የቴሌብር ቦነስ

የዕለት ተዕለት ሥራዎን በቴሌብር እያከናወኑ በሚያገኙት የቴሌብር ቦነስ ይደሰቱ።

  • ያልተገደበ የጥቅል አገልግሎት የገዙ  ደንበኞች ለቦነስ ብቁ አይሆኑም።
  • የቴሌብር ቦነስ እስከ መስከረም 29 ቀን 2014 ዓ.ም ይቆያል፡፡

የቴሌብር ደንበኛ ይሁኑ እና ስጦታ ያግኙ!

ለመጀመሪያ ጊዜ ለቴሌብር ደንበኝነት ሲመዘገቡ ብር 15 ሂሳብ የመክፈቻ ስጦታ ያገኛሉ። ማሳሰቢያ፡ የ15 ብር ስጦታው የአየር ሰዓት ለመሙላት ወይም ሀገር ውስጥ ለሚገኝ ወዳጅ ዘመድዎ ለማስተላለፍ ብቻ ያገለግላል።

እንዴት ለቴሌብር መመዝገብ ይቻላል?

ሀ) በቴሌብር የሞባይል መተግበሪያ ላይ፡-

  • “አዲስ አካውንት ይክፈቱ” የሚለውን ይጫኑ፣
  • "ፈጣን አካውንት ይክፈቱ" ወይም "በራስ አገዝ አካውንት ይክፈቱ" የሚለውን ይምረጡ፣
  • "የሞባይል ቁጥርዎን" ካስገቡ በኋላ "መለያ ቁጥር ያግኙ" የሚለውን ይጫኑ፣
  • ከዚያም በአጭር የጽሑፍ መልዕክት ባለ 6 አሃዝ የመለያ ቁጥር ይደርስዎታል፣ የሚደርስዎትን የመለያ ቁጥር በማረጋገጫ ባዶ ቦታው ላይ በማስገባት "ይቀጥሉ" የሚለውን ይጫኑ፣
  • ቀጥሎ ከታች የተዘረዘሩትን መታረም የሚችሉ የግል መረጃዎች ያገኛሉ፣
  • ማዕረግ፣
  • የመታወቂያ ዓይነት፣
  • የመታወቂያ ቁጥር፣
  • ስም፣ የአባት ስም እና የአያት ስም
  • ጾታ
  • የትውልድ ቀን፣ ወርና ዓ.ም
  • የሚመርጡት ቋንቋ
    • የግል መረጃውን ካስገቡ ወይም ካረጋገጡ በኋላ “ይቀጥሉ” የሚለውን ይጫኑ፣
    • ከዚያም የምስጢር መለያ ቁጥር በአጭር የጽሑፍ መልዕክት አማካኝነት ይደርስዎታል
    • የምስጢር መለያ ቁጥሩን በማስገባት “ይግቡ” የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ፣
    • የቴሌብር ሒሳብዎን ለማስጀመር የተላከልዎትን የምስጢር መለያ ቁጥር በራስዎ አዲስ ባለ ስድስት አሃዝ የምስጢር መለያ ቁጥር ይቀይሩ እና "ይቀጥሉ" የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ፣
    • በመጨረሻም የቴሌብር ሒሳብዎ በተሳካ ሁኔታ የጀመረ መሆኑን የሚገልጽ የማሳወቂያ መልዕክት በአጭር የጽሑፍ መልዕክት ይደርስዎታል።

 

ለ) በአጭር ቁጥር (USSD) አማካኝነት ለመመዝገብ

  • ወደ *127# ይደውሉ፣
  • ለመመዝገብ 1 ቁጥርን ይምረጡና ይላኩ፣
  • የግብዣ ቁጥሩን ያስገቡ ወይም ይህንን አማራጭ ለመዝለል ከፈለጉ # ይጫኑ፣
  • እንደገና ለማስጀመር ወደ *127# ይደውሉ፣
  • ለማስጀመር ዜሮን አስገብተው ይላኩ፣
  • ቋንቋ ይምረጡ
  • በ127 የተላከልዎትን የምስጢር መለያ ቁጥር አስገብተው በራስዎ አዲስ የምስጢር ቁጥር ይቀይሩ
  • በመጨረሻም የቴሌብር ሒሳብዎ በተሳካ ሁኔታ የጀመረ መሆኑን የሚገልጽ የማሳወቂያ መልዕክት በአጭር የጽሑፍ መልዕክት ይደርስዎታል።

የቴሌብር ሞባይል መተግበሪያን በማውረድ የዳታ ስጦታ ያግኙ!

  • የቴሌብር አይ.ኦ.ኤስ ወይም አንድሮይድ የሞባይል መተግበሪያን ከጎግል ፕሌይ ወይም አፕ ስቶር በነፃ ያውርዱና የቴሌብር አካውንት በመክፈት 70 ሜ.ባ የዳታ ስጦታ ያግኙ።
  • ስጦታው የቴሌብር ሞባይል መተግበሪያን ተጠቅመው የቴሌብር አካውንት በከፈቱበት የሞባይል አገልግሎት ቁጥርዎ ላይ የሚደርስዎት ይሆናል።

 

አሁኑኑ ያውርዱ
  • ለአንድሮይድ (ፕሌይ ስቶር)
  • ለአንድሮይድ (ኢትዮ ቴሌኮም አፕ ስቶር)
  • ለአይ.ኦ.ኤስ
 

ጓደኞችዎን ይጋብዙ እና የፍሌክሲ ጥቅል ስጦታ ያግኙ!

  • የቴሌብር ተጠቃሚ ከሆኑ የቴሌብር ሞባይል መተግበሪያ ወይም አጭር ቁጥር ላይ "ጓደኛ መጋበዝ" የሚለውን አማራጭ በመጠቀም ቤተሰቦችዎን፣ ጓደኞችዎን እና የሥራ ባልደረቦችዎን ለቴሌብር አገልግሎት እንዲመዘገቡ መጋበዝ ይችላሉ።

ሌሎችን እንዴት መጋበዝ ይችላሉ?

ግብዣዎችን እንዴት መላክ ይቻላል?

ሀ) በቴሌብር ሞባይል መተግበሪያ ለመጋበዝ

  1. የቴሌብር አካውንትዎን እንደከፈቱ በመተግበሪያው መነሻ ገጽ ታችኛው ቀኝ ጥግ ላይ "የእኔ አካውንት" የሚለውን ይጫኑ፣
  2. "ጓደኛ መጋበዝ" የሚለውን ይምረጡና ይጫኑ፣
  3. የጓደኛዎን የሞባይል ስልክ ቁጥር ያስገቡ እና "ላክ" ሚለውን ቁልፍ ይጫኑ፡፡

ለ) በአጭር ቁጥር (USSD) ለመጋበዝ

  1. ወደ *127# ይደውሉ፣
  2. # ያስገቡና "ላክ" የሚለውን ይጫኑ፣
  3. እንደገና # ያስገቡና "ላክ" የሚለውን ይጫኑ፣
  4. "ጓደኛ መጋበዝ" የሚለውን ይምረጡ (ቁጥር 9) ፣
  5. መጋበዝ የሚፈልጉትን ሰው የሞባይል ስልክ ቁጥር ያስገቡ፣
  6. የምስጢር መለያ ቁጥርዎን ያስገቡ፣
  7. ያስገቡትን የሞባይል ስልክ ቁጥር ትክክለኛነት ለማረጋገጥ 1 ቁጥርን ይምረጡ፣

ከዚያም ከቴሌብር በ127 የማሳወቂያ መልእክት ይደርስዎታል።

 ማሳሰቢያ፡ የሚያገኙት ጥቅል ስጦታ ለ48 ሰዓታት የሚያገለግል ይሆናል፡፡

የአየር ሰአት ይሙሉ እና የአየር ሰዓት ጥቅል ስጦታ ያግኙ!

  • የሞባይል አየር ሰዓት ሲሞሉ የ10 በመቶ የአየር ሰዓት ስጦታ ያገኛሉ። የአየር ሰዓት ስጦታው ለ5 ቀናት ብቻ ያገለግላል።

የአየር ሰዓት እንዴት ይሞላሉ?
  • ወደ *127# ይደውሉ ወይም በቴሌብር ሞባይል መተግበሪያ ይግቡ፣
  • ከተዘረዘረው አማራጭ ውስጥ “የአየር ሰዓት/ጥቅል” የሚለውን ይምረጡ፣
  • ለእርስዎ ከሆነ “ለራስ” የሚለውን ይምረጡ፣ ወይም
  • ለሌላ ሰው ከሆነ ደግሞ “ለሌላ ሰው” የሚለውን ይምረጡ፣
  • የተቀባዩን ስልክ ቁጥር ያስገቡ/ይምረጡ፣
  • የሚፈልጉትን የአየር ሰዓት መጠን ያስገቡ/ የገንዘብ መጠን ይምረጡ/ የጥቅል ዓይነቱን ይምረጡ፣
  • የሚስጥር መለያ ቁጥርዎን ያስገቡ
  • የግብይቱን ትክክለኛነት ያረጋግጡ፡፡

ጥቅል ይግዙ እና የ10 በመቶ ቦነስ/ቅናሽ ያግኙ!

  • የሞባይል ጥቅል በቴሌብር መተግበሪያ ሲገዙ እንደ መረጡት ጥቅል ዓይነት የ10 በመቶ ስጦታ ወይም ቅናሽ ይደረግልዎታል።