5ጂ ሞባይል ጥቅል New Speed, New Convenience, New Lifestyle በድርጅትዎ በልዩነት የቀረቡ የ5ጂ ኔትወርክ አገልግሎቶች መጠንን መሰረት ያደረገ የሞባይል ጥቅል ጥቅልወርኃ ዋጋ200 ጊ.ባ1,225 ብር500 ጊ.ባ1,910 ብር1 ቴራ ባይት 2,730 ብር ፍጥነትን መሰረት ያደረገ መደበኛ ዋየርለስ 5ጂ ኢንተርኔት (እውነተኛ የፍጥነት ገደብ የሌለው ኢንተርኔት የሚያገኙበት) የፍጥነት ገደብወርኃዊ ዋጋ50 ሜጋ ቢትስ በሰከንድ4,095 ብር100 ሜጋ ቢትስ በሰከንድ6,140 ብር200 ሜጋ ቢትስ በሰከንድ10,920 ብር ፍጥነትን መሰረት ያደረገ የ5ጂ ቪ.ፒ.ኤን አገልግሎት የፍጥነት ገደብወርኃዊ ዋጋ50 ሜጋ ቢትስ በሰከንድ4,095 Birr100 ሜጋ ቢትስ በሰከንድ6,140 Birr200 ሜጋ ቢትስ በሰከንድ10,920 Birr ደንብና ሁኔታዎች የድርጅት ደንበኞች የ5ጂ አገልግሎትን በቅድመ ክፍያ፣ ድህረ ክፍያ እንዲሁም የሀይብሪድ ሲም ካርድ በመጠቀም አገልግሎቱን በነጠላ ወይም በጅምላ ማግኘት ይቻላል፡፡ የቅድመ ክፍያ ደንበኞች የአየር ሰዓተ በመጠቀም፣ በጥሬ ገንዘብ እንዲሁም ቴሌብርን ተጠቅመው መግዛት ይችላሉ፡፡ መጠንን መሰረት ያደረጉት ጥቅሎች ዋጋ እና የጥቅል ሀብት ለአንድ ጊዜ ወይም በየወሩ በቋሚነት መግዛት ይቻላል፡፡ ፍጥነትን መሰረት ያደረጉት ጥቅሎች በድህረ ክፍያ አማራጭ በየወሩ በቋሚነት በነጠላ እንዲሁም ለጅምላ ሽያጭ የቀረቡ ናቸው፡፡ የ5ጂ ደንበኞች ከ5ጂ ኔትወርክ ሽፋን ውጭ በሚሆኑበት ጊዜ የ4ጂ ኔትወርክን በመጠቀም የገዙትን የዳታ ጥቅል መጠቀም ይችላሉ፡፡ አገልግሎቱን ለማግኘት በአቅራቢያዎ የሚገኙ የኢትዮ ቴሌኮም ሽያጭ ማዕከላትን መጎብኘት ይኖርቦታል፡፡ ለ5ጂ ከሽያጭ በኋላ ያሉ አገልግሎቶች ማለትም ከቅድመ ክፍያ ወደ ድህረክፍያ/ሀይብሪድ ለመቀየር፣ ከድህረ ክፍያ ወደ ቅድመ ክፍያ ለማዞር፣ ከ2ጂ/3ጂ/4ጂ ወደ 5ጂ ለማሳደግ፣ ሲም ካርድ በድጋሜ ለማውጣት፣ የባለቤት ለውጥ እና የመሳሰሉት አገልግሎቶች ከ4ጂ አገልግሎት ተመሳሳይ በሆነ ዋጋ የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡ ደንበኞች ሲም ካርዳቸውነ ከ5ጂ ወደ 4ጂ ፍጥነት ዝቅ በሚያደርጉበት ጊዜ የገዟቸው ጥቅሎች በ4ጂ ኔትወርክ የሚጠቀሙ ይሆናል፡፡ ያልተገደበ 4ጂ ጥቅል የገዙ ደንበኞች 5ጂ የሚያስጠቅም መገልገያ ቢኖራቸውም ሲም ካርዱ 5ጂ እስካልሆነ ድረስ የ5ጂ ኔትወርክ መጠቀም አይችሉም፡፡ ደንበኞች የቢሮ አድራሻቸውን መቀየር ከፈለጉ በቅድሚያ የቦታ ለውጥ ለማድረጋቸው በማሳወቅ ከክፍያ ነፃ በመሆነ መንገድ ይስተናገዳሉ፡፡ መጠንን መሰረት ያደረገ ጥቅል የገዙ ደንበኞች ጥቅላቸውን ከቀነ ገደቡ በፊት ቀድመው ከጨረሱ በ 0.4 ሣንቲም ክፍያ አገልግሎቱን ማግኘት መቀጠል ይችላሉ፡፡ ደንበኞች ለአገልግሎት ሲመዘገቡ ለመጀመሪያው ወር እንዲሁም አገልግሎቱን ሲያቋርጡ ወርሃዊ ክፍያ እና የጥቅል መጠን አገልግሎቱን ለሚያገኙበት ቀናት ብቻ ተሰልቶ የሚጠቀሙ እና የሚከፍሉ ይሆናል፡፡ መጠንን መሰረት ያደረገ የ5ጂ ጥቅል ወደ ሌላ ጥቅል መቀየር እንዲሁም ወደ ሌላ የ5ጂ የአገልግሎት ቁጥር ማስተላለፍ ይቻላል፡፡ ሁሉም ዋጋዎች ተ.እ.ታን ያካትታሉ፡፡ Please send your purchase request to Corporate.Enterprise@ethiotelecom.et OR Enterprise.Customer@ethiotelecom.et