የነዳጅ ክፍያዎን በቀላሉ በቴሌብር ይፈጽሙ!

በነዳጅ ማደያ የነዳጅ ክፍያ ለመፈፀም

 • ነዳጅ ካስቀዱ በኋላ ለነዳጅ ቀጂው ቴሌብር የሚጠቀሙበትን ስልክ ቁጥር ይንገሩ፤
 • ባለሙያው የቀዱትን መጠን እና አስፈላጊ መረጃ ከሞላ በኋላ በስልክ ስክሪንዎ ላይ በሚደርስዎ መልዕክት ላይ ያስቀዱትን ገንዘብ መጠን በማረጋገጥ የፒን ቁጥርዎን ያስገቡ።
 • ይህን ሂደት ሲጨርሱ ከቴሌብር አካውንትዎ ላይ ተቀናሽ በማድረግ ክፍያ መፈጸሙን የሚያረጋግጥ አጭር መልዕክት ይደርስዎታል።
 • ደረሰኝ ካስፈለገዎ ከቴሌብር ሱፐርአፕ ማግኘት ይችላሉ

የቴሌብር አካውንት ከሌለዎት በቴሌብር ሱፐርአፕ መተግበሪያ ለመመዝገብ

 • የቴሌብር ሱፐርአፕ መተግበሪያን ከ http://onelink.to/fpgu4m ያውርዱ
 • አዲስ አካውንት ይክፈቱ የሚለውን በመጫን በደንብ እና ሁኔታዎች መስማማትዎን ያረጋግጡ
 • “ፈጣን አካውንት ይክፈቱ”  የሚለውን ይምረጡ
 • የሞባይል ቁጥርዎን ያስገቡ
 • “ማረጋገጫ ቁጥር ያግኙ” የሚለውን በመጫን በአጭር መልዕክት የሚደርስዎትን ባለ 6 አሃዝ የማረጋገጫ ቁጥር በማስገባት “ይቀጥሉ“ የሚለውን ይጫኑ
 • ቀጥሎ በሚመጣው ፎርም ላይ የግል መረጃዎች በመሙላት “ያስገቡ“ የሚለውን ይጫኑ
 • ከዚያም በአጭር መልዕክት የሚደርስዎትን መለያ ቁጥር (PIN) በማስገባት ይግቡ የሚለውን ይጫኑ
 • አገልግሎቱን ለማስጀመር የሚስጢር መለያ ቁጥሩን በአዲስ ይቀይሩ (የራስዎትን የሚስጥር ቁጥር ይጠቀሙ) ከዚያም ለመጨረስ የሚለውን ይጫኑ
 • የቴሌብር አካውንትዎ በተሳካ ሁኔታ መጀመሩን የሚገልፅ አጭር የፅሁፍ መልዕክት ይደርስዎታል፡፡

የቴሌብር አካውንት ከሌለዎት በበአጭር ቁጥር (*127#) ለመመዝገብ

 • ወደ *127# ይደውሉ
 • ለመመዝገብ 1 ቁጥርን በመለላክ የ# በመጫን ይቀጥሉ
 • በድጋሜ *127# በመደወል ለማስጀመር ዜሮ (0) ይላኩ
 • ቋንቋ ይምረጡ
 • በአጭር መልዕክት ከ127 የደረስዎትን የሚስጢር ቁጥር በማስገባት በራስዎ አዲስ የሚስጢር ቁጥር ይቀይሩ
 • ከዚያም የቴሌብር አካውንትዎ በተሳካ ሁኔታ መጀመሩን የሚገልፅ አጭር የፅሁፍ መልዕክት ይደርስዎታል፡፡

ገንዘብ ወደ ቴሌብር አካውንትዎ ገቢ ማድረጊያ አማራጮች

ከቴሌብር ጋር በተሳሰሩ 23 ባንኮች የሞባይል ባንኪንግ ቴሌብር ዋሌት ገንዘብ የማስተላለፊያ አማራጭን በመምረጥ ገንዘብ ማስተላለፍ የሚችሉ ሲሆን በባንኮቹ ቅርንጫፎች በኩልም እንዲሁ ገነዘብ ወደ ቴሌብር አካውንትዎ ገቢ ማድረግ ወይም ማስተላለፍ ይችላሉ፡፡

ከቴሌብር ጋር ትስስር ያደረጉ ባንኮች

 • የኢትዮጰያ ንግድ ባንክ
 • አቢሲንያ ባንክ
 • ዳሽን ባንክ
 • አዋሽ ባንክ
 • አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
 • ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ
 • ወጋገን ባንክ
 • ዘመን ባንክ
 • ብርሃን ባንክ
 • ሕብረት ባንክ
 • እናት ባንክ
 • ኦሮሚያ ባንክ
 • አማራ ባንክ
 • የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ
 • ደቡብ ግሎባል ባንክ
 • ዘምዘም ባንክ
 • አባይ ባንክ
 • ፀሐይ ባንክ
 • ሂጅራ ባንክ
 • አሐዱ ባንክ

ከዚህ በተጨማሪም በየአካባቢዎ በሚገኙ የቴሌብር ወኪሎች እና በኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት መስጫ ማዕከላት በኩል ገንዘብ ወደ ቴሌብር አካውንትዎ ገቢ ማድረግ ይችላሉ፡፡