ማኅበራዊ ኃላፊነት​

በኩባንያችን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ ለማህበራዊ ኃላፊነት ቁልፍ ቦታ መሰጠቱ ለጉዳዩ ያለንን ቁርጠኝነት ያሳያል። ኩባንያችን  ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት የሚያደርገው ይህ ተግባር በማህበረሰቡ፣ በአከባቢ ልማት እና በሁሉም ባለድርሻ አካላት ላይ በጎ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር እሙን ነው፡፡ የኩባንያችን  ማህበራዊ ኃላፊነት የማህበረሰቡን የረጅም ጊዜ ልማት ማሳለጥ በሚችሉ እንደ ትምህርት፣ ጤና፣ የአካባቢ ጥበቃ፣ አካባቢን የማስዋብ መርሃግብር በመሳሰሉ መሠረታዊ ፕሮጀክቶች ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡

ማኅበራዊ ኃላፊነት​ የትኩረት መስኮች​

ትምህርት

ትምህርት በአንድ አገር ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ እድገት ውስጥ የዜጎችን ተሳትፎ ለማሳደግ ወሳኝ ሲሆን፣ በትምህርት ዘርፉ ላይ የሚውለው መዋዕለ-ንዋይም በዘላቂነት የሚያስገኘው ጥቅም እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡  ተጨማሪ ለማንበብ.

የአካባቢ ልማትና ጥበቃ

ኢትዮ ቴሌኮም የአካባቢ ጥበቃ እንቅስቃሴዎች እና የአረንጓዴ አሻራ እንዲቀጥል በማድረጉ ረገድ ያለው ቁርጠኝነት ከፍተኛ ነው። ተጨማሪ ለማንበብ.

ሰብአዊነት

ኢትዮ ቴሌኮም በፖሊሲው መሠረት ከማህበረሰቡ ለሚቀርቡ ለተለያዩ ሰብዓዊ-ነክ የድጋፍ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት የማኅበራዊ ኃላፊነቱን ሚና በትጋት እየተወጣ ይገኛል። ተጨማሪ ለማንበብ.

የሠራተኛ በጎ ፈቃደኝነት

የኢትዮ ቴሌኮም ሠራተኞች የተለያዩ የበጎ ፈቃድ ሥራዎችን በማከናወን የማህበረሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመቅረፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።  ተጨማሪ ለማንበብ…

ለኮቪድ -19 የተሰጠ ምላሽ

በሀገር አቀፍ ደረጃ የኮሮናቫይረስወረርሽኝንለመከላከልለሚደረገው እንቅስቃሴ የ100 ሚሊዮንብር ድጋፍ እና በኮቪድ ላይ የሚደረገውን ጥናትና ምርምር ለማገዝ የ604,484 የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ ተደርጓል  ተጨማሪ ለማንበብ.

የመንግሥት ፕሮጀክቶች ድጋፍ

በቴክኖሎጂ የተደገፈ ጥራት ያለው ትምህርት፣ ጤና፣ አስተዳደር፣ ወዘተ መደገፍና ማጠናከር ማህበረሰቡ የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኝ ያስችላል።  ተጨማሪ ለማንበብ.

ሰታቲስትክስ

0 ሚ. ብር
ትምህርት
0 ሚ. ብር
የአካባቢ ልማትና ጥበቃ
0 ሚ. ብር
የመንግሥት ፕሮጀክቶች ድጋፍ
0 ሚ. ብር
ሰብአዊነት
0 ሚ. ብር
የሠራተኛ በጎ ፈቃደኝነት
0 ሚ. ብር
አጭር ቁጥር ኮድ እና መልዕክት
0 ሚ. ብር
አጠቃላይ