የአየር ሰዓት ለመግዛት

የቴሌብር የአየር ሰዓት ለመሙላት በድረ-ገጽ (Web)፣ በሞባይል መተግበሪያ፣ በአጭር ቁጥር (USSD) እና በአጭር የጽሑፍ መልዕክት (SMS) የመሳሰሉ አማራጮችን በመጠቀም ለራስዎ ወይም ለሌላ ሰው የአገልግሎት ቁጥር ለመሙላት ያስችላል። የተመዘገቡ ደንበኞች የቴሌብር አካውንታቸውን በመጠቀም ለሞባይል ስልካቸው በቀላሉ የአየር ሰዓት መሙላት ይችላሉ።

በቴሌብር የአየር ሰዓት መሙላት በጣም ቀላል እና ፈጣን ነው!

ቴሌብርን በመጠቀም የችርቻሮ መሸጫ ሱቆችን በአካል መጎብኘት ሳያስፈልግዎ በማንኛውም ጊዜና ቦታ ለራስዎ ወይም ለሌላ ሰው የሞባይል የአየር ሰዓት በቀላሉ መሙላት ይችላሉ።

በቴሌብር የአየር ሰዓት መሙላት በጣም ቀላል እና ፈጣን ነው!

ቴሌብርን በመጠቀም የችርቻሮ መሸጫ ሱቆችን በአካል መጎብኘት ሳያስፈልግዎ በማንኛውም ጊዜና ቦታ ለራስዎ ወይም ለሌላ ሰው የሞባይል የአየር ሰዓት በቀላሉ መሙላት ይችላሉ።

ቴሌብርን በመጠቀም የሞባይል አየር ሰዓት እንዴት መሙላት እንችላለን?

 • *127# ይደውሉ ወይም ወደ ቴሌብር ሞባይል መተግበሪያ ይግቡ
 • ከአማራጮች ውስጥ ‘አየር ሰዓት ይግዙ/ጥቅል’ የሚለውን ይምረጡ
 • ‘ለራስ’ የሚለውን ይምረጡ፣ ወይም ለሌላ (ለሌላ ሰው) ይምረጡ
  • የተቀባዩን ስልክ ቁጥር ያስገቡ/ ይምረጡ
  • የአየርሰአትመጠንያስገቡ/የጥቅልአይነትን ይምረጡ
  • የሚስጥር ቁጥር (PIN) ያስገቡ
  • ማስተላለፍዎን ያረጋግጡ

                           

ኢትዮቴሌ ክሬዲት አገልግሎት

እርስዎ ወይም ወዳጅዎ ያሎት/ያላቸው ቀሪ ሂሳብ አነስተኛ ሆኖ በወቅቱ የአየር ሰዓት ለመሙላት ካልቻሉ የቴሌብር መተግበሪያን ተጠቅመው ወይም *127# በመደወል የአየር ሰዓት ወይም የጥቅል ክሬዲት ማግኘት ይችላሉ፡፡

የብቁነት መስፈርት

የአካውንት ደረጃ

የኔትወርካችን ተጠቃሚ የሆኑበት ጊዜ

የግብይት መጠን

የግብይት መጠን በብር 

መበደር የሚችሉት መጠን በብር

ደረጃ 1

3 ወራት

4

ከ 4 እስከ 400

ከ 1 እስከ 100

ደረጃ 2 እና 3

3 ወራት

3 እና ከዛ በላይ

ከ 3 እስከ 750

ከ 1 እስከ 250

 • ለክሬዲት አገልግሎት ብቁ የሚያደርጎት የግብይት ዓይነቶች፡ ባለፈው ወር የቴሌብር ሞባይል መተግበሪያን ተጠቅመው ወይም *127# በመደወል የገዙት ጥቅል እንዲሁም አየር ሰዓት፣ ቴሌብር ተጠቅመው የገዟቸው ምርትና አገልግሎቶች ካሉ፣ የአገልግሎት ክፍያ በቴሌብር ከፈፀሙ የክሬዲት አገልግሎት ለማግኘት ብቁ ያደርጎታል፡፡
 • ደረጃ አንድ ላይ ያሉ ደንበኞች መጠየቅ ከፈለጉት ክሬዲት በ4 እጥፍ በባለፈው ወር ግብይት ፈፅመው የሚያውቁ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ (ለምሳሌ የ 1 ብር ክሬዲት ለመጠየቅ ከፈለጉ የ4 ብር ግብይት በባለፈው ወር ማከናወን ይጠበቅባቸዋል፡፡)
 • ደረጃ ሁለትና ሶስት ላይ ያሉ ደንበኞች መጠየቅ ከፈለጉት ክሬዲት በ3 እጥፍ በባለፈው ወር ግብይት ፈፅመው የሚያውቁ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ (ለምሳሌ የ 100 ብር ክሬዲት ለመጠየቅ ከፈለጉ የ300 ብር ግብይት በባለፈው ወር ማከናወን ይጠበቅባቸዋል፡፡)
 • ከ 1 እስከ 250 ብር ክሬዲት ሲጠይቁ የተከፋፈለ ስላልሆነ ደንበኞች በአካውንት ደረጃቸው መሰረት የሚፈልጉትን የገንዘብ መጠን መጠን ማስገባት ይችላሉ፡፡
 • ደንበኞች ክሬዲት ለመጠየቅ የኢትዮ ቴሌኮም ኔትወርክ መጠቀም/ ደንበኛ መሆን ከጀመሩ ቢያንስ 3 ወራት (90 ቀናት) መሆን ይኖርበታል፡፡
 • ደንበኞች ቢያንስ ለአንድ ወር የቴሌብር አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
 • የአየር ሰዓት ክሬዲት ከወሰዱ በኋላ ጥቅል ሊገዙበት ወይም የፈለጉትን አገልግሎት ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡
 • ቴሌብር ላይ ያሎት ቦነስ/ማበረታቻ ሽልማት የወሰዱትን አየር ሰዓት/ጥቅል ክሬዲት ለመክፈል አያገለግልም፡፡
 • ደንበኞች ለወሰዱት አየር ሰዓት/ጥቅል ክሬዲት በወኪሎች፣ ኢትዮ ቴሌኮም ሽያጭ ማዕከላት ወይም ከባንክ ገንዘብ ወደ ቴሌብር አካውንታቸው ተቀማጭ ሲያደርጉ ወይም ከውጭ ሀገራት ገንዘብ ሲላክ፣ የአየር ሰዓት በቴሌብር ወይም በሞባይል ቁጥራቸው ሲሞሉ ተቆራጭ የሚደረግ ይሆናል፡፡
 • ሁሉም የሚሰራ የሞባይል ቁጥር ያላቸው እና ቴሌብር የሚጠቀሙ ደንበኞች የኢትዮቴል ክሬዲት አገልግሎት ለራሳቸው እንዲሁም ለወዳጃቸው ማግኘት ይችላሉ፡፡
 • ለሌሎች ደንበኞች የጠየቁት የአየር ሰዓት ወይም ጥቅል ክሬዲት የሚከፈለው በጠያቂው ይሆናል፡፡
 • የሞባይል ቁጥራቸው የአገልግሎት ጊዜ በማለፉ የተዘጉ፣ የታገዱ እንዲሁም አገልግሎት መስጠት ያቋረጡ ደንበኞች የክሬዲት አገልግሎት ለማግኘት አይችሉም፡፡
 • ደንበኞች የወሰዱትን ክሬዲት ከፍለው ሳይጨርሱ ሌላ ክሬዲት መጠየቅ አይችሉም፡፡
 • ከወሰዱት ክሬዲት ጋር 10% የአገልግሎት ክፍያ ተደምሮ ይከፍላሉ፡፡
 • ደንበኞች በቴሌብር የወሰዱትን ክሬዲት በ90 ቀናት ውስጥ ካልከፈሉ የወሰዱትን ክሬዲት ከነአገልግሎት ክፍያው ሲስተሙ ከቴሌብር ሂሳባቸው ላይ ተቀናሽ ያደርጋል፡፡
 • የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ የሆኑ ደንበኞች የወሰዱትን ክሬዲት በ90 ቀናት ውስጥ መክፈል ካልቻሉ እና በቂ የቴሌብር ባላንስ ከሌላቸው የክሬዲት መጠኑ ከነ አገልግሎት ክፍያው በቀጣይ ወር ቢል ጋር የሚደመር ይሆናል፡፡
 • የቅድመ ክፍያ ደንበኞች በ90 ቀናት ውስጥ መመለስ ካልቻሉ እንዲሁም በቴሌብር ሂሳባቸው ውስጥ የወሰዱትን ክሬዲት ከነ አገልግሎት ክፍያው ለመመለስ የሚያስችል በቂ ሂሳብ ከሌላቸው በማንኛውም ጊዜ ሂሳብ ሲሞሉ 15% የቅጣት ክፍያ ጨምሮ የሚቆረጥባቸው ይሆናል፡፡
 • ደንበኞች የክሬዲት አገልግሎት ሲወስዱ እንዲሁም መልሰው ሲከፍሉ የማረጋገጫ መልዕክት በሞባይል ቁጥራቸው የሚደርሳቸው ይሆናል፡፡
 • አንድ ደንበኛ የወሰደው ክሬዲት የመመለሻ ጊዜ አልፏል የሚባለው 48 ሰዓታት ካለፉት ነው፡፡ ደንበኛው ቀድሞ የወሰደውን ክሬዲት ከፍሎ ሳይጨርስ ሌላ ክሬዲት የመመለሻው ጊዜ ካለፈ በኋላ መጠየቅ አይችልም፡፡
 • በክሬዲት የተወሰደ የተመላሽ ሂሳብ ቀነገደብ 90 ቀን ነው
 • የወሰደውን ክሬዲት ላልመለሰ ደንበኛ በየ15 ቀኑ እንዲከፍል የማስታወሻ አጭር የፅሁፍ መልዕክት ይላክለታል፡፡

የአየር ሰዓት ክሬዲት ለማግኘት ብቁ ያልሆኑ:

 • የሞባይል ቁጥራቸው የአገልግሎት ጊዜ በማለፉ የተዘጉ፣ የታገዱ እንዲሁም አገልግሎት መስጠት ያቋረጡ ደንበኞች
 • የታገደ እንዲሁም አገልግሎት የማይሰጥ የቴሌብር አካውንት ያላቸው ደንበኖች
 • ተጨማሪ ብድር ለመጠየቅ ደንበኞች በፊት የወሰዱትን ብድር ከፍለው መጨረስ አለባቸው፡፡ ነገር ግን የመጀመሪያውን ብድር በጠየቁ እስከ 48 ሰዓት ውስጥ በአካውንት ደረጃቸው ፣ የግብይት መጠን እና የግብይት ብዛት መሰረት እስከተፈቀደላቸው የክሬዲት መጠን ድረስ መልሰው ክሬዲት መውሰድ የሚችሉ ይሆናል፡፡

ለምሳሌ፡ አንድ ደንበኛ የተፈቀደለት ከፍተኛው የክሬዲት መጠን 100 ብር ሆኖ 50 ብር ቢወስድ በድጋሚ እስከ 50 ብር ድረስ ክሬዲት መውሰድ ይችላል ማለት ነው፡፡ በድጋሚ ክሬዲት ለመጠየቅ የመጀመሪያውን ብድር ከወሰደ እስከ 48 ሰዓት ውስጥ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡ ከ 48 ሰዓታት በኋላ ክሬዲት ቢጠይቅ አገልገሎቱን ማግኘት አይችልም፡፡

 • ቴሌብርን አጭር ቁጥር 127/ መተግበሪያ ተጠቅመው የአየር ሰዓት ሲገዙ እስከ 5 ቀናት የሚያገለግል 10% የአየር ሰዓት ስጦታ
 • ቴሌብር የሞባይል መተግበሪያን በመጠቀም ለሚገዙ ጥቅሎች 10% ስጦታ ይሰጣል።

  • ስጦታው የተገደበ ጥቅል ለሚገዙ ደንበኞች ብቻ ያገለግላል፡፡
 • የሞባይል ጥቅል ሲገዙ

  • ቴሌብር የሞባይል መተግበሪያን በመጠቀም ለሚገዙ ጥቅሎች 10% ስጦታ ይሰጣል።
  • ስጦታው የተገደበ ጥቅል ለሚገዙ ደንበኞች ብቻ ያገለግላል፡፡