ቴሌብር እንደኪሴ
    • ይህ የአገልግሎት አይነት የቴሌብር ደንበኞች በቴሌብር አካውንት ያላቸው ቀሪ የሂሳብ መጠን በቂ ባልሆነበት ጊዜ ክሬዲት አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል አገልግሎት ነው፡፡
    • ደንበኞች በሚፈቀደው ዝቅተኛ እና ከፍተኛ የክሬዲት መጠን መካከል ማንኛውንም መጠን መበደር ይችላሉ።

የቴሌብር እንደኪሴ አገልግሎት ለማግኘት ብቁ የሚያደርጉ መስፈርቶች

  • የደንበኛ የመበደር አቅም ደንበኛው ባደረገው የ6 ወር የቴሌብር የገንዘብ እንቅስቃሴ እና በቴሌኮም አጠቃቀም ይወሰናል።
  • በተጨማሪም ከታች ያሉት የቴሌብር ግብይቶች እና የገንዘብ ልውውጥ የደንበኛ የብድር አቅምን ለማስላት የሚውሉ ይሆናል።
    • ለእርስዎ ወይም በስጦታ የአየር ሰዓት መሙላት ወይም ጥቅል
      መግዛት (በራስ አገዝ ወይም ከወኪሎች)
    • ዕቃ ወይም አገልግሎት ግዢን መፈጸም
    • ለእርስዎ ወይም የሌላ ደንበኛ ቢል ክፍያ (በራስ አገዝ ወይም
      ከወኪሎች) ማከናወን
    • ለእርስዎ ወይም የሌላ ደንበኛን የፍጆታ አገልግሎት ክፍያ (በራስ አገዝ ወይም ከወኪሎች) መፈፀም
    • ከውጭ አገር ገንዘብ መቀበል
    • የጅምላ ክፍያ (ደሞዝ፣ ሴፍቲኔት…) መፈፀም 
    • የትኬት ክፍያ መፈፀም
    • ለገንዘብ ማሰባሰቢያ የእርዳታ ክፍያ መፈፀም
    • የቁጠባ አገልግሎት
    • የቴሌኮም ፍጆታ (ድምጽ፣ ዳታ ወይም መልዕክት) መፈፀም

• ከቴሌኮም አገልግሎት ፍጆታ በተጨማሪ ቢያንስ አንድ የቴሌብር አገልግሎት መጠቀም ይኖርብዎታል፡፡
• የ6 ወራት ግብይት ወይም አጠቃቀም ለብቁነት መስፈርት የሚቆጠር ይሆናል።
• በሚፈቀደው ዝቅተኛ እና ከፍተኛ የክሬዲት መጠን መካከል ማንኛውንም መጠን መበደር ይችላሉ።

የቴሌብር እንደኪሴ ማስጀመሪያ መስፈርቶች

  • 18 አመት እና ከዚያ በላይ
  • አገልግሎት የሚሰጥ የኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርድ መያዝ
  • የቴሌብር እና የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቶችን እንደ ዳታ/ድምጽ/አጭር የጽሁፍ መልዕክት መጠቀም ይኖርብዎታል፡፡
  • ለመመዝገብ በአጭር ቁጥር (*127#) ወይም በቴሌብር መተግበሪያን ይጠቀሙ፡፡
  • የቴሌብር የደንበኝነት ቆይታ 3 ወር እና ከዛ በላይ መሆን ይኖርበታል፡፡

መስፈርቶቹን በመጠቀም ነጥቡ እንዴት እንደሚሰራ

ስኮሪንግ ባንድ ሬንጅ

የብድር መጠን ገደብ

ዝቅተኛ

ከፍተኛ

ዝቅተኛከፍተኛ

0

650

 

 

 

0

 

 

 

0

651

660

671

680

681

690

691

700

701

710

711

720

721

730

 

 

 

 

 

 

1

5

731

740

50

741

750

100

751

760

200

761

770

300

771

780

400

781

790

500

791

800

600

801

810

700

811

820

800

821

830

1000

831

840

1200

841

850

1500

851

860

1500

 

እንደኪሴ

የክሬዲት መጠንታሪፍ
የአገልግሎት ክፍያዕለታዊ ክፍያቅጣት
2002.50%1.10%0.11%
400 1%
600 0.95%
1,100 0.85%
2,000 0.80%
2,200 0.75%
2,500 0.70%
3,500 0.30%
ማስታወሻ: ሁሉም የገንዘብ መጠኖች በብር የተቀመጡ ናቸው፡፡

የብድር አይነት

ትንሹ የብድር መጠን

ትልቁ የብድር መጠን

የክፍያ ጊዜ

የአገልግሎት ክፍያ

እለታዊ ክፍያ

ቅጣት 

እንደኪሴ  

12,000

1 ወር 

3%0.30%-1.2%0.50%

በቴሌብር
የሞባይል መተግበሪያ
እንዴት አገልግሎቱን ማስጀመር እና መጠቀም እንችላለሁ?

አገልግሎቱን ለማስጀመር

  • የፋይናንስ አገልግሎት የሚለውን ይጫኑ
  • ቴሌብር እንደኪሴ የሚለውን
    ይምረጡ
  • ደንብ እና ሁኔታዎችን በማንበብ የ √ ምልክት በመጫን መስማማትዎን ይግለጹ
  • ለማስጀመር የሚለውን ይጫኑ

አገልግሎቱን ለመጠቀም

  •  ቀሪ ሂሳብዎ አነስተኛ ሆኖ የተለያዩ አገልግሎቶችን ሲጠቀሙ ለሚደርስዎት የክሬዲት ክፍያ መጠቀም እንደሚፈልጉ የሚጠይቀውን ማሳወቂያ መስማማትዎን ይግለጹ

የወሰዲትን ክሬዲት ለመክፈል

  • የቴሌብር አካውንትዎ ላይ ገንዘብ ተቀማጭ ያድርጉ

1. የውል ስምምነት

ይህ ስምምነት (ከዚህ በኋላ "ደንቦች እና ሁኔታዎች" የሚባል) የክሬዲት ክፍያ አገልግሎትን በተመለከተ አጠቃላይ ደንብ እና ሁኔታዎች ያካትታል፡፡

እነዚህ ደንቦችና ሁኔታዎች እንዲሁም ከዚህ ጋር የተያያዙ ማሻሻያዎች እና ለውጦች በክሬድት ደንበኛው ተነበው ተቀባይነት ሲያገኙ (ይሲማሙ የሚለውን ምርጫ ሲጫኑ) ሥራ ላይ ይውላሉ፡፡

2. ትርጓሜ

በዚህ የደንቦች እና ሁኔታዎች መረጃ ውስጥ የተዘረዘሩ ቃላት እና አባባሎች የሚከተለውን ትርጉሜ ይይዛሉ፡

  • " የቴሌብር እንደኪሴ ክሬዲት ክፍያ አገልግሎት" ማለት ለግለሰብ ደንበኞች በኤሌክትሮኒክ ገንዘብ አነስተኛ መጠን ያለው ክሬዲት የሚያገኙበት የአገልግሎት አይነት ነው።
  • “የክሬዲት ክፍያ” ማለት ከታች በተቀመጡ ደንብ እና ሁኔታዎች መሰረት በኢትዮ ቴሌኮም ለደንበኞች የሚቀርብ የክሬዲት አገልግሎት ነው፡፡
  • “የግለሰብ ደንበኛ” ማለት በስሙ አነስተኛ የቁጠባ አካውንት ያለው የቴሌብር ደንበኛ ነው።
  • "አንተ" "አንቺ" ወይም "የአንተ" ማለት ደንበኛውን ለማለት ነው።
  • “ኤ-ገንዘብ” ማለት እኩል መጠን ያለው ጥሬ ገንዘብን የሚወክል ደንበኛው የሚመለከተው የቴሌብር የኤሌክትሮኒክስ የገንዘብ ዋጋ ነው።
  • "ዋና መጠን" ማለት መጀመሪያ እንደመነሻ ከኢትዮ ቴሌኮም የተወሰደ የክሬዲት መጠን ነው፡፡
  • “ደንበኛ” ማለት በስሙ በቴሌብር አካውንት ለክሬዲት ክፍያ የተመዘገበ የቴሌብር ተመዝጋቢ ነው።
  • "አንተ" "አንቺ" ወይም "የአንተ" ማለት ደንበኛውን ለማለት ነው።
  • "ዋና ገንዘብ" ማለት በመጀመሪያ በክሬዲት የወሰዱት የገንዘብ መጠን ማለት ነው።
  • "የግብይት ክፍያ" የአገልግሎት ክፍያ፣ የቅጣት እና ሌሎች ለክሬዲት ክፍያ አገልግሎት የሚከፈሉ ክፍያዎችን ያጠቃልላል፡፡
  • “የአገልግሎት ክፍያ” ማለት የክሬዲት ክፍያ አገልግሎትን ለመጠቀም በደንበኞች የሚከፈል የክፍያ መጠን ነው።
  • "የቅጣት ክፍያ" ማለት ለክሬዲት የመጨረሻ መክፍያ ቀነ ገደቡ አልፎ ክፍያው ሲፈጸም የሚከፍል ተጨማሪ የክፍያ መጠን ነው፡፡
  • "የመጨረሻ ክፍያ ቀን" ማለት የክሬዲት መመለሻ የጊዜ ገደብ (ገባሪ የክሬዲት ጊዜ) ያላለፈ መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን ክሬዲት ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ 30 ቀናትን የሚያካትት ነው፡፡
  • "ቀነ ገደቡ ያለፈ" ማለት የክሬዲት መመለሻ ቀነ ገደቡ ያለፈ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡
  • "የተበላሸ ብድር" ማለት ክሬዲት ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በ90 ቀናት ውስጥ ያልተከፈለ ክሬዲት ሲሆን በወቅቱ ባለመመለሱ እንደ ተበላሸ ብድር መሆኑን የሚያሳይ ጊዜ ነው፡፡

3. ደንብ እና ሁኔታዎችን ስለመቀበል

  • የክሬዲት ክፍያ አገልግሎትን ለመጠቀም ከማመልከትዎ በፊት እነዚህን ደንብ እና ሁኔታዎች በጥንቃቄ በማንበብ የክሬዲት ክፍያ ሂሳብ አጠቃቀም እና መመሪያን አንብበው ይስማሙ፡፡
  • በእነዚህ ደንቦችና ሁኔታዎች ካልተስማሙ እባክዎን ከዝርዝር መምረጫ ውስጥ ሰርዝ የሚለውን ይጫኑ፤
  • ደንቦችና ሁኔታዎችን እንዳነበቡ፣ እንደተረዱና እንደተቀበሉ የሚቆጠረው፡-
  • “ይስማሙ” የሚለውን አማራጭ ሲጫኑ ደንብ እና ሁኔታዎችን በማንበብ ተረድተው ለማክበር መስማማትዎን እንዳረጋግጡ ወይም ክሬዲት ክፍያን ለመጠቀም እንደተስማሙ ይወሰዳል።
  • ደንብ እና ሁኔታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በኢትዮ ቴሌኮም እና በዳሽን ባንክ ሊሻሻሉ ወይም ሊለወጡ የሚችሉ ሲሆን በቴሌብር ፖርታል ወይም ድህረ ገጽ ላይ ከተለቀቁበት ዕለት ጀምሮ በደንበኛው ላይ ተግባራው ይደረጋሉ፡፡
  • የክሬዲት ክፍያ አገልግሎትን በኤሌክትሮኒካዊ መንገድ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ለመተግበር እና የክሬዲት ክፍያ አገልግሎትን በኤሌክትሮኒካዊ መንገድ በቴሌብር ሲስተም ለመጠቀም ተስማምተዋል።

4. የክሬዲት ክፍያ አገልግሎትን ለማስጀመር

የክሬዲት ክፍያ አገልግሎትን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ለማስጀመር ቢያንስ፡-

  • 18 አመት እና ከዚያ በላይ
  • አገልግሎት የሚሰጥ የኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርድ መያዝ
  • የቴሌብር እና የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቶችን እንደ ዳታ/ድምጽ/አጭር የጽሁፍ መልዕክት የሚጠቀሙ
  • የቴሌብር የደንበኝነት ቆይታ 3 ወር እና ከዛ በላይ መሆን አለበት
  • ለመመዝገብ በዩኤስኤስዲ (*127#) ወይም በቴሌብር መተግበሪያ መጠቀም ይችላሉ፡፡
  • ለተሳካ ምዝገባ የማሳወቂያ አጭር የፅሁፍ መልዕክት ይደርስዎታል፡፡

5. የክሬዲት ክፍያ አገልግሎት ለማግኘት መሰረታዊ መስፈርቶች

  • የደንበኛ የመበደር አቅም ደንበኛው የክሬዲት ክፍያ አገልግሎት ለመጠቀም ጥያቄ ካቀረበበት ቀን በፊት ባደረገው የ6 ወር የቴሌብር የገንዘብ እንቅስቃሴ እና በቴሌኮም አጠቃቀም ይወሰናል። ከታች ያሉት የቴሌብር ግብይቶች እና የገንዘብ ልውውጥ የደንበኛ የብደር አቅምን ለማስላት ይውላሉ።
  • ለእርስዎ ወይም ለስጦታ የአየር ሰዓት መሙላት ወይም ጥቅል መግዛት (በራስ አገዝ ወይመ ከወኪሎች)
  • ዕቃ ወይም አገልግሎት በመግዛት ግብይት መፈጸም
  • ለእርስዎ ወይም የሌላ ደንበኛ ቢል ክፍያ (በራስ አገዝ)
  • ለእርስዎ ወይም የሌላ ደንበኛ የፍጆታ አገልግሎት ክፍያ (በራስ አገዝ)
  • ከውጭ አገር ገንዘብ መቀበል
  • የጅምላ ክፍያ (ደሞዝ፣ ሴፍቲኔት…)
  • የትኬት ክፍያ
  • ለገንዘብ ማሰባሰቢያ የእርዳታ ክፍያ
  • የቁጠባ አገልግሎት
  • የቴሌኮም ፍጆታ (ድምጽ፣ ዳታ ወይም መልዕክት)
  • ከቴሌኮም አገልግሎት ፍጆታ በተጨማሪ ቢያንስ አንድ የቴሌብር አገልግሎት መጠቀም ይጠበቅብዎታል፡፡
  • የ6 ወራት ግብይት ወይም አጠቃቀም (አንፃራዊ ወር) ለብቁነት ይቆጠራል።

6. የክሬዲት መጠን እና ክፍያ

  • በሚፈቀደው ዝቅተኛ እና ከፍተኛ የክሬዲት መጠን መካከል ማንኛውንም መጠን መበደር ይችላሉ።
  • ሌላ ክሬዲት ለማግኘት መጀመሪያ ቀድመው የወሰዱትን ክሬዲት መክፈል ይጠበቅብዎታል፡፡
  • ያለብዎትን ክሬዲት በከፊል ወይም በሙሉ መክፈል ይችላሉ።
  • የክሬዲት መክፈያ ማብቂያ ቀነ ገደብ ቡድሩን ከወሰዱበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 30 ቀናት ውስጥ ይሆናል።
  • ያለብዎትን የሰላሳ (30) ቀን ክሬዲት በአንድ ቀን ውስጥ ከከፈሉ የወሰዱትን የብድር መጠን 6% ሲሆን ከዚያ በኋላ ሲከፍሉ በቀን 138% የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላሉ፡፡
  • ከ30 ቀን በኋላ ለሚከፍሉ የወሰዱትን የብድር መጠን ወይም በከፊል ተከፍሎ ባልተከፈለ ቀሪ ገንዘብ ላይ በቀን 2 % በመቶ የቅጣት ክፍያ እንዲከፍሉ ታሳቢ ይደረጋል።
  • የክሬዲት ክፍያ የሚፈጸመው ማንኛውንም የገንዘብ መጠን ወደ ኢ-ገንዘብ አካውንታቸው ገቢ ሲሆን በቀጥታ በመቀነስ ነው።
  • በጉርሻ የሚያገኙት ገንዘብ ለክሬዲት ክፍያ አይውልም፡፡
  • ይህ የክሬዲት አገልግሎት የሚሰጠው ኢትዮ ቴሌኮም ከዳሸን ባንክ ጋር በመተባበር ነው፡፡ ለክሬዲት አገልግሎት የሚውለውን ገንዘብ የሚያቀርበው ዳሸን ባንክ ሲሆን ይህን ገንዘብ በባለቤትነት የሚቆጣጠረው ዳሸን ባንክ ነው፡፡ የተበላሸ ወይም ቀነ ገደቡ ያለፈ ብድር በሚከሰትበት ጊዜ ባንኩ ጉዳዩን ወደ መደበኛ ፍርድቤት የመውሰድና የመክሰስ ሙሉ መብት አለው፡፡ ከፍርድቤት ውጭ ያሉ አማራጮች የመጠቀም መብት አለው፡፡

ይህ ዉል (ከዚህ በኋላ "ደንቦች እና ሁኔታዎች" እየተባለ የሚጠራው) የቴሌብር መላ የብድር አገልግሎት ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ አጠቃላይ ደንብ እና ሁኔታዎች ያካትታል፡፡
እነዚህ ደንቦችና ሁኔታዎች እንዲሁም ከዚህ ጋር የተያያዙ ማሻሻያዎች እና ለውጦች የቴሌብር መላ አነስተኛ የብድር አገልግሎት በደንበኛዉ ተነበው ተቀባይነት ሲያገኙ (ይስማሙ የሚለውን ምርጫ ሲጫን) በደንበኛው ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
1. ትርጓሜ
በዚህ የደንቦች እና ሁኔታዎች መረጃ ውስጥ የተዘረዘሩ ቃላት የሚከተለውን ትርጉም ይይዛሉ፡-
1.1. "ዳሽን ባንክ" ማለት ቁጥጥር የሚደረግበት የፋይናንስ ተቋም ሲሆን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ለቴሌብር ደንበኞች መላ አነስተኛ የብድር አገልግሎት ለመስጠት የተስማማ የፋይናንስ ተቋም ነው።
1.2. "ኢትዮ ቴሌኮም" ማለት ክፍያ ለመፈፀም ፈቃድ ያለው እና ከዳሽ ባንክ ጋር በመተባበር ቴሌብር መለ አነስተኛ የብድር አገልግሎት ለቴሌብር ደንበኞች ለመስጠት ስምምነት ያለው ተቋም ነው፡፡
1.3. "የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ" ማለት በአዋጅ ቁጥር 591/2001 መሠረት ለፋይናንስ ተቋማት ፍቃድ ለመሰጠትና ሥራቸዉን ለመቆጣጠር የተቋቋመ ተቋም ነው።
1.4. "ቴሌብር" ማለት ደንበኞች የሞባይል ስልካቸዉን በመጠቀም የፋይናንስ አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚያስችል የኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት የንግድ ስም ነው።
1.5. "የቴሌብር አካውንት" ማለት የቴሌብር ተጠቃሚ ደንበኞች በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ገንዘብ የሚያስቀምጡበት፣ የሚላላኩበት እና የሚቀበሉበት አካዉንት ነዉ ፡፡
1.6. "መላ አነስተኛ የብድር አገልግሎት" ማለት በዳሽን ባንክና በኢትዮ ቴሌኮም የጋራ ትብብር ግለሰብ ደንበኞች በኤሌክትሮኒክ ገንዘብ አነስተኛ መጠን ያለው ብድር በቴሌብር የሚያገኙበት የአገልግሎት ዓይነት ነው።
1.7. “መላ መዳረሻ አነስተኛ የብድር አገልግሎት” ማለት ለግል እና ለመንግስት ተቋማት ሰራተኞች ከየተቋማቸዉ ጋር በሚኖር ስምምነት ከታች በተቀመጡ ደንብ እና ሁኔታዎች መሰረት በቴሌብር አማካኝነት ዳሽን ባንክ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር የሚያቀርበዉ የብድር አገልግሎት ነው፡፡
1.8. “ግለሰብ ደንበኛ” ማለት የተፈጥሮ ሰዉ ሆኖ በስሙ የቴሌብር አካውንት ያለዉና ቴሌብር መላ አነስተኛ የብድር አገልግሎት ለመዉሰድ የተስማማ ማለት ነው።
1.9. “ኤሌክትሮኒክ ገንዘብ/ኢ- መኒ” ማለት ከ ኢትዮጵያ ብር ጋር እኩል መጠን ያለው ገንዘብን የሚወክል ደንበኛው የሚያስተዳድረዉ አና በደንበኛዉ የቴሌብር ሂሳብ ዉስጥ የሚገኝ የኤሌክትሮኒክስ የገንዘብ ዋጋ ነው።
1.10. "አንተ" ወይም " የአንተ" ማለት የግለሰብ ደንበኛ ማለት ሲሆን የግለሰቡን የግል ተወካዮችም ያጠቃልላል።
1.11. "እኛ" "አኛን" እና "የእኛ" ማለት የኢትዮጵያ ደሽን ባንክ እና ኢትዮ ቴሌኮም ማለት ነው፡፡
1.12. “የአገልግሎት ክፍያ ” ማለት መላ አነስተኛ የብድር አገልግሎትን ለመጠቀም በግለሰብ ደንበኞች የሚፈፀም ክፍያ ነው ::የዚህ ክፍያ መጠን በኢትዮ ቴሌኮም እና በዳሽን ባንክ ውሳኔ በማንኛውም ጊዜ አስቀድሞ በሚሰጥ ማሳሰቢያ ሊቀየር ይችላል።
1.13. ”ዕለታዊ ክፍያ ” ማለት ሳይከፈል በቀረዉ የዕዳ መጠን ላይ ግለሰብ ደንበኛዉ በወሰደዉ የብድር ዓየነት መሠረት በየዕለቱ የሚከፈል የክፍያ ዓይነት ነዉ ፡፡
1.14. "የቅጣት ክፍያ" ማለት የብድሩ ግለሰብ ደንበኛዉ በገባዉ ዉል መሠረት የብድሩን ገንዘብ ሳይከፍል የቀረ እንደሆን የሚከፍለዉ ገንዘብ ነዉ ፡፡
1.15. "የክፍያ ቀን " ማለት ግለሰብ ደንበኛዉ የወሰደዉን ብድር ከፍሎ እንዲያጠናቅቅ የሚጠበቅበት የመጨረሻዉ ቀን ነወ ፡፡
1.16. "የተበላሸ ብድር" ማለት ከክፍያ ቀን ማግስት ጀምሮ በሚቆጠር 90 ቀናት ዉስጥ ያልተከፈለ ዕዳ ነዉ፡፡
1.17. በአነስታይ ፆታ የተገለፁ ለተባዕታይ ፆታ እንደዚሁም በተባዕታይ ፆታም የተገለፁ ለአነስታይ ፆታ ያገለግላሉ
1.18. ግለሰብ የሚለዉ ቃል ወንድና ሴት ፆታን ለመግለፅ ያገለግላል ፡፡


2. ደንብ እና ሁኔታዎችን ስለመቀበል
2.1. መላ የብድር አገልግሎትን ለመጠቀም ከማመልከትዎ በፊት እነዚህ ደንብ እና ሁኔታዎች ላይ የተጠቀሰውን የ ብድሩን አጠቃቀም እና መመሪያ በጥንቃቄ በማንበብ እና በመረዳት መስማማት ይኖርቦታል፡፡
2.2. በእነዚህ ደንቦችና ሁኔታዎች ካልተስማሙ እባክዎን ከዝርዝር መምረጫ ውስጥ ሰርዝ የሚለውን ይጫኑ፤
2.3. ደንቦችና ሁኔታዎችን እንዳነበቡ፣ እንደተረዱና እንደተቀበሉ የሚቆጠረው፡-
“ይስማሙ” የሚለውን አማራጭ ሲጫኑ ደንብ እና ሁኔታዎችን በማንበብ ተረድተው ለማክበር መስማማትዎን እንዳረጋግጡ ወይም ብድር ክፍያን ለመጠቀም እንደተስማሙ ይወሰዳል።
2.4. መላ አነሰተኛ የብድር አገልግሎትን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ለመተግበር እና የክሬዲት አገልግሎትን በኤሌክትሮኒካዊ መንገድ ብቻ በቴሌብር ሲስተም ለመጠቀም ተስማምተዋል።
2.5. ደንብ እና ሁኔታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በኢትዮ ቴሌኮም እና በዳሽን ባንክ ሊሻሻሉ ወይም ሊለወጡ የሚችሉ ሲሆን ይህንንም ለዉጥ የሚያስገነዝብ ማሳሰቢያ አስቀድሞ እንዲደርስዎት ይደረጋል ፡፡ እነዚህ ለዉጦች በቴሌብር ፖርታል፣በቴሌብር መተግበሪያ ወይም ድረ ገጽ ላይ ከተለቀቁበት ዕለት ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡
2.6. ደንበኛው ገንዘቡን ለህጋዊ አላማ ለማዋል ተስማምተዋል።
3. የብድር አገልግሎትን ለማስጀመር
የብድር አገልግሎትን ከኢትዮ ቴሌኮም እና ዳሽን ባንክ ጋር ለማስጀመር ቢያንስ፡-
3.1. እነዚህን ደንቦችና ሁኔታዎችን ሊያነቡ፣ሊረዱ እና ሊስማሙ ይገባል
3.2. 18 አመት እና ከዚያ በላይ መሆን
3.3. አገልግሎት የሚሰጥ የኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርድ መያዝ
3.4. የቴሌብር እና የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቶችን እንደ ዳታ/ድምጽ/አጭር የጽሁፍ መልዕክት የሚጠቀሙ መሆን አለብዎት
3.5. የቴሌብር የደንበኝነት ቆይታ 3 ወር እና ከዛ በላይ መሆን አለበት
ለመመዝገብ በዩ ኤስ ኤስ ዲ (*127#) ወይም በቴሌብር መተግበሪያ መጠቀም ይችላሉ፡፡
4. መላ አነሰተኛ ብድር ለማግኘት መሰረታዊ መስፈርቶች፤
• የግለሰብ ደንበኛው የመበደር አቅም፣ ደንበኛው የብድር ክፍያ አገልግሎት ለመጠቀም ጥያቄ ካቀረበበት ቀን በፊት ባደረገው የ6 ወር የቴሌብር የገንዘብ እንቅስቃሴ፣ቀደም ሲል የወሰደዉን ብድር የመክፈል ታሪክ እና በቴሌኮም አገልግሎት አጠቃቀም ይወሰናል። ከታች ያሉት የቴሌብር ግብይቶች እና የገንዘብ ልውውጥ የደንበኛ የብደር አቅምን ለማስላት ይውላሉ።
o የአየር ሰዓት መሙላት ወይም ጥቅል መግዛት (በራስ አገዝ ወይመ ከወኪሎች)፣
o ዕቃ ወይም አገልግሎት በመግዛት ግብይት መፈጸም፣
o ቢል ክፍያ (በራስ አገዝ ወይም ከወኪሎች)፣
o ለእርስዎ ወይም የሌላ ደንበኛ የፍጆታ አገልግሎት ክፍያ (በራስ አገዝ ወይም ከወኪሎች)፣
o በልክ ዲስፐርስመንት ( የቀን ሠራተኞች ክፍያ ፣ደመወዝ ፣ዕርዳታ፣ጡረታ፣…) ክፍያ በቴሌብር መቀበል፣
o ከውጭ አገር ገንዘብ መቀበል፣
o የትኬት ግዢ፣
o ለገንዘብ ማሰባሰቢያ የእርዳታ ክፍያ( ፈንድ ረይዚንግ)፣
o በቴሌብር ወኪሎች በኩል ገንዘብ መቀበልና ወጪ ማድረግ፣
o የቁጠባ አገልግሎት፣
o ገንዘብ መላክ፣
o የቴሌኮም ፍጆታ (ድምጽ፣ ዳታ ወይም መልዕክት)፣
o በቴሌብር የተወሰደን ብድር በአግባቡ የመክፈል የቀደመ ታሪክ ፡፡
• ብቁ ለመሆን ደንበኞች ከቴሌኮም አገልግሎት ፍጆታ በተጨማሪ የቴሌብር አገልግሎት መጠቀም አለባቸው፡፡
• መላ መዳረሻ ብድር ለማግኘት ወርሃዊ ደሞዝን በቴሌብር አማካኝነት መቀበል ወይም ከሚሰራበት ተቋም ጋር የሚደረግ ስምምነት በቂ ነዉ፡፡
5. የብድሩ መጠን እና ክፍያ
5.1. በሚፈቀደው ዝቅተኛ እና ከፍተኛ የብድር መጠን መካከል ማንኛውንም መጠን መበደር ይችላሉ።
5.2. የጠየቁትን የብድር መጠን እንዳገኙ የቴሌብር ሂሳብዎ (ኤሌክትሮኒክ-ገንዘብ አካውንት) ላይ ገቢ ይደረጋል።
5.3. ሌላብድር ለማግኘት መጀመሪያ ከቴሌብር የወሰዱትን ብድር መክፈል ይጠበቅብዎታል፡፡
5.4. ያለብዎትን ብድር በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውሰጥ በከፊል ወይም በሙሉ መክፈል ይችላሉ፡፡
5.5. እንደየ ብድሩ ዐዓይነት የብድር መከክፈያ ቀነ ገደብ 1 ቀን ፣ 7 ቀን፣ 30 ቀን እና 50 ነዉ፡፡
5.6. ያለብዎትን የአንድ ቀን ዕዳ በ1 ቀን ውስጥ ከከፈሉ የዋናዉን ዕዳ 1% የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላሉ፡፡
5.7. ያለብዎትን የሰባት ቀን ብድር በ7 ቀናት ውስጥ ከከፈሉ በመጀመሪያዉ ቀን የዋናዉን ዕዳ 1% የአገልግሎት ክፍያ እና ከሁለተኛው ቀን ጀምሮ የክሬዲት መጠነዎን መሰረት ያደረገ በቀን የዋናዉን ዕዳ ከ0.35% እስከ 1.2% ክፍያ ይከፍላሉ፡፡
5.8. ያለብዎትን ኦቨርድራፍት ብድር በ30 ቀናት ውስጥ ከከፈሉ የወሰዱትን የብድር መጠን 2.5% በመጀመሪያዉ ቀን የሚከፍሉ ሲሆን ከዚያ በኋላ ሲከፍሉ የክሬዲት መጠነዎን መሰረት ያደረገ በቀን ከ 0.3% እስከ 1.1% ተጨማሪ የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላሉ፡፡
5.9. ያለብዎትን የሰላሳ ቀን ብድር በ30 ቀናት ውስጥ ከከፈሉ የወሰዱትን የብድር መጠን 3% በመጀመሪያዉ ቀን የሚከፍሉ ሲሆን ከዚያ በኋላ ሲከፍሉ የክሬዲት መጠነዎን መሰረት ያደረገ በቀን ከ0.3% እስከ 0.8% ተጨማሪ የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላሉ፡፡
5.10. ያለብዎትን የሃምሳ ቀን ብድር በ50 ቀናት ውስጥ በትክክል ከከፈሉ የአገልግሎት ክፍያ የወሰዱትን የብድር መጠን 6% የሚከፍሉ ሲሆን ከዚያ በኋላ ሲከፍሉ የክሬዲት መጠነዎን መሰረት ያደረገ በቀን ከ0.5% እስከ 0.7% ተጨማሪ የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላሉ፡፡
5.11. ለመላ መዳረሻ የብድር ክፍያዉ በወሰዱት የብድር ጊዜ ተከፋፍሎ ቀስ በቀስ ይከፈላል ፡፡
5.12. የደመወዝዎን 30% ለወሰዱት መላ መዳረሻ የመክፈያ ቀነ ገደቡ 3 ወር ሲሆን 10% የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላሉ፡፡
5.13. የመክፈያ ጊዜዉ 9 ወር ለሆነ የ2 ወር ደመወዝ መላ መዳረሻ ብድር 16% የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላሉ ፡፡
5.14. የመክፈያ ጊዜዉ 12 ወር ለሆነ የ3 ወር ደመወዝ መላ መዳረሻ ብድር 20% የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላሉ ፡፡
5.15. የ2 እና የ3 ወር መላ መዳረሻ ብድርን ከመክፈያ ጊዜዉ ቀደም ብሎ ከከፈሉ የቀሪ ክፍያዉን 3% ብቻ የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላል፡፡
5.16. ያለብዎትን ዕዳ በቀነ ገደቡ ውስጥ የማይከፍሉ ከሆነ ባለበዎት ክሬዲት መጠን ላይ በየዕለቱ የሚሰላ 0.11% የቅጣት ክፍያ ይከፍላሉ፡፡ ነገር ግን ለመላ የቀን ብድር ያለብዎን ክሬዲት በቀነ ገደቡ ውስጥ የማይከፍሉ ከሆነ ባለበዎት ክሬዲት መጠን ላይ በየዕለቱ የሚሰላ 2% የቅጣት ክፍያ ይከፍላሉ::
5.17. ብደሩን የመክፈያ ቀነ ገደብ ባለፈ 90 ቀናት ዉስጥ ግለሰብ ደንበኛዉ የማይከፍል ከሆነ ሳይከፈል የቀረዉ ዕዳ ከሳንዱቅ የቁጠባ ሂሳቡ በቀጥታ ተቆራጭ ይደረጋል፣
5.18. በጉርሻ የሚያገኙት ገንዘብ ለክሬዲት ክፍያ አይውልም፡፡
5.19. ብድሩ መከፈል ባለበት ጊዜ ሳይከፈል የቀረ እንደሆነ ኢትዮ ቴሌኮም እና ዳሽን ባንክ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከባለዕዳዉ የደሽን ባንክ ወይም ሌሎች ባንኮች ሒሳብ በቀጥታ መቁረጥን ጨምሮ ማናቸዉም አማራጭ ዜዴዎች በመጠቀም ከፍርድ ቤት ዉጭ ባለ አማራጭ ዕዳዉን መሰብሰብ ይችላሉ፡፡
5.20. የመክፈያ ጊዜው ካለፈ በኋላ ግለሰብ ደንበኛዉ በሰዓቱ ካልከፈለ ኢትዮ ቴሌኮም እና ዳሽን ባንክ የቀረውን የብድር መጠን ከቴሌብር ሂሳቡ ወዲያውኑ ተቀናሽ ያደርጋሉ ፡፡
5.21. ከፍርድ ቤት ዉጭ ባለ አማራጭ ዕዳዉን ለመሰብሰብ ያግዝ ዘንድ ኢትዮ ቴሌኮም እና ዳሽን ባንክ የግለሰብ ደንበኛዉን የመኖሪያ ወይም የሥራ አድራሻ ማናቸዉም አማራጭ ዘዴዎች በመጠቀም አፈላልገዉ በማግኘት ዕዳዉን የመሰብሰብ መብት ያላቸዉ መሆኑን ግለሰብ ደንበኛዉ ተስማምቷል፡፡
5.22. ዕዳዉ መከፈል ባለበት ጊዜ ሳይከፍል የቀረ እንደሆነ ኢትዮ ቴሌኮም እና ዳሸን ባንክ የግለሰብ ደንበኛዉን የግል መረጃ ዕዳዉን በመሰብሰብ ሥራ ላይ ለሚሳተፍ ሦስተኛ ወገን (ድርጅት ወይም ግለሰብ) አሳልፈዉ መስጠት የሚችሉ መሆኑን ግለሰብ ደንበኛዉ ተስማምቷል፡፡
5.23. ከፍርድ ቤት ዉጭ ባለ አማራጭ ዕዳዉ የማይከፈል ከሆነ ኢትዮ ቴሌኮም እና ዳሽን ባንክ ጉዳዩን ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት በራሳቸዉ ወይም በሌላ የሕግ አገልግሎት ሰጪ ተቋም ወይም በግለሰብ ጠበቃ አማካኝነት የመውሰድና የመክሰስ ሙሉ መብት አላቸው፡፡
6. ተፈጻሚነት ያለው ህግ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕጎች፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች፣ እንዲሁም የዳሽን ባንክና የኢትዮ ቴሌኮም አግባብነት ያላቸው አሠራሮች በእነዚህ ደንብ እና ሁኔታዎች ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
7. መረጃ ስለመጠየቅ
ከቴሌብር መላ አገልግሎት፣ ሂደት፣ ደንብ እና ሁኔታዎች ጋር ለተያያዘ ማንኛውም ጥያቄ በቴሌብር የደንበኞች ግንኙነት ማእከል (127 በመደወል) ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
8. የውል መቋረጥ
ማንኛውንም የአነስተኛ ቁጠባ እና ብድር አገልግሎቶችን ያለቅድመ ማስጠንቀቂያ ወይም ያለማስታወቂያ በእርስዎ አላግባብ መጠቀም ወይም ማጭበርበር ምክንያት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ለማገድ ወይም ለማቋረጥ መብት ይኖረናል። የዚህ ውል መቋረጥ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የሁለቱም ተዋዋይ ወገኖች መብቶችን እና ግዴታዎችን ሊነካ አይችልም።


9. ቅሬታዎች
ቅሬታዎች በአካል፣ በጽሁፍ፣ በፖስታ፣ በፋክስ፣ በኢሜል ወይም በስልክ ሊቀርቡ ይችላሉ። ኢትዮ ቴሌኮም ቅሬታዎን በተገቢው ጊዜ ለመፍታት ሁሉንም እርምጃዎች ይወስዳል። በመልሱ ካልረኩ ጉዳዩን ወደ ዳሽን ባንክ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቅደም ተከተል መውሰድ ይችላሉ::
10. የግጭት አፈታት
ከዚህ ውል ጋር በተያያዘ የሚነሳ ማንኛውም አለመግባባት ከላይ በአንቀጽ 9 መሠረት ያልተፈታ እንደሆነ ስልጣን ላለው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፍርድ ቤት መቅረብ ይችላል።
11. የመያዝ መብት
እኛ ጋር ያለብወትን እዳ ካልከፈሉ በተለይም በጥሬ ገንዘብ፣ዕቃዎች፣ዋስትናዎች፣ውድ ጌጦች፣ቼኮች እና ማንኛውን ተንቀሳቃሽም ሆነ የማይነቀሳቀስ ንብረትዎ ላይ አጠቃላይ የመያዝ መብት ይኖረናል፡፡እኛ ጋር ያለቦትን እዳ መክፈል የማይችሉ ከሆነ እና የማቻቻል መብት ሲፈጠር በመያዣ መብት ስር የተያዙ ንብረቶችን ላልተከፈለው ብድር እንደ ዋስትና ተደርጎ መቁጠር ይቻላል፡፡

12. ዕዳ ስለማቻቻል
የወሰዱትን አነስተኛ ብድር መጠን እንዲከፍሉ ካሳወቅን በኋላ በተቀመጠለት ጊዜ ገደብ ውስጥ መመለስ ካልቻሉ ባንክ ውስጥ ካሉዎት ሌሎች የባንክ ተቀማጭ ጥሬ ገንዘብ፣ ቁጠባ፣ተርም ዲፖዚት፣የጋራ ወይም የተናጠል ከሆኑት ላይ ያለበዎትን ክሬዲት መጠን ያህል ለመውሰድ እንችላለለን ፡፡
13. ማስተባበል
የቴሌብር ሚስጥር ቁጥር (ፒን) በሚስጥር መቀመጥ አለበት ከእርስዎ ሌላ ለማንም ተደራሽ መሆን የለበትም። የሚስጥር ቁጥርዎን ሌላ ሶስተኛ ወገን እንዲያዉቀዉ በማድረግዎ ወይም በየጊዜው ባለመቀየርዎ፣ ያልተፈቀደ የቴሌብር አጠቃቀም በማከናወንዎ፣ የሞባይል ስልክዎ ወይም ሲም ካርድ ሲሰረቅብዎ ወይም ሲጠፋብዎ ለሚመለከተዉ አካል ፈጥነዉ ባለማሳቅዎ እና ባለመስዘጋትዎ የሚደርስብዎ ኪሳራ /ጉዳት የእርስዎ ኃላፊነት ብቻ ይሆናል፡፡