የዌቭ ሌንግዝ አገልግሎት

ዌቭ ሌንግዝ በፋይበር ኦፕቲክ አማካይነት የሚቀርብ ከፍተኛ የባንድዊድዝ አቅም እና ፍጥነት ያለዉ የዳታ እና ኢንተርኔት አገልግሎት ነው፡፡

ጥቅሞች

  • ከፍተኛ የመረጃ ደህንነት ፍላጎት ላላቸው ድርጅቶች የሚያገለግ ሲሆን ይህ አገልግሎት እያንዳንዱ የዳታ ቻናል ከሌላኛው በዌቭ ሌንግዝ (frequency) ስለሚለያይ በመረጃ ፍሰቱ ላይ ምንም አይነት የዳታ መደራረብ አይፈጠርም። በተጨማሪም የዌቭ ሌንግዝ አገልግሎት ከመደበኛው የኢንተርኔት አገልግሎት በተለየ መስመር ስለሚሰጥ ከደህንነት ስጋት ነጻ ነው።
  • እራሱን በቻለ መስመር ከፍተኛ ባንድዊድዝ የሚሰጥ በመሆኑ ከትራፊክ መጨናነቅ ነጻ በሆነ ከፍተኛ ፍጥነት ባለው አገልግሎት በማገዝ የቢዝነስ ስራዎን ውጤታማ ያደርጋል፡፡
  • ደንበኞች ከኩባንያችን ጋር የአገልግሎት አሰጣጥ ስምምነት (SLA) የሚገቡ በመሆኑ የተሻለ የጥገና እና አገልግሎት አሰጣጥ ይስተናገዳሉ እንዲሁም ከፍተኛ ፍጥነት እና አስተማማኝ አገልግሎት ያገኛሉ፡፡

ወርሃዊ Pizza Box (AGO10) ዋጋ


ሜትሮ


 ሪጂናል


አቅም (Capacity)

ፒ3

ፒ2

ፒ3

ፒ2

10 ጊ.ባ

98,032

135,678

244,276

354,908

8 ጊ.ባ

86,738

118,737

211,059

305,083

4 ጊ.ባ

60,386

79,209

133,554

188,824

1 ጊ.ባ

45,328

56,622

89,265

122,391

500 ሜ.ባ

41,564

50,975

78,192

105,783

100 ሜ.ባ

34,035

39,681

56,048

72,566

ማስታወሻ

  • ደንበኞች የ Pizza Box (AGO10) በራሳቸዉ የሚያቀርቡ ከሆነ ክፍያው በ21,873 ቅናሽ ያገኛሉ፡፡
  • ደንበኞች የረጅም ጊዜ ስምምነት ከፈጸሙ ተጨማሪ ቅናሽ ያገኛሉ፡፡
  • ሜትሮ - ሁለቱም ተጠቃሚዎች በአንድ ከተማ ውስጥ በ15 ኪ.ሜ ራዲየስ ውስጥ ከሆኑ እንደ ሜትሮ ይቆጠራል፡፡
  • ዶመስቲክ ወይም ሪጅናል - ሁለቱም ተጠቃሚዎች በአንድ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ከሆነ እንደ ዶመስቲክ ይቆጠራሉ፡፡
  • P3 (protection level three): ይህን አማራጭ የመረጡ ደንበኞች አገልግሎቱን ያለ መጠባበቂያ መስመር የሚያገኙ ይሆናል፡፡
  • P2 (protection level two): ይህን አማራጭ የመረጡ ደንበኞች አገልግሎቱን ከመጠባበቂያ መስመር ጋር የሚያገኙ ሲሆን በዋናው መስመር የአገልግሎት መቋረጥ ቢያጋጥም አገልግሎቱን በተዘረጋላቸው መጠባበቂያ መስመር መቀጠል ይችላሉ፡፡
  • የተገለጹት ዋጋዎች ተ.እ.ታ ያካትታሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ወደ 980/994 ይደውሉ ወይም በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የሽያጭ ማዕከላችን ጎራ ይበሉ