በድርጅት ማስጀመሪያ ጥቅል የድርጅትዎን የከፍታ ጉዞ ያስጀምሩ!

አነስተኛና ጥቃቅን ንግድዎን ጅማሬውን ከማሳመር ወጪ ላይ ጥሩ መሆንን ይጠይቃል፡፡ ለዛም ነው በጀትዎን የማይጎዳ የድርጅት ማስጀመሪያ ጥቅል ለጀማሪ የንግድ ባለቤቶች አዘጋጅተን ያቀረብነው፡፡

በድርጅት ማስጀመሪያ ጥቅል፤ በዝቅተኛ ዋጋ ብዙ ጥቅሞችን ያገኛሉ!

በንግድ ጉዞዎ ስንቅ እንዲሆንዎ በመደበኛ ብሮድባንድ እና አዲስ ሲም ካርድ ከእኛ ሲገዙ በተመጣጣኝ ዋጋ ለእርስዎ የሚሆኑ ጥቅሎች ያገኛሉ፡፡ ለእርስዎ እንዲሆኑ ተደርገው የተዘጋጁት የቴሌኮም አገልግሎቶቻችን የፋይናስ አቅምዎን የማይፈታተን መሆኑን እርግጠኛ ነን፡፡

ከዚህ በታች የተጠቀሱት የድርጅት ማስጀመሪያ ጥቅሎች ይመልከቱ…

በድርጅት ማስጀመሪያ ጥቅል፤ በዝቅተኛ ዋጋ ብዙ ጥቅሞችን ያገኛሉ!

ለአነስተኛና ጥቃቅን ንግደድ ባለቤቶች የተዘጋጀ የግንኙነት አማራጭ

አዲስ መደበኛ ብሮድባንድ ከገዙ እንዲሁም አዲስ ሲም ካርድ ከሞባይል ጥቅል ጋር ቢገዙ ከመደበኛው ዋጋ የ20% ቅናሽ የተደረገባቸውን አማራጮች ያገኛሉ፡፡

የፍጥነት መጠን20% ቅናሽ የተደረገበት ዋጋ
5 ሜ.ቢ በሰከንድ 559
7 ሜ.ቢ በሰከንድ 703
10 ሜ.ቢ በሰከንድ 1,004
20 ሜ.ቢ በሰከንድ 1,868
50 ሜ.ቢ በሰከንድ 4,204
100 ሜ.ቢ በሰከንድ 7,396
200 ሜ.ቢ በሰከንድ 12,572
ሞባይል ጥቅል 1ሞባይል ጥቅል 2ሞባይል ጥቅል 3
530 ደቂቃ1,100 ደቂቃ2050 ደቂቃ
 25 ጊ.ባ5 ጊ.ባ10 ጊ.ባ
250 መልዕክት500 መልዕክት1000 መልዕክት
149.8 ብር/በወር289.8 ብር/በወር505.8 ብር/በወር

ሞደም ያስፈልጎታል?  DS124WS ሲንግል ባንድ ኤዲኤስኤል+ ዋይ-ፋይ ሞደም በ12 የተራዘመ ክፍያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ለኮምቦ አገልግሎታችን ቢመዘገቡ ከቅናሹ በተጨማሪ ደግሞ ነፃ ጥሪዎችን ያገኛሉ!

ያልተገደበ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲሁም የመደበኛ ስልክ አገልግሎትን በአንድ ላይ በኮምቦ አገልግሎታችን ማግኘት ይችላሉ፡፡

  • የኢንተርኔት አገልግሎት ላይ ቅናሽ ያገኛሉ፤

20% ቅናሽ  የመደበኛ ብሮድባንድ አገልግሎታች ላይ የሚያገኙ ያግኙ፤ የንግድ የጅማሬ ገዙዎን በቅናሹ ያሳምሩ!

  • ለ3 ወራት በመደበኛ ስልክ የሚቀርቡ ነፃ ጥሪዎችን ያጣጥሙ!

የኮምቦ አገልግሎት የሚጠቀሙ ከሆነ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን አገልግሎቱች በተከታታይ 3 ወራት ማግኘት ይችላሉ፡፡

  • 1200 ደቂቃ:በተመሳሳይ ከተማ ለሚደረግ ጥሪ
  • 400 ደቂቃ:ወደ ተለያዩ ከተሞች የሚደረግ ጥሪ
  • 300 ደቂቃ:ወደ ሞባይል ለሚደረግ ጥሪ

ይሄን የመሰለ ነፃ ጥሪ ካጣጣሙ ከ3 ወራት በኋላ መቀጠል ቢፈልጉ ተጨማሪ 100 ብር ብቻ በየወሩ እየከፈሉ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ዛሬ ነገ ሳይሉ ይህንን እድል ይጠቀሙበት፤ የመደበኛ ብሮድባንድ እና መደበኛ ስልክ አገልግሎት ዛሬውኑ ይጠይቁን!

ሌላም አለ! በማደግ ላይ ያለውን ንግድዎን የበለጠ ለማገዝ የበለጠ የሚያተርፉበት ሌላም አገልግሎት አለን!

We have a simple offer just for you.

አዲስ ሲም ካርድ በማውጣት 20% ቅናሽ የተደረገባቸውን የሞባይል ጥቅሎች በቅናሽ ያግኙ!

ወርኃዊ ድምፅ ጥቅል

ወርኃዊ ዳታ ጥቅል

ወርኃዊ ድምፅና ዳታ ጥቅል

800 ደቂቃ

250 መልዕክት

137 ብር

 

2,000 ደቂቃ

500 መልዕክት

273 ብር

 

2.5 ጊ.ባ

250 መልዕክት

110 ብር

 

5 ጊ.ባ

500 መልዕክት

218 ብር

 

Ø 600 ደቂቃ

2.5 ጊ.ባ

250 መልዕክት

205 ብር

 

1,600 ደቂቃ

5 ጊ.ባ

500 መልዕክት

410 ብር

ለድርጅት የማስጀመሪያ ጥቅላችን መጠይቅ ከማቅርብዎ በፊት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ደንብና ሁኔታዎች በጥንቃቄ ያንብቡ፡፡

ስለብቁነት

  • ይህ አገልግሎት በልዩነት የቀረበው ለድርጅት ደንበኞች ብቻ ስለሆነ
  • ከቅናሽ ጋር የቀረበው መደበኛ ብሮድባንድ ኢንተርኔታችን በልዩነት የተዘጋጀው ለጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ስራዎች ለተሰማሩ ብቻ ነው፡፡
  • እንዲሁም በቅናሽ የቀረቡት ሞባይል ጥቅሎች የቀረቡት ከአዲስ ሲም ካርድ ተጠቃሚዎች ነው፡፡

ለመመዝገብ

  • አንድ የድርጅት ደንበኛ ይህንን አገልግሎት መግዛት የሚችለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡
  • የሞባይል ጥቅል አገልግሎት ለመግዛት ካሰቡ ለአንድ ጊዜ ወይም በቋሚነት በየወሩ ብለው መምረጥ ይችላሉ፡፡

ለውጦች ስለሚስተናገዱበት ሁኔታ

  • ለማቋረጥ፡ ለኮምቦ አገልግሎት (መደበኛ ብሮድባንድና መደበኛ ስልክ) ካመለከቱ በኋላ ሁለቱም አገልግሎቶች ወይም ከሁለቱ አንዱ እቋረጥልዎ በማንኛውም ጊዜ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ከሁለቱ አንዱን በሚያቋርጡበት ጊዜ ታድያ በምዝገባ ወቅት የቀረበልዎ ቅናሽ እስከፈለጉት ጊዜ ድረስ እንደተጠበቀ ይቆያል፡፡
  • ፍጥነትለማሳደግና ዝቅ ለማድረግ
  • የሚቻልባቸው ሁኔታዎች:
    • ለአነስተኛና ጥቃቅን የብሮድባንድ ፍጥነቶች ውስጥ መርጠው ማሳደግ ወይም ዝቅ ማድረግ ይችላሉ፡፡
    • ነገር ግን በልዩነት ከቀረቡት ፍጥነቶች ውጪ ማለትም የቢዝነስ ቴሌ ፋይበር የፍፍነት አማራጮችን ከፈለጉ መቀየር የሚችሉ ቢሆንም ነገር ግን የተፈቀደልዎ 20% ቅናሽ የሚነሳ ይሆናል፡፡
  • የማይቻልባቸው ሁኔታዎች:
    • ለመደበኛ የጥቃቅንና አነስተኛ የብሮድባንድ አማራጮች ወይም ከቴሌ ቢዝነስ ፋይበር አገልግሎት ወደ እዚህ አገልግሎት የፍጥነት ለውጥ አድርገው መግባት አይችሉም፡፡

ስለቢል አከፋፈል

  • የአከፋፈል ሁኔታ:
    • መደበኛ ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት የቀረበው በድህረ ክፍያ የአከፋፈል ስርዓት ብቻ ነው፡፡
    • ከአዲስ ሲም ካርድ የቀረቡት የሞባይል ጥቅሎችን ግን በቅድመ ክፍያ፣ ድህር ክፍያ እና ሀይብሪድ አማራጭ ቀርቧል፡፡
  • የመጀመሪያ ወር አከፋፈል፡ለሁሉም የአከፋፈል ዘዴዎች (ቅድመ ክፍያ/ድህረ ክፍያ) አማራጭ ክፍያ ለመጀመሪያ ወር ብቻ ቅድሚያ መከፈል አለበት፡፡
  • ስለቀጣይ የአከፋፈል ሁኔታዎች (ለቋሚ ወርኃ ጥቅል ተጠቃሚዎች): ከመጀመሪያው ወር በኋላ ግን የቋሚ ወርኃዊ ጥቅል ተጠቃሚዎች በመደበኛ የአከፋፈል ሁኔታቸው ማለትም በድህረ ክፍያ ወይም ቅድመ ክፍያ የሚቀጥሉ ይሆናል፡፡
  • ተ.እ.ታ:ሁሉም የቀረቡት ዋጋዎች 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እና 2% ኤክሳይስ ግብር ታሳቢ ያደረጉ ናቸው፡፡

ስለ ኮምቦ አገልግሎታችን በተመለከተ 

  • የአከፋፈል ሁኔታ:ለአዲስ የኮምቦ አገልግሎት ጠያቂዎች በምዝገባ ወቅት የመደበኛ ብሮድባንድ ወይም ስልክ አገልግሎት የምዝገባ ክፍያ ሊካተት ይችላል፡፡
  • ስለነፃ የመደበኛ ስልክ አገልግሎት:ለኮምቦ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች ለተከታታይ 3 ወራት በዋና ገፅ ላይ የተጠቀሱትን አገልግሎቶች ከተከታታይ 3 ወራት በነፃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  • ነፃ የመደበኛ ስልክ ጥሪዎችን ለማስቀጠል፡ ከ3 ወራት በኋላ የቀረቡት ነፃ ጥሪዎች ማስቀጠል ቢፈልጉ በየወሩ ተጨማሪ 100 ብር በመክፈል በቋሚነት ማስቀጠል ይችላሉ፡፡

ስለ ሞደም የተራዘመ ክፍያ ሁኔታ፡

  • ስለብቁነት፡ አገልግሎት ጠያቂዎች ማለትም አዲስ ብሮድባንድ ኢንተርኔት ከአዲስ ሲም ካርድ ጋር የሚጠይቁ ደንበኞች የኤዲኤስኤል ሞደም በ12 ወራት የተራዘመ አከፋፈል ሁኔታ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  • ይህን የተራዘመ የአከፋፈል ሁኔታ ለማግኘት የሚገቡት ውል ይኖራል፡፡
  • ቀድሞ አገልግሎት ስለማቋረጥ: በተራዘመ ክፍያ ሞደም ለማግኘት ውል ቢገቡም ማቋረጥ ቢፈልጉ፤ የሞደሙን ዋጋ ቀሪ ክፍያ መፈፀም ይጠበቅብዎታል፡፡

 

 

የሞባይል ጥቅል  በመግዛትዎ የሚያገኟቸው ጥቅሞች

  • ማንኛውም ያልተጠቀሙበት ቀሪ ጥቅል (ደቂቃ፣ መልዕክት ወይም ዳታ) ካለዎት 100% ወደ ቀጣይ ወር ብቻ የሚተላለፍልዎ ይሆናል፡፡
  • ከጥቅለ ውጪ ሲጠቀሙ:የቀረቡትን ጥቅሎች ከወር በፊተ ቀድመው ቢጨርሱ የአገልግሎት ቀኑ (Expiry date) እስኪደርስ ድረስ ከዚህ በታች በተጠቀሱት ዝቅተኛ ዋጋዎች የሚከፍሉ ይሆናል፡፡
  • ዳታ:11 ሳንቲም በሜ.ባ
  • ድምጽ: 50 ሳንቲም በደቂቃ
  • መልዕክት: 12 ሳንቲም በመልክዕት