Description Image
ወጪዎን የሚቆጣጠሩበት…ቀላል የአከፋፈል ዘዴ
ለድርጅትዎ በልዩነት የቀረቡ የሞባይል ጥቅሎችን ያግኙ! ለድርጅቶች የቀረበው የሞባይል ጥቅል ለተጠቃሚዎች ምቹ፣ ቀላል፣ እና የተለያዩ አማራጭ ጥቅሎችን የያዘ አገልግሎት ነው፡፡ በተጨማሪም ድርጅቶች በተለያየ የአካውንት ቁጥር የሚጠቀሟቸውን አገልግሎቶች ወደ አንድ አካውንት በማድረግ ለክፍያ ምቹ እንዲሆንላቸው ማድረግ ይችላሉ፡፡ ይህንን ታሳቢ በማድረግ ያቀረብናቸው ሞባይል ጥቅሎች በተመጣጣኝ ዋጋ ለአከፋፈል ምቹ በሆነ መልኩ ነው፡፡

የእኛን ሞባይል ጥቅሎች ምን ልዩ ያደርጋቸዋል ካሉ

የድርጅትዎ ሰራተኞችን የሞባይል አገልግሎት ፍላጎት የሚያሟሉ ለአጠቃቀም ቀላልና ምቹ የሞባይል ጥቅሎች መሆናቸው ነው፡፡ ቀላል ግን እጅግ ወሳኝ አገልግሎት ሲሆን የተበታተነውን የተለያየ የሞባይል አካውንት በአንድ በማድረግ የሰራተኞችዎን የሞባይል ጥቅል ፍላጎት አሟልተው ቢሉን ደግሞ ወጥ በሆነ የመክፈያ መንገድ መፈፀም ይችላሉ፡፡

ለድርጅትዎ የሚሰጠው ዋና ዋና ጥቅሞች:

  • እጅግ ወጪ ቆጣቢ እና የቴሌኮም በጀትዎን ለመቆጣጠር ይረዳል፡ ከመደበኛ ዋጋ እጅግ በቅናሽ የቀረቡ የሞባይል ጥቅሎች ያገኙበታ እንዲሁም የቴሌኮም ወጪዎን ቀድመው እንዲያውቁ ይረዳል፡፡
  • ለአስተዳደር ቀላል ነው: የተለያዩ የሞባይል መስመሮችን ክፍያ ለመፈፀም የተወሳሰበ አካሄድ ከሚጠቀሙ በቀላሉ በአንድ አካውንት በማምጣት ለማስተዳደር የሚፈጅቦትን ጊዜ ቆጥበው በቀላሉ ክፍያ ይፈፅማሉ፡፡
  • የሰራተኞችዎን የቡድን መንፈስ ያጎለብታል፡ ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ ሰራተኞችዎ የስራ ላይ ግንኙነታቸውን እርስ በእርስ እንዲሁም ከንግድ አጋሮችዎ ጋር እንዲፈፅሙ ያግዛል፡፡
  • ምርታማነትን ይጨምራል:የአስተዳደር ጊዜን ስለሚቆጠብ ይህንን የሚያስተዳድሩ ሰራተኞችዎ ትኩረት ወደ የሚፈልጉ ስራዎች ፊታቸው እንዲያዞሩ ያደርጋል እንዲሁም የሰራተኞችዎ የስራ ላይ ግንኙነት በእጅጉ ስለሚያሳድግ ውጤታማነታቸው ይጨምራል፡፡
  • እንደፍላጎትዎ አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ:የሰራተኞችዎ ብዛት ሲጨምር የቴሌኮም ፍላጎትዎ እንደሚያድግ ግልፅ ነው፡፡ በዚህን ጊዜ ተጨማሪ የሞባይል ጥቅሎችን እንደፈለጉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሰራተኞችዎ ወጪ ቆጣቢ የሆነ እና ለአስተዳደር ቀላል የቴሌኮም አገልግሎት ከፈለጉ ለድርጅቶች በልዩነት የቀረቡ የሞባይል ጥቅሎቻችንን መጠቀም አይርሱ፡፡

ከዚህ በታች የቀረቡትን የሞባይል ጥቅሎቻችን ይመልከቱ!

ወርኃ ድምፅና የአጭር መልዕክት ጥቅሎች

ተ.ቁየአገልግሎቱ አይነትዋጋ በብር
1100 ደቂቃ + 25 መልዕክት35
2250 ደቂቃ + 50 መልዕክት68
3600 ደቂቃ + 150 መልዕክት135
41000 ደቂቃ + 250 መልዕክት205
51500 ደቂቃ + 375 መልዕክት273
62000 ደቂቃ + 500 መልዕክት340
73000 ደቂቃ + 750 መልዕክት410
85000 ደቂቃ + 1250 መልዕክት680
9ያልተገደበ ድምፅ + መልዕክት979

ወርኃዊ ዳታ ጥቅል

ተ.ቁየአገልግሎቱ አይነትዋጋ በብር
1500 ሜ.ባ40
21 ጊ.ባ60
32.5 ጊ.ባ140
45 ጊ.ባ250
510 ጊ.ባ455
615 ጊ.ባ589
720 ጊ.ባ660
830 ጊ.ባ780
950 ጊ.ባ960
10100 ጊ.ባ + ያልተገደበ መልዕክት1229
11150 ጊ.ባ + ያልተገደበ መልዕክት1250
12ያልተገደበ ዳታ + መልዕክት1300

ወርኃዊ ድምፅ እና ዳታ ጥቅል

ተ.ቁየአገልግሎቱ አይነትዋጋ በብር
11 ጊ.ባ + 200 ደቂቃ + 50 መልዕክት75
21 ጊ.ባ + 500 ደቂቃ + 150 መልዕክት135
35 ጊ.ባ + 600 ደቂቃ + 350 መልዕክት273
45 ጊ.ባ + 1500 ደቂቃ + 400 መልዕክት410
56 ጊ.ባ + 2000 ደቂቃ + 500 መልዕክት546
610 ጊ.ባ + 1000 ደቂቃ + 500 መልዕክት680
710 ጊ.ባ + 2000 ደቂቃ + 500 መልዕክት819
820 ጊ.ባ + 2000 ደቂቃ + 500 መልዕክት955
930 ጊ.ባ + 1500 ደቂቃ + 600 መልዕክት1090
1050 ጊ.ባ + 3000 ደቂቃ + 750 መልዕክት1365
11100 ጊ.ባ + 5000 ደቂቃ + 1250 መልዕክት1638
12ያልተገደበ ድምፅ + ዳታ + መልዕክት1699

የጅምላ መልዕክት ጥቅል

ተ.ቁየአገልግሎቱ አይነትዋጋ በሳንቲም በአንድ መልዕክት
1ከ10,000 በታች0.1366
210,001 እስከ 2,000,0000.0185
32,000,001 እስከ ያልተገደበ0.0178

ለድርጅቶች የቀረቡ የሞባይል ጥቅሎችን ከመጠየቅዎ በፊት ይህንን ደንብና ሁኔታ በጥንቃቄ ያንብቡ

ስለብቁነት:

  • ይህ አገልግሎት ለቅድመ ክፍያ፣ ድህረ ክፍያ ወይም ሀይብሪድ የሆኑ የሞባይል አካውንቶች በሙሉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  • ጥቅሎቹ የቀረቡት ለ2ጂ፣ 3ጂ፣እና 4ኔትወርክ ተጠቃሚዎች ብቻ የቀረቡ ናቸው፡፡

የግዢ አማራጮች:

  • የሞባይል ጥቅሎቹን ለመግዛት በአቅራቢያዎ የሚገኝ የድርጅት አገልግሎት መስጫ ማዕከሎቻችንን ይጎብኙ፡፡
  • ጥቅሎቹን ለአንድ ጊዜ ብቻ ወይም በየወሩ በቋሚነት መግዛት ይችላሉ፡፡

የጥቅል ዓይነት:

  • ጥቅሎቹን ለሰራተኞችዎ በቡድን ወይም ለተመረጠ አንድ ሰራተኛ ብቻ መግዛት ይችላሉ፡፡

ስለአጠቃቀም ደንብና ሁኔታዎች:

  • የቡድን ጥቅሎችን ስለማጋራት
  • በድርጅት ስም የተገዛን የሞባይል ጥቅል ለሌላ ሶስተኛ ወገን ማጋራት አይቻልም፡፡
  • ነገር ግን በድርጅቱ ስም ሳይሆን በግልዎ የገዙት የሞባይል ጥቅል ሞባይል ቁጥርዎ ላይ ካለ ግን ለእዛ ሞባይል በተፈቀደው ልዩ ደንብና ሁኔታ ለሌሎች ሊያጋሩት ይችላሉ፡፡
    • ጥቅል ስለመቀየር
  • የድምፅ እና መልዕክት ጥቅሎን በተመለከተ:በመደበኛው የሞባይል ጥቅል መቀየሪያ ህግ መሰረት መቀየር ይቻላል፡፡
  • ዳታ ጥቅሎች(500 ሜ.ባ እስከ 20 ጊ.ባ) ያሉት ወደ ሌላ ጥቅል መቀየር ይችላሉ፡፡
  • ሌሎች ዳታ ጥቅሎች ማለትም 30 ጊ.ባ፣ 50 ጊ.ባ፣100 ጊ.ባ፣ 150 ጊ.ባ እና ያልተገደበ ጥቅሎች ወደ ሌላ ጥቅል ቀይረው መጠቀም አይችሉም፡፡
    • የድምፅ እና የመልዕክት ጥቅሎችን በተመለከተ:እነዚህ ጥቅሎች ለመደወልም ሆነ መልዕክት መላላክ የሚፈቀደው ከተመሳሳይ የኢትዮ ቴሌኮም ኔትወርክ ቁጥር ብቻ ነው፡፡ ወደ ሌላ የአገር ውስጥ ኔትወርክ ለመደወል /መልዕክት ለመላላክ አያስችሉም፡፡
    • ከጥቅል ውጪ ሲጠቀሙ:የቀረቡትን ጥቅሎች ከወር በፊተ ቀድመው ቢጨርሱ የአገልግሎት ቀኑ (Expiry date) እስኪደርስ ድረስ ከዚህ በታች በተጠቀሱት ዝቅተኛ ዋጋዎች የሚከፍሉ ይሆናል፡፡
  • ዳታ:11 ሳንቲም በሜ.ባ
  • ድምጽ: 50 ሳንቲም በደቂቃ
  • መልዕክት: 12 ሳንቲም በመልክዕት

አጠቃላይ ህጎች

  • ነባር የሞባይል ጥቅል ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው፡፡

ዋጋ በተመለከተ

  • ሁሉም ዋጋዎች 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ እና 2% የኤክሳይስ ታክስ ያካተቱ ናቸው፡፡

አገልግሎቱን ለማግኘት

  • የሞባይል ጥቅሎቹን ለመግዛት በአቅራቢያዎ የሚገኝ የድርጅት አገልግሎት መስጫ ማዕከሎቻችንን ይጎብኙ፡፡