ይህ የአገልግሎት አይነት ለግለሰብ እና ለነጋዴዎች/ወኪሎች አነስተኛ ንግድ/ቢዝነስ እንዲጀምሩ ወይም እንዲያስፋፉ በኤሌክትሮኒክ ገንዘብ አነስተኛ መጠን ያለው ክሬዲት የሚያገኙበት የአገልግሎት አይነት ነው።
መላ ሳምንታዊ እና ወርሃዊ
የብድር ዓይነት
| የብድር ዓይነት | ትንሹ የብድር መጠን | ትልቁ የብድር መጠን | የመክፈያ ጊዜ | የአገልግለት ክፍያ | የቀን ክፊያ | ቅጣት |
|---|---|---|---|---|---|---|
| መላ ዕለታዊ | 100 | 2,000 | 1 ቀን | 1% | 2% | |
| መላ ሳምንታዊ | 100 | 5,000 | 7 ቀናት | 1% | 0.35% እስከ 1.2% | 2% |
| ማስታወሻ: ሁሉም የገንዘብ መጠኖች በብር የተቀመጡ ናቸው፡፡ |
ወርኃዊ መላ
| የክሬዲት መጠን | ታሪፍ | ||
|---|---|---|---|
| የአገልግሎት ክፍያ | ዕለታዊ ክፍያ | ቅጣት | |
| 600 | 3% | 0.80% | 0.11% |
| 800 | 0.75% | ||
| 1,400 | 0.70% | ||
| 3,000 | 0.67% | ||
| 6,000 | 0.62% | ||
| 8,000 | 0.58% | ||
| 10,000 | 0.50% | ||
| 12,000 | 0.30% | ||
| ማስታወሻ: ሁሉም የገንዘብ መጠኖች በብር የተቀመጡ ናቸው፡፡ |
የ50 ቀናት መላ
| የክሬዲት መጠን | ታሪፍ | ||
|---|---|---|---|
| የአገልግሎት ክፍያ | ዕለታዊ ክፍያ | ቅጣት | |
| 3000 | 6% | 0.70% | 0.11% |
| 5,000 | 0.66% | ||
| 7,000 | 0.62% | ||
| 9,000 | 0.59% | ||
| 11,000 | 0.56% | ||
| 13,000 | 0.53% | ||
| 15,000 | 0.50% | ||
| 18,000 | 0.50% | ||
| ማስታወሻ: ሁሉም የገንዘብ መጠኖች በብር የተቀመጡ ናቸው፡፡ |
| የብድር ;አይነት | ትንሹ የብድር መጠን | ትልቁ የብድር መጠን | የመክፈያ ጊዜ | የአገልግሎት ክፍያ | ቅጣት |
|---|---|---|---|---|---|
| መላ እለታዊ | 100 | 2,000 | 1 day | 1% | 2% |
| መላ ሳምንታዊ | 5,000 | 7 Days | 1% | 0.50% | |
| መላ ወርሃዊ | 10,000 | 1 Month | 3% |
ለመላ ክሬዲት ተለዋዋጭ ዋጋ
|  ሳምንታዊ | ወርሃዊ | |||||||||
| የብድር መጠን | አገልግሎቱን ለማግኘት የሚከፈል | እለታዊ ክፍያ | እለታዊ የቅጣት ክፍያ | የብድር መጠን | አገልግሎቱን ለማግኘት የሚከፈል | እለታዊ ክፍያ | እለታዊ የቅጣት ክፍያ | |||
| ትንሹ | የመጨረሻው | ትንሹ | የመጨረሻው | |||||||
| 100 | 5000 | 1% | 0.35% | 0.50% | 100 | 10000 | 3% | 0.35% | 0.50% | |
| 4000 | 0.40% | 8000 | 0.40% | |||||||
| 3000 | 0.85% | 6000 | 0.65% | |||||||
| 2000 | 1.05% | 2500 | 0.85% | |||||||
| 1000 | 1.10% | 1000 | 1.05% | |||||||
| 100 | 1.20% | 200 | 1.20% | |||||||
መዳረሻ
መዳረሻ የቴሌብር መላ አገልግሎት አንዱ አካል ሲሆን በቴሌብር ደሞዛቸውን ለሚቀበሉ የመንግስት እና የግል ሰራተኞች ክሬዲት እንዲያገኙ የሚያስችል አገልግሎት ነው፡፡
|
መላ መዳረሻ |
|||
|
ምርት |
ዝቅተኛ |
ከፍተኛ |
የአገልግሎት ክፍያ |
|
የክሬዲት መጠን |
1000 |
36000 |
|
|
የመመለሻ ቀነ ገደብ |
90 ቀናት ወይም 3 ወር |
|
|
|
የብድር መክፈያ ጊዜ |
በየወሩ |
|
|
|
ከመመለሻ ቀነ ገደብ ወይም ከ90 ቀናት በኋላ |
|
0.5% በቀን |
|
ማስታወሻ፡–
- የብድር ገደብ ከብር 1,000 እስከ 36,000 ነው።
- የመመለሻ ቀነ ገደብ ከ90 ቀናት በኋላ ይሆናል….
መላ መዳረሻ በቴሌብር መተግበሪያ አገልግሎት ለመጠቀም
- የፋይናንስ አገልግሎትን ይምረጡ
- ቴሌብር መላን ይምረጡ
- መላ መዳረሻን ይምረጡ
- ክሬዲት ገደብዎን ይመልከቱ
- ክሬዲት ይጠይቁ የሚለውን
- የብር መጠን አስገብተው ይመልከቱ የሚለውን ይጫኑ
- ለመጨረስ ያረጋግጡ የሚለውን ይጫኑ
በአጭር ቁጥር *127# በመደወል
- *127# ይደውሉ
- ለፋይናንሽያል አገልግሎት 1ን ያስገቡ
- ለቴሌብር መላ 1ን ያስገቡ
- ክሬዲት ለመውሰድ 1ን ይምረጡ
- ወደ ቀጣይ ማውጫ ለመሄድ (#) ን ቀጥሎ መዳረሻ 3 ወርን ለመምረጥ 4ን ያስገቡ
- በቀጣይ ማውጫ (#) የሚፈልጉትን የክሬዲት መጠን ያስገቡ
- ለማረጋገጥ 1ን ያስገቡ
- የመዳረሻ ክሬዲት አገልግሎትን ለማግኘት ሰራተኞች በቅድሚያ የውል ስምምነት መፈጸም ይገባቸዋል፡፡
- ሰራተኞች በ90 ቀናት ውስጥ ብድሩን ከመለሱ የአገልግሎት ክፍያው 10% ይሆናል።
- ከብድር መክፈያ ቀነ ገደቡ በኋላ ተበዳሪዎች በቀን5% ከጠቅላላው ቀሪ ክፍያ እንዲከፍሉ ይደረጋል።
- ደመወዛቸው በቴሌብር ገቢ ሲደረግ የተመላሽ ክፍያው ወዲያውኑ ተቀናሽ/ተፈጻሚ ይሆናል።
- ሰራተኞች የደሞዛቸውን 30% መበደር ይችላሉ።
- ከፋይ/ቀጣሪ ድርጅቱ እና እና ሰራተኞች ደሞዛቸውን በቴሌብር ለመቀበል የሚያስችል ስምምት ማድረግ ይገባቸዋል፡፡
- የመዳረሻ ብድር አገልግሎትን ለማግኘት ሰራተኞች 3 ጊዜ (ወራት) ደሞዛቸውን በቴሌብር መቀበል ይጠበቅባቸዋል።
- የኮንትራት ውሉ ሲፈረም የደመወዛቸውን 30% በክሬዲት እንዲወስዱ የሚያስችል ይሆናል።
- ክሬዲቱ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የሚከፈል ይሆናል፡፡
- ቀጣሪ ድርጅቱ/ኩባንያው የሰራተኞቹ የደሞዝ ክፍያ በቴሌብር መክፈሉን እንደሚቀጥል በማረጋገጥ እንንሁም ኮንትራቱን ሲያቋርጥ ከአንድ ወር በፊት ለኢትዮ ቴሌኮም ማሳወቅ አለበት።
የቴሌብር መላ አገልግሎት ለማግኘት ብቁ የሚያደርጉ መስፈርቶች
- የደንበኛ የመበደር አቅም ደንበኛው ባደረገው የ6 ወር የቴሌብር የገንዘብ እንቅስቃሴ እና በቴሌኮም አጠቃቀም ይወሰናል።
- በተጨማሪም ከታች ያሉት የቴሌብር ግብይቶች እና የገንዘብ ልውውጥ የደንበኛ የብድር አቅምን ለማስላት የሚውሉ ይሆናል።
- ለእርስዎ ወይም በስጦታ የአየር ሰዓት መሙላት ወይም ጥቅል
መግዛት (በራስ አገዝ ወይም ከወኪሎች) - ዕቃ ወይም አገልግሎት ግዢን መፈጸም
- ለእርስዎ ወይም የሌላ ደንበኛ ቢል ክፍያ (በራስ አገዝ ወይም
ከወኪሎች) ማከናወን - ለእርስዎ ወይም የሌላ ደንበኛን የፍጆታ አገልግሎት ክፍያ (በራስ አገዝ ወይም ከወኪሎች) መፈፀም
- ከውጭ አገር ገንዘብ መቀበል
- የጅምላ ክፍያ (ደሞዝ፣ ሴፍቲኔት…) መፈፀም
- የትኬት ክፍያ መፈፀም
- ለገንዘብ ማሰባሰቢያ የእርዳታ ክፍያ መፈፀም
- የቁጠባ አገልግሎት
- የቴሌኮም ፍጆታ (ድምጽ፣ ዳታ ወይም መልዕክት) መፈፀም
- ለእርስዎ ወይም በስጦታ የአየር ሰዓት መሙላት ወይም ጥቅል
• ከቴሌኮም አገልግሎት ፍጆታ በተጨማሪ ቢያንስ አንድ የቴሌብር አገልግሎት መጠቀም ይኖርብዎታል፡፡
• የ6 ወራት ግብይት ወይም አጠቃቀም ለብቁነት መስፈርት የሚቆጠር ይሆናል።
• በሚፈቀደው ዝቅተኛ እና ከፍተኛ የክሬዲት መጠን መካከል ማንኛውንም መጠን መበደር ይችላሉ።
የቴሌብር መላ አገልግሎት ለማግኘት ብቁ የሚያደርጉ መስፈርቶች
- 18 አመት እና ከዚያ በላይ
- አገልግሎት የሚሰጥ የኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርድ መያዝ
- የቴሌብር እና የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቶችን እንደ ዳታ/ድምጽ/አጭር የጽሁፍ መልዕክት መጠቀም ይኖርብዎታል፡፡
- ለመመዝገብ በአጭር ቁጥር (*127#) ወይም በቴሌብር መተግበሪያን ይጠቀሙ፡፡
- የቴሌብር የደንበኝነት ቆይታ 3 ወር እና ከዛ በላይ መሆን ይኖርበታል፡፡
በቴሌብር
የሞባይል መተግበሪያ
እንዴት አገልግሎቱን ማስጀመር እና መጠቀም እችላለሁ?
አገልግሎቱን ለማስጀመር
- የፋይናንስ አገልግሎት የሚለውን ይጫኑ
- ቴሌብር መላ የሚለውን ይምረጡ _ ደንብ እና ሁኔታዎችን በማንበብ የ √ ምልክት በመጫን መስማማትዎን ይግለጹ
- ለማስጀመር የሚለውን ይጫኑ
ክሬዲት ለመውሰድ
- ቴሌብር መላ ከሚለው ስር የሚፈልጉትን ኮንትራት ይምረጡ
- የክሬዲት ገደብዎን እና የክሬዲቱን ዝርዝር ደንቦች ይመልከቱ
- ክሬዲት ይጠይቁ የሚለውን ይምረጡ
- የክሬዲት መጠን ያስገቡ
- ይመልከቱ የሚለውን ይጫኑ
- ያረጋግጡ የሚለውን በመጫን ይጨርሱ
ክሬዲት ለመክፈል
- ቴሌብር መላ ከሚለው ስር የእኔ ቴሌብር መላ የሚለውን ይምረጡ
- የሚከፍሉትን ኮንትራት ይምረጡ
- በውል ዝርዝር ስር ይክፈሉ የሚለውን ይጫኑ
- የሚከፍሉትን የብር መጠን ያስገቡ (በሙሉ ወይም በከፊል)
- ያረጋግጡ የሚለውን በመጫን ይጨርሱ
- ለአገልግሎቱ ብቁ የሚያደርጉ መስፈርቶች
ለግለሰብ ደንበኞች
- 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ ዕድሜ፣
- ደንበኛው በስድስት ወራት ውስጥ ያከናወናቸው ግብይቶች ማለትም
- የአየር ሰዓት እና ጥቅል መግዛት፣
- የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቶች (ድምጽ፣ አጭር ጽሁፍ እና ዳታ) አጠቃቀም፣
- የኢትዮ ቴሌኮም ኔትዎርክ የቆይታ ጊዜ፣
- ምርቶችንና አገልግሎትን መግዛት፣ ወርሃዊ የአገልግሎት ክፍያዎችን መፈጸም፣
- የገቢ ማሰባሰቢያ ክፍያ፣
- ገንዘብ ለመላክ፣
- ገንዘብ ተቀማጭ ማድረግ፣
- ገንዘብ ወጪ ማድረግ፣
- ከውጭ ሃገር ገንዘብ መቀበል፣
- በአንዴ ብዙ ክፍያዎን መፈጸም (ደመወዝ፣ ሴፍቲኔት..)፣
- ትኬት መግዛት፣
- ከዚህ በፊት የነበር የብድር ታሪክ፣ ወዘተ ግምት ውስጥ የሚገቡ ይሆናል፡፡
- ደንበኛው ከዚህ በፊት የወሰደውን አነስተኛ ብድር ካልመለስ መበደር አይችልም፡፡
- የአነስተኛ ብድር፣ የአየር ሰዓት ብድር እና የኢትዮ ቴል አገልግሎት ብድር ያለበት ደንበኛ ለአስተኛ ብድር አገልግሎት ብቁ አይሆንም፡፡
ለነጋዴዎች ወይም ወኪሎች
ሀ. ወኪል
- ወኪሉ ለብድር አገልግሎቱ ተጨማሪ የውል ስምምነት መፈጸም ይኖርበታል፣
- ወኪሉ ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ በቴሌብር ጥሩ የስራ እንቅስቃሴ ያለው፣
- በተጨማሪም የጥቅል ሽያጭ፣ ወርሃዊ የአገልግሎት ክፍያ መፈጸም፣ ገንዘብ ወጪ ማድረግ፣ የአየር ሰዓት መሙላት፣ ለቴሌብር አገልግሎት የተመዘገቡ ደንበኞች ብዛት እና የደንበኝነት ደረጃ ማሳደግ፣ የብድር መመለስ ሁኔታ ግምት ውስጥ የሚገቡ ይሆናል፡፡
ለ. ነጋዴ
- ለብድር አገልግሎቱ ተጨማሪ የውል ስምምነት መፈጸም እንዲሁም የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ።
- ነጋዴው ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ በቴሌብር ጥሩ የስራ እንቅስቃሴ ያለው እንዲሁም በቴሌብር ክፍያዎችን የተቀበለ፣ በቴሌብር ምርትና አገልግሎቶችን የሸጠ፣ የአየር ሰዓት የሞላ መሆን ይገባዋል፡፡
- በተጨማሪም የወሰዱትን ብድር በቶሎ መመለስ በድጋሚ ለመበደር ያስችላል፡፡
ዉል
I.ይህ ዉል (ከዚህ በኋላ "ደንቦች እና ሁኔታዎች" እየተባለ የሚጠራው) የቴሌብር መላ የብድር አገልግሎት ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ አጠቃላይ ደንብ እና ሁኔታዎች ያካትታል፡፡
IIእነዚህ ደንቦችና ሁኔታዎች እንዲሁም ከዚህ ጋር የተያያዙ ማሻሻያዎች እና ለውጦች የቴሌብር መላ አነስተኛ የብድር አገልግሎት በግለሰብ ደንበኛዉ ተነበው ተቀባይነት ሲያገኙ ("ለማስጀመር " የሚለውን ምርጫ ሲጫን) በደንበኛው ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
- ትርጓሜ
በዚህ ደንቦች እና ሁኔታዎች ውስጥ የተዘረዘሩ ቃላት የሚከተለውን ትርጉም ይይዛሉ፡-
- "ዳሽንባንክ" ማለት ቁጥጥር የሚደረግበት የፋይናንስ ተቋም ሲሆን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ለቴሌብር ደንበኞች መላ አነስተኛ የብድር አገልግሎት ለመስጠት የተስማማ የፋይናንስ ተቋም ነው።
- "ኢትዮቴሌኮም" ማለት የክፍያ መፈጸምያ ሰነድ አዉጭነት ፍቃድ ያለው እና ዳሽን ባንክ ለሚሰጠዉ መላ አነስተኛ የብድር አገልግሎት ሥራ ለማመቻቸት ከዳሽን ስምምነት ያለው ተቋም ነው፡፡
- "የኢትዮጵያብሔራዊ ባንክ" ማለት በአዋጅ ቁጥር. 718/2003 (1282/2015 እንደተሻሻለዉ) መሠረት ለፋይናንስ ተቋማት ፍቃድ ለመሰጠትና ሥራቸዉን ለመቆጣጠር ሥልጣን ያለዉ ተቋም ነው።
- "ቴሌብር” ማለት ደንበኞች የሞባይል ስልካቸዉን በመጠቀም የፋይናንስ አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚያስችል የኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት የንግድ ስም ነው።
- "የቴሌብር አካውንት" ማለት የቴሌብር ተጠቃሚ ደንበኞች በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ገንዘብ የሚያስቀምጡበት፣ የሚላላኩበት እና የሚቀበሉበት አካዉንት ነዉ፡፡
- "መላ አነስተኛ የብድር አገልግሎት" ማለት በዳሽን ባንክና በኢትዮ ቴሌኮም የጋራ ትብብር ግለሰብ ደንበኞች በኤሌክትሮኒክ ገንዘብ አነስተኛ መጠን ያለው ብድር በቴሌብር አማካኝነት የሚያገኙበት የአገልግሎት ዓይነት ነው።
- “መላ መዳረሻ አነስተኛ የብድር አገልግሎት” ማለት ለግል እና ለመንግስት ተቋማት ሰራተኞች ከየተቋማቸዉ ጋር በሚደረግ ስምምነት በዚህ ደንብ እና ሁኔታዎች መሰረት በቴሌብር አማካኝነት ዳሽን ባንክ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር የሚያቀርበዉ የብድር አገልግሎት ነው፡፡
- “ግለሰብ ደንበኛ” ማለት የተፈጥሮ ሰዉ ሆኖ በስሙ የቴሌብር አካውንት ያለዉና ቴሌብር መላ አነስተኛ የብድር አገልግሎት ለመዉሰድ የተስማማ ሰዉ ማለት ነው።
- “ኤሌክትሮኒክ ገንዘብ/ኢ- መኒ” ማለት ከ ኢትዮጵያ ብር ጋር እኩል መጠን ያለው ገንዘብን የሚወክል ደንበኛው የሚያስተዳድረዉ አና በደንበኛዉ የቴሌብር ሂሳብ ዉስጥ የሚገኝ የኤሌክትሮኒክስ የገንዘብ ዋጋ ነው።
- "አንተ" ወይም " የአንተ" ማለት የግለሰብ ደንበኛ ማለት ሲሆን የግለሰቡን የግል ተወካዮችም ያጠቃልላል።
- "እኛ" "አኛን" እና "የእኛ" ማለት ዳሽን ባንክ እና ኢትዮ ቴሌኮም ማለት ነው፡፡
- “የአገልግሎት ክፍያ ” ማለት መላ አነስተኛ ብድር አገልግሎት በመጀመሪያዉ ቀን በግለሰብ ደንበኞች የሚፈፀም ክፍያ ነው ::
- ”ዕለታዊ ክፍያ ” ማለት ሳይከፈል በቀረዉ የዕዳ መጠን ላይ ግለሰብ ደንበኛዉ በወሰደዉ የብድር ዓየነት መሠረት በየዕለቱ የሚፈፀም የክፍያ ዓይነት ነዉ ፡፡
- "የቅጣት ክፍያ" ማለት ግለሰብ ደንበኛዉ በገባዉ ዉል መሠረት የብድሩን ገንዘብ ሳይከፍል የቀረ እንደሆን የሚከፍለዉ ገንዘብ ነዉ፡፡
- "የክፍያ ቀን " ማለት ግለሰብ ደንበኛዉ የወሰደዉን ብድር ከፍሎ እንዲያጠናቅቅ የሚጠበቅበት የመጨረሻዉ ቀን ነወ ፡፡
- "የተበላሸ ብድር" ተበዳሪዉ ብድሩን አጠናቆ እንዲከፍል ከሚጠበቅበት የመጨረሻዉ ዕለት ጀምሮ ከሚቆጠር 90 ቀናት በኋላ ያልተከፈለ ብድር ማለት ነዉ፡፡
- በአነስታይ ፆታ የተገለፁ ለተባዕታይ ፆታ እንደዚሁም በተባዕታይ ፆታም የተገለፁ ለአነስታይ ፆታ ያገለግላሉ
- ግለሰብ የሚለዉ ቃል ወንድና ሴት ፆታን ለመግለፅ ያገለግላል፡፡
- ደንብ እና ሁኔታዎችን ስለመቀበል
- ይህአነስተኛ የብድር አገልግሎት ዳሽን ባንክ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር የሚያቀርበዉ ሲሆን ለብድሩ የዋለዉ ገንዘብ በዳሽን ባንክ የቀረበ ነዉ ፡፡
- መላ አነስተኛ የብድር አገልግሎትን ለማስጀመር ግለሰብ ደንበኛዉ USSD (*127#) ወይም የቴሌብርን መተግበሪያ መጠቀም ይችላል ፡፡
- መላየብድር አገልግሎትን ለመጠቀም ከማመልከትዎ በፊት ይህን ደንብ እና ሁኔታዎች በጥንቃቄ በማንበብ እና በመረዳት መስማማት ይኖርብዎታል፡፡
- በእነዚህ ደንቦችና ሁኔታዎች ካልተስማሙ እባክዎን ከዝርዝር ምርጫዉ “ለማስጀመር” የሚለውን ምረጫ አይጫኑ፡፡
- “(ለማስጀመር)” የሚለውን አማራጭ ሲጫኑ ደንብ እና ሁኔታዎችን በማንበብ ተረድተው ለማክበር መስማማትዎን እንዳረጋጋጡ ወይም ብድር ክፍያን ለመጠቀም እንደተስማሙ ይወሰዳል።
- መላ አነሰተኛ የብድር አገልግሎትን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ለመተግበር እና የክሬዲት አገልግሎትን በኤሌክትሮኒካዊ መንገድ ብቻ በቴሌብር ለመጠቀም ተስማምተዋል።
- ደንብ እና ሁኔታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በኢትዮ ቴሌኮም እና/ወይም በዳሽን ባንክ ሊሻሻሉ ወይም ሊለወጡ የሚችሉ ሲሆን ይህንንም ለዉጥ የሚያስገነዝብ ማሳሰቢያ አስቀድሞ እንዲደርስዎት ይደረጋል። እነዚህ ለዉጦች በቴሌብር ፖርታል በቴሌብር መተግበሪያ ወይም ድረ ገጽ ላይ ከተለቀቁበት ዕለት ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡
- ደንብና ሁኔታዎች በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ተቀባይነት ካገኘበት ጊዜ ጀምሮ በእርስዎ እና በእኛ መካከል በህጋዊ መንገድ አስገዳጅ ውል ይሆናሉ።በዚህ በዚህ ስምምነት ስር ያለዎትን ማንኛውንም መብት ወይም ግዴታ ለሌላ ለማንም ማስተላለፍ አይፈቀድልዎትም።
- ግለሰብ ደንበኛውገንዘቡን ለህጋዊ ዓላማ ብቻ ለማዋል ተስማምቷል።
- 3.የብድርአገልግሎትን ለማስጀመር
የብድር አገልግሎትን ከኢትዮ ቴሌኮም እና ዳሽን ባንክ ጋር ለማስጀመር ቢያንስ፡-
- እነዚህንደንቦችና ሁኔታዎችን ሊያነቡ፣ሊረዱ እና ሊስማሙ ይገባል፣
- 18ዓመት እና ከዚያ በላይ መሆን፣
- አገልግሎት የሚሰጥ የኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርድ መያዝ፣
- የቴሌብር እና የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቶችን እንደ ዳታ/ድምጽ/አጭር የጽሁፍ መልዕክት የሚጠቀሙ መሆን አለብዎት
- የቴሌብር የደንበኝነት ቆይታ 3 ወር እና ከዛ በላይ መሆን አለበት
- መላአነሰተኛ ብድር ለማግኘት መሰረታዊ መስፈርቶች፤
- የግለሰብ ደንበኛው የመበደር አቅም፣ ደንበኛው የብድር ክፍያ አገልግሎት ለመጠቀም ጥያቄ ካቀረበበት ቀን በፊት ባደረገው የ6 ወር የቴሌብር የገንዘብ እንቅስቃሴ፣ቀደም ሲል የወሰደዉን ብድር የመክፈል ታሪክእና በቴሌኮም አገልግሎት አጠቃቀም ይወሰናል። ከታች ያሉት የቴሌብር ግብይቶች የደንበኛ የብድር አቅምን ለማስላት ይውላሉ።
- የአየርሰዓት መሙላት ወይም ጥቅል መግዛት (በራስ አገዝ ወይመ ከወኪሎች)፣
- ዕቃወይም አገልግሎት በመግዛት ግብይት መፈጸም፣
- ቢልክፍያ (በራስ አገዝ ወይም ከወኪሎች)፣
- ለእርስዎወይም የሌላ ደንበኛ የፍጆታ አገልግሎት ክፍያ (በራስ አገዝ ወይም ከወኪሎች)፣
- በልክ ዲስፐርስመንት (የቀን ሠራተኞች ክፍያ ፣ደመወዝ ፣ዕርዳታ፣ጡረታ፣…) ክፍያ በቴሌብር መቀበል፣
- ከውጭአገር ገንዘብ መቀበል፣
- የትኬት ግዢ፣
- ለገንዘብማሰባሰቢያ የእርዳታ ክፍያ( ፈንድ ረይዚንግ)፣
- በቴሌብር ወኪሎች በኩል ገንዘብ መቀበልና ወጪ ማድረግ፣
- የቁጠባአገልግሎት፣
- ገንዘብመላክ፣
- የቴሌኮምፍጆታ (ድምጽ፣ ዳታ ወይም መልዕክት)፣
- በቴሌብር የተወሰደን ብድር በአግባቡ የመክፈል የቀደመ ታሪክ ፡፡
- ብቁለመሆን ደንበኞች ከቴሌኮም አገልግሎት ፍጆታ በተጨማሪ የቴሌብር አገልግሎት መጠቀም አለባቸው፡፡
- መላመዳረሻ ብድር ለማግኘት ወርሃዊ ደሞዝን በቴሌብር አማካኝነት መቀበል እና ከሚሰራበት ተቋም ጋር የሚደረግ ስምምነት በቂ ነዉ፡፡
- የብድሩ መጠን እና ክፍያ
- የግቢይት መጠንዎን መሠረት በማድረግ በሚፈቀደው ዝቅተኛ እና ከፍተኛ የክሬዲትመጠን መካከል ማንኛውንም መጠን መበደር ይችላሉ፡፡
- በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 576/2018 መሠረት ለኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ ከጠየቁት ጠቅላላ የብድር መጠን ላይ አንድ በመቶ (1%) ተቀናሽ ተደርጎ ቀሪዉ ወደ ቴሌብር አካውንትዎ ገቢ ይደረጋል፡፡
- ሌላ ብድር ለማግኘት መጀመሪያ ከቴሌብር የወሰዱትን ብድር መክፈል ይጠበቅብዎታል፡፡
- ያለብዎትን ብድር በከፊል ወይም በሙሉ በአንድ ጊዜ መክፈል ይችላሉ፡፡
- እንደየ ብድሩ ዐዓይነት ብድሩን ከወሰዱበት ዕለት ጀምሮ የብድር መክፈያ ቀነ ገደብ 1 ቀን ፣ 7 ቀን 30 ቀን እና 50 ቀን ነዉ፡፡
- ለመላ ዕለታዊ ዝቅተኛዉ የብድር መጠን 100.00 ብር ሲሆን ከፍተኛዉ 2,00 ነዉ ፣ ለመላ ሣምነንታዊ ዝቅተኛዉ የብድር መጠን 100.00 ብር ሲሆን ዝቅተኛዉ 5,000.00 ነዉ ፣ ለመላ ወርሀዊ ዝቅተኛዉ የብድር መጠን 600.00 ሲሆን ከፍተኛዉ 15,000.00 ብር ነዉ ፣ ለመላ የ50 ቀን ዝቅተኛዉና ከፍተኛዉ የብድር መጠን 30,000.00 ነዉ፡፡
- ያለብዎትንዕለታዊ ብድር በመክፈያዉ ቀን ከከፈሉ በመጀመሪያዉ ቀን የዋናዉን ዕዳ 1% የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላሉ፡፡
- ያለብዎትን ሣምንታዊ ብድር በመክፈያዉ ቀን ከከፈሉ በመጀመሪያዉ ቀን የዋናዉን ዕዳ 1% የአገልግሎት ክፍያ የሚከፍሉ ሲሆን የዋናዉን ዕዳ ቀሪ ክፍያ ዕዳዉን ከፍለዉ እስኪያጠናቅቁ ድረስ በየዕለቱ ከ 0.35 % እስከ 1.2% ዕለታዊ ክፍያ ይፈፅማሉ፡፡
- ያለብዎትን ወርሀዊ ብድር በመክፈያዉ ቀን ከከፈሉ በመጀመሪያዉ ቀን የዋናዉን ዕዳ 3% የአገልግሎት ክፍያ የሚከፍሉ ሲሆን የዋናዉን ዕዳ ቀሪ ክፍያ ዕዳዉን ከፍለዉ እስኪያጠናቅቁ ድረስ በየዕለቱ ከ 0.3 % እስከ 0.8% ዕለታዊ ክፍያ ይፈፅማሉ፡፡
- ያለብዎትን የሃምሳ ቀን ብድር በመክፈያዉ ቀን ከከፈሉ በመጀመሪያዉ ቀን የዋናዉን ዕዳ 6% የአገልግሎት ክፍያ የሚከፍሉ ሲሆን የዋናዉን ዕዳ ቀሪ ክፍያ ዕዳዉን ከፍለዉ እስኪያጠናቅቁ ድረስ በየዕለቱ ከ 0.5 % እስከ 0.7% ዕለታዊ ክፍያ ይፈፅማሉ፡፡
- ለመላመዳረሻ የብድር ክፍያዉ በወሰዱት የብድር ጊዜ ተከፋፍሎ በየወሩ ይከፈላል ፡፡
- የመክፈያጊዜዉ 3 ወር ለሆነ የ30% ለመላ መዳረሻ ደመወዝ ብድር 10% የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላሉ ::
- የመክፈያጊዜዉ 9 ወር ለሆነ የ2 ወር ለመላ መዳረሻ ደመወዝ ብድር 16% የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላሉ ::
- የመክፈያጊዜዉ 12 ወር ለሆነ የ3 ወር ለመላ መዳረሻ ደመወዝ ብድር 20 % የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላሉ::
- የ2 እና 3 ወር ደመወዝ ብድሮዎትን ከክፍያ ቀን በፊት የሚከፍሉ ከሆነ የዋናውን ብድር ቀሪ ክፍያ 3% ብቻ የሚከፍሉ ይሆናል፡፡
- እንደየ ብድሩ ዐይነት የሚጠበቅብዎትን ክፍያ ሳይፈፅሙ የመክፈያ ቀን ካለፈ ቀጥሎ በተመለከተዉ ሁኔታ የቅጣት ክፍያ ተፈፃሚ ይደረጋል፤
- ለመላ ወርሀዊ እና መላ የ 50 ቀን በየዕለቱ 0.11%፣
- ለመላ ሣምንታዊ እና መላ መዳረሻ በየዕለቱ 0.50%፣
- ለመላ ዕለታዊ 2%
- በጉርሻየሚያገኙት ገንዘብ ለክሬዲት ክፍያ አይውልም፡፡
- ያልተፈፀመ ክፍያ አሰባሰብ
- የሚጠበቅብዎትን ክሬዲት ክፍያ በሰዓቱ ካልፈፀሙ ኢትዮ ቴሌኮም ወይም ዳሽን ባንክ የቀረውን የብድር መጠን ከቴሌብር ሂሳብዎ ወይም ከ ሣንዱቅ ቁጠባ አካውንቶ ወዲያውኑ ተቀናሽ ያደርጋሉ፡፡
- ብድሩ መከፈል ባለበት ጊዜ ሳይከፈል የቀረ እንደሆነ ኢትዮ ቴሌኮም እና/ወይም ዳሽን ባንክ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከባለዕዳዉ ዳሽን ባንክ ወይም ሌሎች ባንኮች ሒሳብ በቀጥታ መቁረጥን ጨምሮ ማናቸዉም አማራጭ ዜዴዎች በመጠቀም ከፍርድ ቤት ዉጭ ባለ አማራጭ ዕዳዉን መሰብሰብ ይችላሉ፡፡
- ከፍርድቤት ዉጭ ባለ አማራጭ ዕዳዉን ለመሰብሰብ ያግዝ ዘንድ ኢትዮ ቴሌኮም እና/ወይም ዳሽን ባንክ የግለሰብ ደንበኛዉን አድራሻ ማናቸዉም አማራጭ ዘዴዎች በመጠቀም አፈላልገዉ በማግኘት ዕዳዉን የመሰብሰብ መብት ያላቸዉ መሆኑን ግለሰብ ደንበኛዉ ተስማምቷል፡፡
- ዕዳዉመከፈል ባለበት ጊዜ ሳይከፍል የቀረ እንደሆነ ኢትዮ ቴሌኮም እና/ወይም ዳሸን ባንክ የግለሰብ ደንበኛዉን አድራሻ እና ሌሎች ለእዳው አሰባሰብ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ዕዳዉን በመሰብሰብ ሥራ ላይ ለሚሳተፍ ሦስተኛ ወገን (ድርጅት ወይም ግለሰብ) አሳልፈዉ መስጠት የሚችሉ መሆኑን ግለሰብ ደንበኛዉ ተስማምቷል፡፡
- ከፍርድ ቤት ዉጭ ባለ አማራጭ ዕዳዉ የማይከፈል ከሆነ ኢትዮ ቴሌኮም እና/ወይም ዳሽን ባንክ ጉዳዩን ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት በራሳቸዉ ወይም በሌላ የሕግ አገልግሎት ሰጪ ተቋም ወይም በግለሰብ ጠበቃ አማካኝነት የመውሰድና የመክሰስ ሙሉ መብት አላቸው፡፡
- የተበላሸ ብድር ውስጥ ያለ ደንበኛ አጠቃላይ ዕዳውን ለመክፈል " የተበላሸ ብድርን በተራዘመ የመክፈያ ጌዜ አማራጭን" መጠቀም ይችላል።እንደ ተበላሸው የብድር መጠን ከ0.75%-1% የአገልግሎት ክፍያ ይኖረዋል፡፡
- ተፈጻሚነትያለው ሕግ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕጎች፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች፣ እንዲሁም የዳሽን ባንክና/ ወይም የኢትዮ ቴሌኮም አግባብነት ያላቸው አሠራር ሥርዐቶች በእነዚህ ደንብ እና ሁኔታዎች ላይ ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
- መረጃ ስለመጠየቅ
ከቴሌብር መላ አገልግሎት፣ ሂደት፣ ደንብ እና ሁኔታዎች ጋር ለተያያዘ ማንኛውም ጥያቄ በቴሌብር የደንበኞች ግንኙነት ማእከል (127 በመደወል)፣ አጭር የፅሁፍ መልዕከት ወደ 126 በመላክ የኢትዮ ቴሌኮም ማህበራዊ ድረ ገፅ (https://telehub.ethiotelecom.et/) በመጎብኘት ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
- የውል መቋረጥ
ማንኛውንም የአነስተኛ ቁጠባ እና ብድር አገልግሎቶችን ያለቅድመ ማስጠንቀቂያ ወይም ያለማስታወቂያ በእርስዎ አላግባብ መጠቀም ወይም ማጭበርበር ምክንያት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ለማገድ ወይም ለማቋረጥ መብት ይኖረናል። የዚህ ውል መቋረጥ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የሁለቱንም ተዋዋይ ወገኖች መብቶችን እና ግዴታዎችን ሊነካ አይችልም።
- ቅሬታእና የግጭት አፈታት
ቅሬታዎች በአካል፣ በጽሁፍ፣ በፖስታ፣ በፋክስ፣ በኢሜል ወይም በስልክ ሊቀርቡ ይችላሉ ኢትዮ ቴሌኮም ቅሬታዎን በተገቢው ጊዜ ለመፍታት ሁሉንም እርምጃዎች ይወስዳል። በመልሱ ካልረኩ ጉዳዩን ወደ ዳሽን ባንክ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቅደም ተከተል መውሰድ ይችላሉ፡፡ቅሬታዉ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮ ቴሌኮም ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ በሚቆጠር ሠለላሳ ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ተዋዋይ ወገኖች ስምምነት ላይ መድረስ ካልቻሉ ጉዳዮቻቸውን በኢትዮጵያ ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት ብቻ ለማቅረብ ተስማምተዋል።
- የመያዝ መብት
እኛ ጋር ያለብወትን እዳ ካልከፈሉ በተለይም በጥሬ ገንዘብ፣ዕቃዎች፣ዋስትናዎች፣ውድ ጌጦች፣ቼኮች እና ማንኛውን ተንቀሳቃሽም ሆነ የማይነቀሳቀስ ንብረትዎ ላይ አጠቃላይ የመያዝ መብት ይኖረናል፡፡እኛ ጋር ያለብወትን እዳ የማይከፍሉ ከሆነ እና የማቻቻል መብት ሲፈጠር በመያዣ መብት ስር የተያዙ ንብረቶችን ላልተከፈለው ብድር እንደ ዋስትና ተደርጎ መቁጠር ይቻላል፡፡
- ዕዳ ስለማቻቻል
የወሰዱትን አነስተኛ ብድር መጠን እንዲከፍሉ ካሳወቅን በኋላ በተቀመጠለት ጊዜ ገደብ ውስጥ መመለስ ካልቻሉ ባንክ ውስጥ ካሉዎት ሌሎች የባንክ ተቀማጭ ጥሬ ገንዘብ፣ ቁጠባ፣ተርም ዲፖዚት፣የጋራ ወይም የተናጠል ከሆኑት ላይ ያለብዎትን ዕዳ መጠን ያህል ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መዉሰድ እንድንችል ተስማምተዋል፡፡
- ማስተባበል
የቴሌብር ሚስጥር ቁጥር (ፒን) በሚስጥር መቀመጥ አለበት ከእርስዎ ሌላ ለማንም ተደራሽ መሆን የለበትም። የሚስጥር ቁጥርዎን ሌላ ሶስተኛ ወገን እንዲያዉቀዉ በማድረግዎ ወይም በየጊዜው ባለመቀየርዎ፣ ያልተፈቀደ የቴሌብር አጠቃቀም በማከናወንዎ፣ የሞባይል ስልክዎ ወይም ሲም ካርድ ሲሰረቅብዎ ወይም ሲጠፋብዎ ለሚመለከተዉ አካል ፈጥነዉ ባለማሳቅዎ እና ባለመስዘጋትዎ የሚደርስብዎ ኪሳራ /ጉዳት የእርስዎ ኃላፊነት ብቻ ይሆናል፡፡