ኢትዮ ቴሌኮም በምሥራቅ ሪጅን የላቀ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን 4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት ጀመረ

ኩባንያችን በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች የዳታ ትራፊክ እድገትና ፍላጎትን መሠረት በማድረግ እያከናወነ ያለውን የ4G/LTE አገልግሎት የማስፋፊያ ሥራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል ከሁለት ቀናት በፊት በምሥራቅ ሪጅን በሚገኙ ሶስት ከተሞች ካደረጋቸው ማስፋፊያዎች በተጨማሪ በዛሬው ዕለት ደግሞ በማዕከላዊ ምሥራቅ ሪጅን ማለትም በሐረር፣ አወዳይ እና ሀረማያ ከተሞች የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ  የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ማስፋፊያ ፕሮጀክት አጠናቆ አገልግሎቱን ማስጀመር ችሏል፡፡

የ4G LTE አገልግሎት የላቀ ፍጥነትና ባንድዊድዝ እንዲሁም አስተማማኝ የዳታ አገልግሎት የሚሰጥ እንደመሆኑ ደንበኞቻችን አገልግሎታቸውን ዲጂታይዝ ለማድረግ፣ ምርታማነትን ለማሳደግ እና በአጠቃላይ የቴሌኮም አገልግሎት ላይ ያላቸውን ተሞክሮ በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ ያስችላል፡፡

ቀደም ሲል አዲስ አበባን ጨምሮ በደቡብ ምሥራቅ ሪጅን ፣በሰሜን ምዕራብ ሪጅን ፣ በምሥራቅ ምሥራቅ ሪጅን፣ በደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን እና በምስራቅ ሪጅን የተለያዩ ከተሞች የ4G/LTE አገልግሎት ማስፋፊያ መደረጉ የሚታወቅ ሲሆን ዛሬ በማዕከላዊ ምስራቅ ሪጅን ያስጀመርነውን ጨምሮ እስካሁን የ4ጂ ሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑ ከተሞች ቁጥር 33 ደርሷል፡፡

በቀጣይነትም ኩባንያችን በተመሳሳይ ሁኔታ የዳታ ትራፊክ እድገትና ፍላጎትን መሠረት ባደረገ መልኩ በዕቅድ ይዞ በከፍተኛ ርብርብ እያከናወናቸው ያሉ የ4G/LTE አገልግሎት የማስፋፊያ ሥራዎችን በማጠናቀቅ በተለያዩ የክልል ከቶሞች አገልግሎቱን በቅርቡ ለማስጀመር የሚያስችሉ ቅድመ ሥራዎች በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

በዚህ አጋጣሚ የቴኮም አገልግሎት መጠቀሚያ መሣሪያ (smart phone) እና የይዘት (content) አቅራቢዎች በመረጃ የበለፀገ ማህበረሰብና ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ እንዲሁም አሁን የተዘረጋውን ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የሞባይል ኔትወርክ በስፋት ለመጠቀም የሚያስችሉ ዘመናዊ የሞባይል ቀፎዎችና ይዘቶችን ለህብረተሰቡ በስፋትና በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የበኩላችሁን አስተዋጽዖ እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives