ወቢ ( አነስተኛ ብድር)

This credit service enables individual customers and Merchant/Agents to access micro credit service via their contact numbers. 

ይህ  ዉል  (ከዚህ በኋላ "ደንቦች እና ሁኔታዎች" እየተባለ የሚጠራው) የቴሌብር ወቢ የብድር አገልግሎት ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ  አጠቃላይ ደንብ እና ሁኔታዎች ያካትታል፡፡

እነዚህ ደንቦችና ሁኔታዎች እንዲሁም ከዚህ ጋር የተያያዙ ማሻሻያዎች እና ለውጦች የቴሌብር ወቢ አነስተኛ የብድር አገልግሎት በደንበኛዉ ተነበው ተቀባይነት ሲያገኙ (ይስማሙ የሚለውን ምርጫ ሲጫን)  በደንበኛው ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

  1. ትርጓሜ

በዚህ የደንቦች እና ሁኔታዎች መረጃ ውስጥ የተዘረዘሩ ቃላት የሚከተለውን ትርጉም ይይዛሉ፡-

  • "ሲንቄባንክ" ማለት  ቁጥጥር  የሚደረግበት የፋይናንስ  ተቋም  ሲሆን      ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር  በመተባበር  ለቴሌብር ደንበኞች  ወቢ  አነስተኛ  የብድር  አገልግሎት  ለመስጠት የተስማማ የፋይናንስ ተቋም  ነው።
  • "ኢትዮ ቴሌኮም" ማለት ክፍያ ለመፈፀም ፈቃድ ያለው እና  ሲንቄ ባንክ   ጋር  በመተባበር  ቴሌብር  ወቢ  አነስተኛ የብድር አገልግሎት  ለቴሌብር  ደንበኞች ለመስጠት  ስምምነት ያለው  ተቋም ነው፡፡
  • "የኢትዮጵያብሔራዊ ባንክ"  ማለት በአዋጅ ቁጥር 591/2001 መሠረት  ለፋይናንስ  ተቋማት ፍቃድ ለመሰጠትና ሥራቸዉን ለመቆጣጠር የተቋቋመ ተቋም ነው።
  • "ቴሌብር"ማለት ደንበኞች  የሞባይል ስልካቸዉን በመጠቀም የፋይናንስ አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚያስችል የኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት የንግድ ስም    ነው።
  • "የቴሌብርአካውንት" ማለት የቴሌብር ተጠቃሚ ደንበኞች  በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ገንዘብ የሚያስቀምጡበት፣ የሚላላኩበት እና የሚቀበሉበት  አካዉንት ነዉ ፡፡
  • "ወቢ አነስተኛ የብድር አገልግሎት" ማለት ሲንቄ ባንክና በኢትዮ ቴሌኮም የጋራ ትብብር ግለሰብ ደንበኞች በኤሌክትሮኒክ ገንዘብ አነስተኛ መጠን ያለው ብድር በቴሌብር የሚያገኙበት የአገልግሎት ዓይነት ነው።
  • “ወቢ የደሞዝ አነስተኛ የብድር አገልግሎት” ማለት ለግል እና ለመንግስት ተቋማት ሰራተኞች ከየተቋማቸዉ ጋር በሚኖር ስምምነት ከታች በተቀመጡ ደንብ እና ሁኔታዎች መሰረት በቴሌብር አማካኝነት  ሲንቄ ባንክ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር የሚያቀርበዉ የብድር አገልግሎት ነው፡፡
  • ግለሰብደንበኛ  ማለት  የተፈጥሮ  ሰዉ  ሆኖ  በስሙ የቴሌብር አካውንት ያለዉና  ቴሌብር  ወቢ አነስተኛ  የብድር አገልግሎት ለመዉሰድ የተስማማ ማለት ነው።
  • ኤሌክትሮኒክገንዘብ/ኢ- መኒ  ማለት ከ  ኢትዮጵያ ብር ጋር  እኩል መጠን ያለው ገንዘብን   የሚወክል ደንበኛው  የሚያስተዳድረዉ አና በደንበኛዉ የቴሌብር ሂሳብ  ዉስጥ የሚገኝ   የኤሌክትሮኒክስ  የገንዘብ ዋጋ ነው።
  • "አንተ"ወይም " የአንተ"  ማለት የግለሰብ ደንበኛ ማለት ሲሆን  የግለሰቡን  የግል ተወካዮችም ያጠቃልላል።
  • "እኛ" "አኛን"  እና "የእኛ"  ማለት የኢትዮጵያ ሲንቄ ባንክ እና ኢትዮ ቴሌኮም ማለት      ነው፡፡
  • የአገልግሎት ክፍያ ማለት ወቢ አነስተኛ የብድር  አገልግሎትን ለመጠቀም በግለሰብ  ደንበኞች  የሚፈፀም  ክፍያ   ነው ::የዚህ  ክፍያ መጠን  በኢትዮ  ቴሌኮም  እና  ሲንቄ ባንክ  ውሳኔ በማንኛውም  ጊዜ  አስቀድሞ በሚሰጥ ማሳሰቢያ ሊቀየር ይችላል።
  • ”ዕለታዊ ክፍያማለት ሳይከፈል በቀረዉ የዕዳ መጠን ላይ ግለሰብ ደንበኛዉ በወሰደዉ የብድር ዓየነት መሠረት በየዕለቱ የሚከፈል የክፍያ ዓይነት ነዉ ፡፡
  • "የቅጣት ክፍያ" ማለት የብድሩ ግለሰብ ደንበኛዉ በገባዉ ዉል መሠረት የብድሩን ገንዘብ ሳይከፍል የቀረ እንደሆን የሚከፍለዉ ገንዘብ ነዉ ፡፡
  • "የክፍያ ቀን " ማለት  ግለሰብ  ደንበኛዉ የወሰደዉን ብድር ከፍሎ እንዲያጠናቅቅ የሚጠበቅበት የመጨረሻዉ ቀን ነወ ፡፡
  • "የተበላሸብድር"  ማለት ከክፍያ ቀን ማግስት ጀምሮ በሚቆጠር 90 ቀናት ዉስጥ ያልተከፈለ  ዕዳ  ነዉ፡፡
  • በአነስታይ ፆታ የተገለፁ ለተባዕታይ ፆታ እንደዚሁም በተባዕታይ ፆታም የተገለፁ ለአነስታይ ፆታ ያገለግላሉ
  • ግለሰብ የሚለዉ ቃል ወንድና ሴት ፆታን ለመግለፅ ያገለግላል ፡፡

 

 

 

 

  1. ደንብእና ሁኔታዎችን ስለመቀበል
    • ወቢ የብድር አገልግሎትን ለመጠቀም ከማመልከትዎ በፊት እነዚህ ደንብ እና ሁኔታዎች ላይ የተጠቀሰውን የ ብድሩን አጠቃቀም እና መመሪያ በጥንቃቄ በማንበብ እና በመረዳት መስማማት ይኖርቦታል፡፡
    • በእነዚህ ደንቦችና ሁኔታዎች ካልተስማሙ እባክዎን ከዝርዝር መምረጫ ውስጥ ሰርዝ የሚለውን ይጫኑ፤
    • ደንቦችና ሁኔታዎችን እንዳነበቡ፣ እንደተረዱና እንደተቀበሉ የሚቆጠረው፡-

ይስማሙ” የሚለውን አማራጭ ሲጫኑ ደንብ እና ሁኔታዎችን በማንበብ ተረድተው ለማክበር መስማማትዎን እንዳረጋግጡ ወይም ብድር ክፍያን ለመጠቀም እንደተስማሙ ይወሰዳል።

  • ወቢ አነሰተኛ የብድር አገልግሎትን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ለመተግበር እና የክሬዲት አገልግሎትን በኤሌክትሮኒካዊ መንገድ ብቻ በቴሌብር ሲስተም ለመጠቀም ተስማምተዋል።
  • ደንብ እና ሁኔታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በኢትዮ ቴሌኮም እና ሲንቄ ባንክ ሊሻሻሉ ወይም ሊለወጡ የሚችሉ ሲሆንይህንንም ለዉጥ የሚያስገነዝብ ማሳሰቢያ አስቀድሞ እንዲደርስዎት ይደረጋል ፡፡ እነዚህ ለዉጦች   በቴሌብር ፖርታል፣በቴሌብር መተግበሪያ ወይም ድረ ገጽ ላይ ከተለቀቁበት ዕለት ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡
  • ደንበኛው ገንዘቡን ለህጋዊ አላማ ለማዋል ተስማምተዋል።
  1. የብድር አገልግሎትን ለማስጀመር

የብድር አገልግሎትን ከኢትዮ ቴሌኮም እና ሲንቄ ባንክ ጋር ለማስጀመር ቢያንስ፡-

  • እነዚህን ደንቦችና ሁኔታዎችን ሊያነቡ፣ሊረዱ እና ሊስማሙ ይገባል
  • 18 አመት እና ከዚያ በላይ መሆን
  • አገልግሎት የሚሰጥ የኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርድ መያዝ
  • የቴሌብር እና የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቶችን እንደ ዳታ/ድምጽ/አጭር የጽሁፍ መልዕክት የሚጠቀሙ መሆን አለብዎት
  • የቴሌብር የደንበኝነት ቆይታ 3 ወር እና ከዛ በላይ መሆን አለበት

ለመመዝገብ በዩ ኤስ ኤስ ዲ (*127#) ወይም በቴሌብር መተግበሪያ መጠቀም ይችላሉ፡፡

  1. ወቢ አነሰተኛ ብድር ለማግኘት መሰረታዊ መስፈርቶች፤
  • የግለሰብ ደንበኛው የመበደር አቅም፣ ደንበኛው የብድር ክፍያ አገልግሎት ለመጠቀም ጥያቄ ካቀረበበት ቀን በፊት ባደረገው የ6 ወር የቴሌብር የገንዘብ እንቅስቃሴ፣ቀደም ሲል የወሰደዉን ብድር የመክፈል ታሪክ   እና በቴሌኮም አገልግሎት አጠቃቀም ይወሰናል። ከታች ያሉት የቴሌብር ግብይቶች እና የገንዘብ ልውውጥ የደንበኛ የብደር አቅምን ለማስላት ይውላሉ።
    • የአየር ሰዓት መሙላት ወይም ጥቅል መግዛት (በራስ አገዝ ወይመ ከወኪሎች)፣
    • ዕቃ ወይም አገልግሎት በመግዛት ግብይት መፈጸም፣
    • ቢል ክፍያ (በራስ አገዝ ወይም ከወኪሎች)፣
    • ለእርስዎ ወይም የሌላ ደንበኛ የፍጆታ አገልግሎት ክፍያ (በራስ አገዝ ወይም ከወኪሎች)፣
    • በልክ ዲስፐርስመንት ( የቀን ሠራተኞች ክፍያ ፣ደመወዝ ፣ዕርዳታ፣ጡረታ፣…) ክፍያ በቴሌብር መቀበል፣
    • ከውጭ አገር ገንዘብ መቀበል፣
    • የትኬት ግዢ፣
    • ለገንዘብ ማሰባሰቢያ የእርዳታ ክፍያ( ፈንድ ረይዚንግ)፣
    • በቴሌብር ወኪሎች በኩል ገንዘብ መቀበልና ወጪ ማድረግ፣
    • የቁጠባ አገልግሎት፣
    • ገንዘብ መላክ፣
    • የቴሌኮም ፍጆታ (ድምጽ፣ ዳታ ወይም መልዕክት)፣
    • በቴሌብር የተወሰደን ብድር በአግባቡ የመክፈል የቀደመ ታሪክ ፡፡
  • ብቁ ለመሆን ደንበኞች ከቴሌኮም አገልግሎት ፍጆታ በተጨማሪ የቴሌብር አገልግሎት መጠቀም አለባቸው፡፡
  • ወቢ የደሞዝ ብድር ለማግኘት ወርሃዊ ደሞዝን በቴሌብር አማካኝነት መቀበል ወይም ከሚሰራበት ተቋም ጋር የሚደረግ  ስምምነት በቂ ነዉ፡፡
  1. የብድሩ መጠን እና ክፍያ
    • በሚፈቀደው ዝቅተኛ እና ከፍተኛ የብድር መጠን መካከል ማንኛውንም መጠን መበደር ይችላሉ።
    • የጠየቁትን የብድር መጠን እንዳገኙ የቴሌብር ሂሳብዎ (ኤሌክትሮኒክ-ገንዘብ አካውንት) ላይ ገቢ ይደረጋል።
    • ሌላብድር ለማግኘት መጀመሪያ ከቴሌብር የወሰዱትን ብድር መክፈል ይጠበቅብዎታል፡፡
    • ያለብዎትን ብድር በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውሰጥ በከፊል ወይም በሙሉ መክፈል ይችላሉ፡፡
    • እንደየ ብድሩ ዐዓይነት የብድር መከክፈያ ቀነ ገደብ 5 ቀን ፣ 10 ቀን፣ 30 ቀን 45 እና 14 ወር ነዉ፡፡
    • ለ5 ቀናት፣ ለ10 ቀናት፣ ለ30 ቀናት እና ለ45 ቀናት ከፍተኛው የብድር መጠን እንደ ቅደም ተከተላቸው 5,000 ብር፣ 6,000 ብር፣ 15,000 ብር እና 30,000 ብር ነው። ከላይ ለተጠቀሱት የክሬዲት ቀናት ዝቅተኛው የብድር መጠን በቅደም ተከተላቸው 100 ብር፣ 100 ብር፣ 200 ብር እና 5,000 ብር ነው።
    • ያለብዎትን የአምስት ቀን ወቢ ብድር በ5 ቀናት ውስጥ ከከፈሉ በመጀመሪያዉ ቀን የዋናዉን ዕዳ 5% የአገልግሎት ክፍያ እና ከሁለተኛው ቀን ጀምሮ የክሬዲት መጠነዎን መሰረት ያደረገ በቀን የዋናዉን ዕዳ  ከ0.35% እስከ 1.2% ክፍያ ይከፍላሉ፡፡
    • ያለብዎትን የአስር ቀን የወቢ ብድር በ10 ቀናት ውስጥ ከከፈሉ የወሰዱትን የብድር መጠን 2%በመጀመሪያዉ ቀን የሚከፍሉ  ሲሆን ከዚያ በኋላ ሲከፍሉ የክሬዲት መጠነዎን መሰረት ያደረገ በቀን ከ 3% እስከ 0.9% ተጨማሪ የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላሉ፡፡
    • ያለብዎትን የሰላሳ ቀን የወቢ ብድር በ30 ቀናት ውስጥ ከከፈሉ የወሰዱትን የብድር መጠን 4%በመጀመሪያዉ ቀን የሚከፍሉ  ሲሆን ከዚያ በኋላ ሲከፍሉ የክሬዲት መጠነዎን መሰረት ያደረገ በቀን ከ3% እስከ 1% ተጨማሪ የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላሉ፡፡
    • ያለብዎትን የአርባ አምስት ቀን የወቢ ብድር በ45 ቀናት ውስጥ በትክክል ከከፈሉ  የአገልግሎት ክፍያ  የወሰዱትን የብድር መጠን5% የሚከፍሉ  ሲሆን ከዚያ በኋላ ሲከፍሉ የክሬዲት መጠነዎን መሰረት ያደረገ በቀን ከ0.5% እስከ 0.67% ተጨማሪ የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላሉ፡፡
    • ለወቢ ደመዎዝ የብድር ክፍያዉ በወሰዱት የብድር ጊዜ ተከፋፍሎ ቀስ በቀስ ይከፈላል ፡፡
    • የመክፈያ ጊዜዉ 14 ወር ለሆነ የ5 ወር ደመወዝ የወቢ ደመዎዝ ብድር 19.5% የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላሉ ፡፡
    • ያለብዎትን ዕዳ በቀነ ገደቡ ውስጥ የማይከፍሉ ከሆነ ባለበዎት ክሬዲት መጠን ላይ በየዕለቱ የሚሰላ11% የቅጣት ክፍያ እስከ ሚከፍሉ ድረስ 90 ቀናት ይከፍላሉ፡፡
    • ብደሩን የመክፈያ ቀነ ገደብ ባለፈ 90 ቀናት ዉስጥ ግለሰብ ደንበኛዉ የማይከፍል ከሆነ ሳይከፈል የቀረዉ ዕዳ ወቢ የቁጠባ ሂሳቡ በቀጥታ ተቆራጭ ይደረጋል፣
    • በጉርሻ የሚያገኙት ገንዘብ ለክሬዲት ክፍያ አይውልም፡፡
    • ብድሩ መከፈል ባለበት ጊዜ ሳይከፈል የቀረ እንደሆነ ኢትዮ ቴሌኮም እና ሲንቄ ባንክ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከባለዕዳዉ የሲንቄ ባንክ ወይም ሌሎች ባንኮች ሒሳብ በቀጥታ መቁረጥን ጨምሮ ማናቸዉም አማራጭ ዜዴዎች በመጠቀም ከፍርድ ቤት ዉጭ ባለ አማራጭ ዕዳዉን መሰብሰብ ይችላሉ፡፡
    • የመክፈያ ጊዜው ካለፈ በኋላ ግለሰብ ደንበኛዉ በሰዓቱ ካልከፈለ ኢትዮ ቴሌኮም እና ሲንቄ  ባንክ የቀረውን የብድር መጠን ከቴሌብር ሂሳቡ ወዲያውኑ ተቀናሽ ያደርጋሉ ፡፡
    • ከፍርድ ቤት ዉጭ ባለ አማራጭ ዕዳዉን ለመሰብሰብ  ያግዝ ዘንድ ኢትዮ ቴሌኮም እና ሲንቄ  ባንክ የግለሰብ ደንበኛዉን  የመኖሪያ ወይም የሥራ አድራሻ ማናቸዉም አማራጭ ዘዴዎች በመጠቀም አፈላልገዉ በማግኘት  ዕዳዉን የመሰብሰብ መብት ያላቸዉ መሆኑን ግለሰብ ደንበኛዉ ተስማምቷል፡፡
    • ዕዳዉ መከፈል ባለበት ጊዜ ሳይከፍል የቀረ እንደሆነ ኢትዮ ቴሌኮም እና ሲንቄ ባንክ የግለሰብ ደንበኛዉን የግል መረጃ ዕዳዉን በመሰብሰብ ሥራ ላይ ለሚሳተፍ ሦስተኛ ወገን (ድርጅት ወይም ግለሰብ) አሳልፈዉ መስጠት  የሚችሉ  መሆኑን ግለሰብ ደንበኛዉ ተስማምቷል፡፡
    • ከፍርድ ቤት ዉጭ ባለ አማራጭ ዕዳዉ የማይከፈል ከሆነ ኢትዮ ቴሌኮም እና ሲንቄ ባንክ ጉዳዩን ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት በራሳቸዉ ወይም በሌላ የሕግ አገልግሎት ሰጪ ተቋም ወይም በግለሰብ ጠበቃ አማካኝነት የመውሰድና የመክሰስ ሙሉ መብት አላቸው፡፡
  2. ተፈጻሚነት ያለው ህግ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕጎች፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች፣ እንዲሁም የሲንቄ ባንክና የኢትዮ ቴሌኮም አግባብነት ያላቸው አሠራሮች በእነዚህ ደንብ እና ሁኔታዎች ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡

  1. መረጃ ስለመጠየቅ

ስለ ወቢ አገልግሎት፣ ሂደት፣ ደንብ  እና ሁኔታዎች ጋር  ለተያያዘ  ማንኛውም   ጥያቄ    በቴሌብር የደንበኞች  ግንኙነት  ማእከል (127 በመደወል), ወደ 126 አጭር ጽሁፍ በመላክ፣ በሶሻል ሚዲያ (https://telehub.ethiotelecom.et/) ተጨማሪ  መረጃ ማግኘት  ይችላሉ።

  1. የውልመቋረጥ

ማንኛውንም የአነስተኛ ቁጠባ እና ብድር አገልግሎቶችን ያለቅድመ  ማስጠንቀቂያ ወይም ያለማስታወቂያ በእርስዎ  አላግባብ  መጠቀም  ወይም  ማጭበርበር  ምክንያት ሙሉ  በሙሉ  ወይም በከፊል  ለማገድ ወይም ለማቋረጥ መብት ይኖረናል። የዚህ ውል መቋረጥ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የሁለቱም ተዋዋይ ወገኖች መብቶችን እና ግዴታዎችን ሊነካ አይችልም።

  1. ቅሬታዎች

ቅሬታዎች በአካል፣ በጽሁፍ፣ በፖስታ፣ በፋክስ፣ በኢሜል ወይም በስልክ ሊቀርቡ ይችላሉ።              ኢትዮ ቴሌኮም ቅሬታዎን በተገቢው ጊዜ ለመፍታት ሁሉንም እርምጃዎች ይወስዳል። በመልሱ  ካልረኩ ጉዳዩን ወደ ሲንቄ  ባንክ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቅደም ተከተል  መውሰድ ይችላሉ::

  1. የግጭት አፈታት

ከዚህ ውል ጋር በተያያዘ የሚነሳ ማንኛውም አለመግባባት ከላይ በአንቀጽ 9 መሠረት ያልተፈታ እንደሆነ ስልጣን ላለው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፍርድ ቤት መቅረብ ይችላል።

  1. የመያዝ መብት

እኛ ጋር ያለብወትን እዳ ካልከፈሉ በተለይም በጥሬ ገንዘብ፣ዕቃዎች፣ዋስትናዎች፣ውድ ጌጦች፣ቼኮች እና ማንኛውን ተንቀሳቃሽም ሆነ የማይነቀሳቀስ ንብረትዎ ላይ አጠቃላይ የመያዝ መብት  ይኖረናል፡፡እኛ ጋር ያለቦትን እዳ  መክፈል የማይችሉ ከሆነ እና የማቻቻል መብት  ሲፈጠር  በመያዣ መብት ስር የተያዙ ንብረቶችን ላልተከፈለው ብድር  እንደ ዋስትና ተደርጎ መቁጠር ይቻላል፡፡

 

  1. ዕዳ ስለማቻቻል

የወሰዱትን አነስተኛ  ብድር  መመጠን እንዲከፍሉ ካሳወቅን በኋላ በተቀመጠለት ጊዜ ገደብ ውስጥ መመለስ  ካልቻሉ ባንክ ውስጥ ካሉዎት ሌሎች የባንክ ተቀማጭ ጥሬ ገንዘብ፣ ቁጠባ፣ተርም ዲፖዚት፣የጋራ ወይም የተናጠል ከሆኑ ላይ  ያለበዎትን ክሬዲት መጠን ያህል ለመውሰድ እንችላለለን ፡፡

  1. ማስተባበል

የቴሌብር  ሚስጥር  ቁጥር (ፒን)  በሚስጥር  መቀመጥ  አለበት ከእርስዎ ሌላ ለማንም ተደራሽ መሆን የለበትም። የሚስጥር   ቁጥርዎን  ሌላ  ሶስተኛ  ወገን  እንዲያዉቀዉ በማድረግዎ  ወይም  በየጊዜው    ባለመቀየርዎ፣ ያልተፈቀደ   የቴሌብር   አጠቃቀም በማከናወንዎ፣ የሞባይል ስልክዎ ወይም ሲም  ካርድ  ሲሰረቅብዎ   ወይም ሲጠፋብዎ ለሚመለከተዉ  አካል  ፈጥነዉ ባለማሳቅዎ እና ባለመስዘጋትዎ     የሚደርስብዎ  ኪሳራ /ጉዳት የእርስዎ ኃላፊነት ብቻ ይሆናል፡፡