ኤትዮ ቴሌኮም ኤል.ቲ.ኢ. አድቫንስድ የተሰኘውን የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ከጥር 25 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ አውሏል፡፡ ኤል.ቲ.ኢ. አድቫንስድ ከ4ጂ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት በፍጥነትም ሆነ በጥራት እጅግ ተሸሽሎ የቀረበ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ነው፡፡

ኤል.ቲ.ኢ. አድቫንስድ የሞባይል ኢንተርኔት ጠቀሜታዎች

 • የላቀ ፍጥነት ያለው የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት መጠቀም የሚያስችል አገልግሎት ሲሆን ፍጥነቱም ከ4ጂ አገልግሎት በ 4 እጥፍ እንዲሁም ከ3ጂ አገልግሎት በ14 እጥፍ የላቀ ነው፡
 • ትላልቅ መጠን ያለቸውን ፋይሎች በፍጥነት ለመጫን (uploading) እና ለማውረድ (downloading) ያስችቻል፡፡
 • ኤች.ዲ. ቪዲዮዎችን እና ቪዲዮ ኮንፈረንሶችን በከፍተኛ የምስል ጥራት በቀጥታ ያለመቆራረጥ ለማስተላለፍ፣ 3ዲ ጌሞችን ለመጫወት ወዘተ…ያስችላል፡፡
 • ለትላልቅ ተቋማት ደህንነቱ የተጠበቀ የቨርቹዋል ፕራይቬት ኔትዎርክ (VPN) እንደ መደበኛ ብሮድባንድ ቪ.ፒ.ኤን. በመጠባበቂያነት ለመጠቀም ያገለግላል፡፡

ኤል.ቲ.ኢ. አድቫንስድ አገልግሎት የት ይገኛል?

በአሁኑ ወቅት አገልግሎቱ በሚከተሉት የሞባይል ኢንተርኔት አጠቃቀም ከፍተኛ በሆነባቸው  የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢዎች ይገኛል፡-

 • ቦሌ አውሮላን ማረፊያ
 • ቦሌ ፍሬንድሺፕ አካባቢ
 • ቦሌ መድኃኔዓለም
 • ቦሌ አትላስ
 • ልደታ (የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አካባቢ)
 • የዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት አካባቢ
 • መስቀል አደባባይ
 • ስቴድየም
 • አረጌው አውሮፕላን ማረፊያ
 • አፍሪካ ሕብረት
 • ኢትዮ ቴሌኮም ዋና መ/ቤት አካባቢ
 • ካዛንችስ
 • አራት ኪሎ (አንድነት ፓርክ)
 • ስድስት ኪሎ

ኤል.ቲ.ኢ. አድቫንስድ አገልግሎትን ለመጠቀም የሚያስችሉ የቀፎ ዝርዝር ሁኔታዎች (specifications)

ቴክኖሎጂ

LTE-A

ተርሚናል ካታጎሬ

≥ Cat 6

ኤል.ቲ.ኢ. አድቫንስድ አገልግሎትን ለመጠቀም ደንበኞች አገልግሎቱን መጠቀም የሚያስችሉ የሞባይል ስልኮች ፣ ዶንግሎች እና ታብሌቶች  ሊኖራቸው ይገባል፡፡ በመሆኑም  ደንበኞች እየተጠቀሙበት የሚገኘው ቀፎ አገልግሎቱን መጠቀም የሚያስችል መሆኑን ለማረጋገጥ www.gsmarena.com ላይ በመግባት እና የቀፎውን ዓይነት Search የሚለው ቦታ ካስገቡ በኋላ Network ከሚለው ውስጥ መመልከት ይችላሉ፡፡

ኤል.ቲ.ኢ. አድቫንስድ አገልግሎትን ለመጠቀም የሚያስችል የሲም ካርድ ዓይነት

ኤል.ቲ.ኢ.አድቫንስድ አገልግሎትን ለመጠቀም ከቀፎ በተጨማሪ  ደንበኞች  64K እና ከዚያ በላይ የሆነ ዪኒቨርሳል ሲም (USIM) መጠቀም ይገባቸዋል፡፡  በዚህም መሠረት፡-

 1. በዪኒቨርሳል ሲም (USIM) የ4ጂ አገልግሎትን በመጠቀም ላይ የሚገኙ ደንበኞቻችን ቀፏቸው ኤል.ቲ.ኢ. አድቫንስድ መጠቀም የሚያስችል ከሆነ ወደ ሽያጭ ማዕከሎቻችን መምጣት ሳይጠበቅባቸው አገልግሎቱን መጠቀም ይችላሉ፡፡
 2. በዪኒቨርሳል ሲም (USIM) የ3ጂ አገልግሎትን በመጠቀም ላይ የሚገኙ ደንበኞቻችን ቀፏቸው  ኤል.ቲ.ኢ. አድቫንስድ መጠቀም የሚያስችል ከሆነ ወደ ሽያጭ ማዕከሎቻችን መምጣት ሳይጠበቅባቸው የ3ጂ አገልግሎታቸው ወደ ኤል.ቲ.ኢ. አድቫንስድ በነፃ እንዲያድግላቸው ተደርጓል::
 3. ሲም ካርዳቸው ከ 64k በታች የሆነ ወይም ዪኒቨርሳል ሲም (USIM) የሌላቸው 3ጂ እና 4ጂ ደንበኞች ኤል.ቲ.ኢ. አድቫንስድ አገልግሎትን ለመጠቀም ሲም ካርዳቸውን ወደ ዪኒቨርሳል ሲም (USIM) መቀየር የሚገባቸው በመሆኑ በአቅራቢያቸው በሚገኝ የሽያጭ ማዕከላችን በመቅረብ በነፃ መቀየር ይችላሉ፡፡

በላቀ ፍጥነት ይደሰቱ!