በኩባንያችን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ ለማህበራዊ ኃላፊነት ቁልፍ ቦታ መሰጠቱ ለጉዳዩ ያለንን ቁርጠኝነት ያሳያል። ኩባንያችን ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት የሚያደርገው ይህ ተግባር በማህበረሰቡ፣ በአከባቢ ልማት እና በሁሉም ባለድርሻ አካላት ላይ በጎ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር እሙን ነው፡፡ የኩባንያችን ማህበራዊ ኃላፊነት የማህበረሰቡን የረጅም ጊዜ ልማት ማሳለጥ በሚችሉ እንደ ትምህርት፣ ጤና፣ የአካባቢ ጥበቃ፣ አካባቢን የማስዋብ መርሃግብር በመሳሰሉ መሠረታዊ ፕሮጀክቶች ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡