሞች ለተውጣጡ አንድ መቶ ሴቶች በፋሽን ዲዛይን የሙያ መስክ ነፃ የትምህርት እድል መስከረም 23 ቀን 2ዐ12 ዓ/ም ሰጠ፡፡ ኩባንያችን በትምህርት ዘርፍ ከሚያደርጋቸው የማህበራዊ ኃላፊነት ሥራዎች መካከል ይህ የትምህርት እድል የተመቻቸው ሴቶች በትምህርት፣ በሥራ እንዲሁም በአጠቃላይ የኢኮኖሚ መስኮች ከወንዶች ያነሰ ተሳትፎ ያላቸው መሆኑን ከግምት በማስገባት ሴቶችን ማስተማር እና...

በኢትዮ ቴሌኮም እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መካከል የቴሌኮም አገልግሎቶች የክፍያ መፈጸሚያ አማራጮች ላይ የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ

ኢትዮ ቴሌኮም የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትና እና ቅልጥፍናን በማሳደግ የደንበኛን እርካታ ለመጨመር በርካታ የማሻሻያ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡  ከዚሁ ጋር በተያያዘ የድህረ ክፍያ አገልግሎት ደንበኞች የአገልግሎት ሂሳባቸውን በቀላሉ መክፈል እንዲችሉ በቅርቡ ተግባራዊ ከተደረጉ የክፍያ አማራጮች በተጨማሪ ሌሎች አማራጭ የክፍያ ዘዴዎችን ለመተግበር ዛሬ  መስከረም 12 ቀን 2012 ዓ.ም በኢትዮ ቴሌኮም እና በኢትዮጵያ ንግድ...